Tuesday, November 28, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
- Advertisement -

ፌርማታ ፅሁፎች

እንዲህ ነው!

ትኩስ ፅሁፎች

የ፳(5) ዓመት ልጅ ፊደል ለመቁጠር፡፡

የ፰(8) ዓመት ልጅ ለማንበብ፡፡

የ፲፭(15) ዓመት ልጅ ጉባዔ ለመስማት፡፡

የ፲፰(18) ዓመት ልጅ ምሽት ለማግባት፡፡

የ፳(20) ዓመት ወጣት ለወታደርነት፡፡

የ፴(30) ዓመት ሙሉ ጉልበት፡፡

የ፵(40) ዓመት ላስተዋይነት፡፡

የ፶(50) ዓመት ላማካሪነት፡፡

የ፷(60) ዓመት እርጅና፡፡

የ፸(70) ዓመት ጥጥ ለመሰለ ሽበት፡፡

የ፹(80) ዓመት የመጨረሻ ጉልበት፡፡

የ፺(90) ዓመት ጉብጠት፡፡

የ፻(100) ዓመት ከሞተ ይቆጠር፡፡

ካንዲት ኢትዮጵያዊት ‹‹ምክርና ምሳሌ›› (1947)

* * *

‹‹መላ ጂስሜን ጦርፎ ይዞኝ››

አንድ የወሎ ባላገር ወደ ሐኪም ቤት ሂዶ ‹‹ሕመምህ ምንድን ነው? ሲባል ‹‹አንድ አንከለፍ ነገር መላ ጂስሜን ጦርፎ ይዞ መጧሪያዬ ላይ ያስጨንቀኛል›› አለ፡፡  ዶክተሩ ተጨንቆ ‹‹ይህን የሚተረጉም ልጅ የለዎትም ወይ?›› ሲል ‹‹አንተ ራስህ አማርኛ አታውቅም ወይ?›› ተባለ፡፡ አንባቢዎችስ ምን ማለት ይመስላችኋል? ጅስም ሰውነት፣ መጦረፍ ቀሥፎ መያዝ፣ መጧሪያ ፊንጢጣ (ሰገራ መውጫ) ማለት ነው፡፡ ባላገሩ መናገር የፈለገው ‹‹ፊንጥጣዬ ላይ ብጉንጅ የሚመስል እባጭ ተፈጥሮ ሰውነቴን ቀሥፎ ይዞ ያሰቃየኛል›› የሚል ነው፡፡ ይህም ብቻ ሳይሆን፣ አንዳንድ እናቶችም የራስ ሕመም  መከራና ሥቃይ ሲፈጥርባቸው ‹‹መጥረቢያውን ይዞ ግንባር ግንባሬን ይፈልጠኛል፤ መዶሻውን ይዞ ራስ ራሴን  ይመታኛል›› የሚሏቸው ቃላት ለትርጉም  ያስቸግራሉ፡፡

አዎ የአማርኛ ቋንቋ በየክፍለ ሀገሩ እንደዚህ የተለያዩ የንግግር ፈሊጦች አሉት፡፡ ለምሳሌ በመሐል አገር የአዲስ አበባ ሕዝብ አባባል (ዘይቤ በእንግሊዝኛው Dialects) ለመኪና ተጓዥ የሚነገረው ቃል ‹‹ተሳፈር›› የሚል ነው፡፡ በጎንደር ግን ተሳፈር ለማለት ‹‹በመኪና ላይ ተሰቀል›› ይላል፡፡

  • መክብብ አጥናው ‹‹የአእምሮ ማዝናኛ››  (2005)

* * *

ፊት አልባ ዓሳ ተገኘ

ከሰሞኑ የአውስትራሊያ አጥኚዎች ያልተለመደ እንግዳ ፍጥረት ማግኘታቸውን ላይቭ ሳይንስ ዘግቧል፡፡ የተገኘው ፍጥረት ፊት አልባ ዓሳ ሲሆን፣ ዓይንም ሆነ የፊት ቅርፅ እንደሌለው ተገልጿል፡፡ በምሥራቅ አውስትራሊያ በሚገኝ ባህር ውስጥ የተገኘው ይኼ ዓሳ አዲስ ፍጥረት አለመሆኑን፣ ነገር ግን እ.ኤ.አ. ከ1800 ጀምሮ ታይቶ እንደማይታወቅ የተሠሩ ጥናቶች አመልክተዋል፡፡ ዓሳው ከባህሩ የላይኛው አካል 4000 ሜትር ወደታች እንደሚኖር ታውቋል፡፡

* * *

ባለካሜራው ዓይን

ካናዳዊው ሮብ ስፔንስ የፊልም ባለሙያ ነው፡፡ አንድ ዓይኑ ላይ ችግር የተፈጠረው ገና በልጅነቱ ነው፡፡ በ40ዎቹ የዕድሜ ክልል የሚገኘው ስፔንስ ልጅ ሳለ ዓይኑ ላይ በደረሰው ጉዳት ብሌኑ እንዲወጣ የተደረገው ከጊዜ በኋላ ነበር፡፡ አርቲፊሻል ብሌን ከማስገጠም የተሻለ ነገር ሲያፈላልግ ብዙ ቆይቷል፡፡ ብሌኑን በካሜራ ለመተካትም ወሰነ፡፡ ካሜራው ለዓይኑ በሚመጥን መልኩ ለማዘጋጀት የተለያዩ ባለሙያዎችን ርብርብ ጠይቋል፡፡ ስፔንስ በዓይኑ የተገጠመውን ካሜራ የሚቆጣጠረው በማብራትና በማጥፋት (ኦን ኤንድ ኦፍ) በማድረግ ነው፡፡ ለ30 ደቂቃ ያህል በአካባቢው ያሉትን ነገሮች የመቅረፅ አቅም አለው፡፡ በሚቀርፅበት ሰዓት ቀይ መብራት የሚያበራ ሲሆን፣ የሰዎችን ትኩረት የሚሰጥና ሰዎች እየተቀረፁ እንደሆኑ ምልክት የሚሰጥ ነው፡፡ ይህ ከሌላው የግላዊነት መብት ጥሰት አኳያ ሊታይበት እንደማይችል እምነት እንዳለው ላይቭ ሳይንስ ዘግቧል፡፡

* * *

 

- Advertisement -
- Advertisement -

ተጨማሪ ለማንበብ

በብዛት የተነበቡ ፅሁፎች