Wednesday, September 27, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊየተመድ የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽነር በኢትዮጵያ የስደተኞች ቀን በዓል ላይ ይሳተፋሉ

የተመድ የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽነር በኢትዮጵያ የስደተኞች ቀን በዓል ላይ ይሳተፋሉ

ቀን:

በዘመኑ ተናኘና በታምራት ጌታቸው

በተባበሩ መንግሥታት ድርጅት (ተመድ) የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽነር ሚስተር ፍሊፕ ግራንዴ፣ የዘንድሮውን የዓለም አቀፍ የስደተኞች ቀን አስመልክቶ ኢትዮጵያ ይመጣሉ፡፡ በኢትዮጵያ በሚከበረው በዓለም አቀፍ ስደተኞች ቀን ላይ ይሳተፋሉ፡፡

በየዓመቱ ሰኔ 13 ቀን የሚከበረው ዓለም አቀፍ የስደተኞች ቀን ዘንድሮ ይከበራል፡፡ የ2009 ዓ.ም. የዓለም የስደተኞች ቀን ‹‹አጋርነት ለስደተኞች ወገኖቻችን›› በሚል መሪ ቃል በኢትዮጵያ ሲከበር፣ በዕለቱ በተለያዩ አገሮች የሚገኙ ስደተኞች እየገጠሙዋቸው ያሉትን ችግሮችና በመፍትሔዎቻቸው ላይ የዓለም አቀፉን ማኅበረሰብ በማስገንዘብ እንደሚከበር ታውቋል፡፡

ዕለቱ በጋምቤላ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት በጉኝል የደቡብ ሱዳን ስደተኞች መጠለያ ጣቢያ በልዩ ሁኔታ እንደሚከበር ተገልጿል፡፡ በዝግጅቱ ላይም የመንግሥት ከፍተኛ ባለሥልጣናት፣ ዲፕሎማቶችና የዓለም አቀፍ ድርጅት ተወካዮች እንደሚገኙ ለማወቅ ተችሏል፡፡

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የስደተኞች ኮሚሸን የዘንድሮው ዓለም አቀፍ የስደተኞች ቀን በኢትዮጵያ እንዲከበር የወሰነበት ዋነኛ ምክንያት፣ በአሁኑ ወቅት ኢትዮጵያ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ስደተኛ በማስተናገዷ በመሆኑ ነው፡፡ መረጃዎች እንደሚያመለክቱት፣ ኢትዮጵያ ስደተኞችን በማስተናገድ ረገድ ከአፍሪካ ቀዳሚ ናት፡፡ በአሁኑ ወቅት ከ850,000 በላይ ስደተኞች በኢትዮጵያ ተጠልለው ይገኛሉ፡፡ በስድስት ክልሎች በተቋቋሙ 27 የስደተኛ መጠለያ ጣቢያዎች መጠለያና ከለላ በመስጠት ላይ እንደሆነች ይታወቃል፡፡ 1,700 ስደተኞችም በ20 የአገሪቱ ዩኒቨርሲቲዎች የነፃ ትምህርት ዕድል እያገኙ መሆኑ ተገልጿል፡፡

በተመሳሳይ ዜና የስደተኞችና ከስደት ተመላሾች ጉዳይ አስተዳደር ዓርብ ሰኔ 9 ቀን 2009 ዓ.ም. ባወጣው መግለጫ መሠረት፣ ኢትዮጵያ ከ80 በመቶ በላይ የስደተኞችን ወጪ እየሸፈነች እንደሆነ ተጠቁሟል፡፡ የአስተዳደሩ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ዘይኑ ጀሚል፣ በኢትዮጵያ የስደተኞች ቁጥር እየጨመረ በመምጣቱ ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ የሚጠበቅበትን ግዴታ እንዲወጣ ጠይቀዋል፡፡ እነዚህ ስደተኞች በተፈጥሮና በሰው ሠራሽ ችግሮች ተጎድተው ባዶ እጃቸውን ወደ ኢትዮጵያ እንደሚመጡ አቶ ዘይኑ አስረድተዋል፡፡

ኢትዮጵያ ስደተኞችን እስከ መቼ እየደጎመች ትኖራለች? ተብለው ለተጠየቁት ጥያቄ አቶ ዘይኑ በሰጡት ምላሽ ‹‹አንድ ስደተኛ በመጀመርያ የዕለት ደራሽ ድጋፍ ነው የሚያስፈልገው፡፡ ነገሮች ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተለወጡ ባለመምጣታቸው የተነሳ ግን ከ20 ዓመታት በላይ በኢትዮጵያ የስደተኞች መጠለያ ካምፕ ውስጥ ተጠልለው ይገኛሉ፤›› ብለዋል፡፡ ‹‹በየቀኑ ዱቄት እየሰፈሩ ማኖር እንኳን እኛን ረጂዎችንም እያንገፈገፈ የመጣ ነው፤›› ብለዋል፡፡ ይኼንን ችግር ለመፍታት ሲባልም በአሁኑ ወቅት በልማት በመሰማራት ቢያንስ ራሳቸውን የሚያኖሩበትን መንገድ ለመፍጠር እየተሠራ መሆኑን የተናገሩት አቶ ዘይኑ፣ በቅርቡ ከደቡብ ሱዳን መሪዎች ጋር ስደተኞችን በተመለከተ የኢትዮጵያ መንግሥት መነጋገሩን አስረድተዋል፡፡

በ71ኛው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ኢትዮጵያ እስከ ዛሬ ላደረገችው በጎ የስደተኞች አቀባበልና አያያዝ ዕውቅና ሰጥቷል፡፡ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽነር ወደ ኢትዮጵያ በመምጣታቸው፣ ኢትዮጵያ ያለባትን የስደተኞች ጫና ለመቀነስ የተለያዩ ድጋፎች ልታገኝ እንደምትችል ይጠበቃል፡፡

 

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የአማራ ክልል ወቅታዊ ሁኔታ

እሑድ ጠዋት መስከረም 13 ቀን 2016 ዓ.ም. የፋኖ ታጣቂዎች...

ብሔራዊ ባንክ ለተመረጡ አልሚዎች የውጭ አካውንት እንዲከፍቱ ለመጀመሪያ ጊዜ የፈቀደበት መመርያና ዝርዝሮቹ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የውጭ ምንዛሪ አጠቃቀምንና ተያያዥነት ያላቸው ጉዳዮችን...

እነ ሰበብ ደርዳሪዎች!

ከሜክሲኮ ወደ ዓለም ባንክ ልንጓዝ ነው። ሾፌርና ወያላ ጎማ...