Friday, December 8, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
- Advertisement -

ፌርማታ ፅሁፎች

ኬፕታውንን የመታው ማዕበል

ትኩስ ፅሁፎች

የደቡብ አፍሪካዋ ኬፕታውን ገጥሟት በማያውቅ ዓይነት ማዕበል የተመታችው ባለፈው ሳምንት ነው፡፡ በሰዓት 100 ኪሎ ሜትር በሚነፍሰው ነፋስና በከባድ ዝናብ አማካይነት በተነሳው ማዕበል የአገሪቱ ውኃማ አካባቢዎች ተናውጠዋል፡፡ ኬፕታውንን ጨምሮ ምዕራባዊ ኬፕ በማዕበሉ የተመቱ ሲሆን፣ ስምንት ሰዎችም ሞተዋል፡፡ በዚህ ሳምንት ማዕበሉ እየተረጋጋ ቢሆንም፣ የአየሩ ሁኔታ አልተስተካከለም፡፡ ማዕበሉ በኬፕታውን ጎዳናዎች የሚያልፉ መኪናዎችን፣ ሕንፃዎችንና ጎዳናዎችን መምታቱን አልጀዚራ ዘግቧል፡፡ 

ለሥዕል

አያልቅም ይህ ጉዞ …

ማስመሰል መተርጎም

በቀለም መዋኘት፤

      በመስመር መጫወት፤

      ከብርሃን መጋጨት፤

ለማወቅ ለመፍጠር ባዶ ቦታ መግባት፤

መፈለግ …. መፈለግ …

አዲስ ነገር መፍጠር፡፡

ከማይታየው ጋር ሄዶ መነጋገር

ሕይወትን መጠየቅ፤

ሐሳብን መጠየቅ፤

ዓለምን መጠየቅ፤

            መሄድ፤ መሄድ መሄድ….

ከጨረቃ በላይ፣

      ከኮከቦች በላይ፤

      ከሰማዩ በላይ፤

መጓዝ ወደ ሌላ – ባዶ ቦታ መግባት

በሐሳብ መደበቅ፤

      መፈለግ – ማስገኘት

አያልቅም ይህ ጉዞ …

ገብረክርስቶስ ደስታ ‹‹መንገድ ስጡኝ ሰፊ›› (2006)

****

ከቤት የማያስወጣ የግንባር ላይ ንቅሳት

ሌቦች እጅ ከፍንጅ ሲያዙ የተለያዩ ዓይነት ድብደባዎች ይፈጸሙባቸዋል፡፡ አንዳንዶች በእጅና በእግራቸው ሲመቷቸው፣ ዱላ ይዘው እስኪደሙ የሚደበድቡም አሉ፡፡ በኬንያ ሌባ እጅ ከፍንጅ ከተያዘ የተደራረበ የመኪና ጎማ ውስጥ ከቶ ማቃጠል የተለመደ ነው፡፡ ሰሞኑን የተከሰተው ደግሞ ከእነዚህ ለየት ያለ ነው፡፡ ሁለት ብራዚላውያን፣ ባይስክል ሰርቆናል ብለው የጠረጠሩትን የ17 ዓመት ታዳጊ ግንባሩ ላይ ‹‹እኔ ሌባ ነኝ›› የሚል ንቅሳት አድርገውበታል፡፡ ታዳጊው ግንባር ላይ ንቅሳቱን ሲያደርጉ በቪዲዮ የቀረጹት ሁለቱ የንቅሳት ባለሙያዎች በቁጥጥር ስር የዋሉ ሲሆን፣ ‹‹ሰው በማሰቃየት›› ወንጀልም ተከሰዋል፡፡

የ17 ዓመቱ ታዳጊ ሌብነት አለመፈጸሙን ለፖሊስ የተናገረ ቢሆንም፣ ከደረሰበት ሥነ ልቦናዊ ጉዳት አንፃር ለአንድ ሳምንት ያህል ራሱን ደብቆ ነበር፡፡ ከሳምንት ፍለጋ በኋላ የተገኘውን ታዳጊ ንቅሳት ለማጥፋትና ለሕክምና አብሮ አደጎቹ ገቢ እያሰባሰቡ ቢሆንም፣ ንቅሳቱን የሠሩት ሰዎች ‘ንቅሳቱን ካጠፋህ እንገድልሃለን’ ብለውኛል ማለቱን ሚረር ዘግቧል፡፡ ታዳጊው ግንባር ላይ በፖርቹጊዝ የተጻፈው ሲተረጎም ‹‹እኔ ሌባ ነኝ›› የሚል መሆኑን ዘገባው ያሳያል፡፡

********

ምድር ለምድር የሚቀበር ቢራ ማስተላለፊያ ቱቦ

መሬት ለመሬት የሚቀበሩ ቱቦዎች በአብዛኛው ለፍሳሽ ቆሻሻ፣ ለነዳጅ ወይም ለውኃ ማስተላለፊያነት የሚውሉ ቢሆንም፣ አሁን ላይ ቢራ ለማስተላለፍም ጥቅም ላይ እየዋሉ ነው፡፡ በቢራ አፍቃሪነታቸው የሚታወቁት ጀርመኖች ቢራን ምድር ለምድር ለማስተላለፍ የቱቦ ቀበራ ግንባታ ጀምረዋል፡፡ ኤንቢሲ ኒውስ እንደዘገበው፣ የቢራ ማስተላለፊያ ቱቦ ቀበራው ሰባት ኪሎ ሜትር የሚሸፍን ሲሆን፣ በነሐሴ በአገሪቱ ይካሄዳል ለተባለው ፌስቲቫልም 400,000 ሺሕ ሊትር ቢራ የሚተላለፍበት ይሆናል፡፡

****

- Advertisement -
- Advertisement -

ተጨማሪ ለማንበብ

በብዛት የተነበቡ ፅሁፎች