Tuesday, December 5, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊከደቡብ ክልል የሚፈልሱትን ለመታደግ

ከደቡብ ክልል የሚፈልሱትን ለመታደግ

ቀን:

በኢትዮጵያ ለ26ኛ ጊዜና በአፍሪካ ለ27ኛ ጊዜ የሚከበረው የአፍሪካ ሕፃናት ቀን ሰኔ 9 ቀን 2009 ዓ.ም. ‹‹በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የሚገኙ ሕፃናትን ለመደገፍ የሁሉም አካላት ተሳትፎ ወሳኝ ነው፤›› በሚል መሪ ቃል ይከበራል፡፡ ቀኑ በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦች ሕዝቦች ክልላዊ መንግሥት የሴቶችና ሕፃናት ጉዳይ ቢሮ አስተባባሪነት በክልሉ ርዕሰ ከተማ ሐዋሳ፣ ሰኔ 6 እና 7 የሚከበር ሲሆን፣ ቢሮው ለሪፖርተር እንዳስታወቀው፣ የሕፃናት ፍልሰትና የጎዳና ተዳዳሪነትን መቅረፍ በዘንድሮው የሕፃናት ቀን ትኩረት ተሰጥቷቸዋል፡፡ የክልሉ ሕፃናት ቤተሰቦቻቸውን በሞት ሲነጠቁ፣ የኢኮኖሚ ችግር ሲገጥማቸው፣ በዕድሜ እኩዮቻቸው በመገፋፋትና በደላሎች ሕገወጥ ዝውውር ሳቢያ ከትውልድ ቀዬያቸው እየፈለሱ ለጎዳና ተዳዳሪነትና ለጉልበት ብዝበዛ እየተዳረጉ ነው፡፡ የደቡብ ክልል ትምህርት ቢሮ ኃላፊ  እሸቱ ከበደ (ዶ/ር)፣ የደቡብ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ፍስሐ ጋረደው፣ የደቡብ ክልል ጤና ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር አብርሃም አላሮ፣ የደቡብ ክልል ፍትሕ ቢሮ ኃላፊ አፀደ አይዛ እና የደቡብ ክልል የሴቶችና ሕፃናት ቢሮ  ምክትል ኃላፊ ወ/ሪት ትዝታ ፍቃዱ እንደገለጹት፣ አዲስ አበባን ጨምሮ ወደ ተለያዩ የአገሪቱ ከተሞች ከክልሉ የሚፈልሱ ሕፃናትን ለመታደግ የድርሻቸውን እየተወጡ ነው፡፡ በትምህርት ረገድ ትምህርት ቤቶችን በማስፋፋትና ሕፃናት በአግባቡ ትምህርታቸውን እንዲከታተሉ የግብዓት ድጋፍ በማድረግ ላይ ይገኛሉ፡፡ ሕገወጥ የሕፃናት ዝውውርን ለመቆጣጠር በሚደረገው ጥረት አምና 8,617፣ ዘንድሮ 4,859 ሕፃናት ከጎዳና ተነስተው ቤተሰቦቻቸውን እንዲቀላቀሉ ተደርጓል፡፡ አዲስ አበባና ጅማ ይኖሩ የነበሩ 1,181 የክልሉ ተወላጆች ወደ ማገገሚያ ተቋም መግባታቸውም ተገልጿል፡፡ ዘንድሮ 2,754 ወላጅ አልባ ሕፃናት ለአደራ ቤተሰብ፣ 565 ሕፃናት ደግሞ ለአገር ውስጥ ጉዲፈቻ ተሰጥተዋል፡፡ በተጨማሪም 44,457 ሕፃናት ከቤተሰቦቻቸው ጋር እየኖሩ ድጎማ እየተደረገላቸው ነው፡፡ ሆኖም አሁንም ከክልሉ የሚፈልሱ ታዳጊዎች በዋነኛነት በአዲስ አበባና ሌሎችም ከተሞች እየተጉላሉ በመሆኑ ሰፊ ሥራ እንደሚጠይቅ አሳውቀዋል፡፡ አሁንም የክልሉ ተወላጅ የሆኑ ሕፃናት ወደ ሌሎች አካባቢዎች እየፈለሱ ሲሆን፣ በሚኖሩበት አካባቢም የተመቻቸ ሕይወት ስለማይገጥማቸው ለእንግልት እየተዳረጉ ይገኛሉ፡፡ (ፎቶ በመስፍን ሰለሞን)

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

በዓለም አቀፍ ደረጃ ሕይወታቸውን በኤድስ ምክንያት ላጡ ሰዎች 35ኛ ዓመት መታሰቢያ

ያለፍንበትን እያስታወስን በቁርጠኝነት ወደፊት እንጓዝ - በኧርቪን ጄ ማሲንጋ (አምባሳደር) በየዓመቱ...

እዚያ ድሮን… እዚህ ድሮን…

በዳንኤል ካሳሁን (ዶ/ር) ተዓምራዊው የማዕበል ቅልበሳ “በሕግ ማስከበር” ዘመቻው “በቃ የተበተነ...

ለፈርጀ ብዙ የማንነት ንቃተ ህሊናችን የሚጠቅሙ ጥቂት ፍሬ ነገሮች

በበቀለ ሹሜ ከጨቅላነት ጅምሮ ያለ የእያንዳንዳችን የሰብዕና አገነባብ ከቤተሰብ እስከ...