Friday, June 2, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊየወሎ ተርሸሪ ኬርና ማስተማሪያ ሆስፒታል ግንባታ ተጀመረ

የወሎ ተርሸሪ ኬርና ማስተማሪያ ሆስፒታል ግንባታ ተጀመረ

ቀን:

  • ከአምስት ቢሊዮን ብር በላይ ይፈጃል

የግንባታና የሕክምና ቁሳቁስ ወጪን ጨምሮ 5.5 ቢሊዮን ብር ያህል ይፈጃል የተባለው ወሎ ተርሸሪ ኬርና ማስተማሪያ ሆስፒታል ግንባታ ተጀመረ፡፡

ከደሴ በስተሰሜን ሰባት ኪሎ ሜትር ርቆ በሚገኘው ጢጣ በ470 ሺሕ ካሬ ሜትር ቦታ ላይ ግንባታው የተጀመረው ወሎ ተርሸሪ ኬርና ማስተማሪያ ሆስፒታል፣ አምስት ዕርከኖች (ሎቶች) ሲኖሩት፣ ሰሞኑን ግንባታው የተጀመረው የመጀመሪያው ዕርከን  የድኅረ ምረቃው ትምህርት ቤት ነው፡፡  

ለግንባታው 3.5 ቢሊዮን ብር ለሕክምና ቁሳቁስ ሁለት ቢሊዮን ብር የሚፈጀውን የሆስፒታሉን ግንባታ ዮሴፍ ወንድሙ ሕንፃ ተቋራጭ የያዘው ሲሆን፣ አማካሪውም አክዩት ኮንሰልታንት መሆኑን የሆስፒታሉ ፕሮጀክት ሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ፀጋዬ አህመድ ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡

አቶ ፀጋዬ እንዳሉት፣ የሁለተኛው ዕርከን ማለትም የቅድመ ምረቃ ተማሪዎች ትምህርት ቤት ግንባታን ለማስጀመር ዓለም አቀፍ ጨረታ የወጣ ሲሆን፣ የሦስተኛና አራተኛ ዕርከኖችን ግንባታ ለማስጀመር ለጨረታ ዝግጁ እየተደረገ ነው፡፡

አምስተኛውና የግንቦታው የመጨረሻው አካል የሆስፒታሉ ግንባታ ሲሆን፣ ይህንንም ለማስጀመር የዲዛይን ሥራው በመጠናቀቅ ላይ እንደሆነ አቶ ፀጋዬ ተናግረዋል፡፡ እስከ 2010 ዓ.ም. አጋማሽ ድረስ ሁሉም የሕንፃ ክፍሎች ወደ ግንባታ ይገባሉ ተብሎ የሚጠበቀው የሆስፒታሉ ፕሮጀክት፣ ይገነባል ተብሎ የመሠረት ድንጋይ የተቀመጠለት ኅዳር 16 ቀን 2004 ዓ.ም. ነበር፡፡

የመሠረት ድንጋዩ ሲቀመጥ፣ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን፣ የወቅቱ የአማራ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ አያሌው ጎበዜና የፕሮጀክቱ የበላይ ጠባቂ ሼሕ መሐመድ ሁሴን ዓሊ አል አሙዲ ተገኝተው ነበር፡፡ በወቅቱም ግንባታው በ2012 ዓ.ም. እንደሚጠናቀቅ ተነግሮ ነበር፡፡

ከዲዛይን ማሻሻል ጋር በተያያዘ ግንባታው የዘገየውና በግንቦት 2009 ዓ.ም. ግንባታው የተጀመረው ወሎ ተርሸሪ ኬርና ማስተማሪያ ሆስፒታል፣ ግንባታው ሙሉ ለሙሉ ሲጠናቀቅ 700 ያህል ተኝተው፣ በሺዎች የሚቆጠሩ ደግሞ በተመላላሽነት እንዲታከሙ የሚያስችል ይሆናል፡፡ ከ1500 በላይ አዲስ ተማሪዎችን በመጀመሪያ ዲግሪ፣ በተወሰኑ የሕክምና መስኮች ከ200 በላይ ስፔሻላይዜሽንና ሰብ ስፔሻላይዜሽን ሐኪሞችን፣ ለሥራ ላይ ሙያተኞች አጫጭር ሥልጠና ይሰጣል፡፡

ለሆስፒታሉ ግንባታ ከቴሌቶንና ከቶምቦላ 60 ሚሊዮን ብር ያህል የተገኘ ሲሆን፣ ወሎ ዩኒቨርሲቲም በጀት በየዓመቱ በመጠየቅ የሚገነባው ነው፡፡ 

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የአዛርባጃንን ብሄራዊ ቀን በአዲስ አበባ በድምቀት ተከበረ

የአዛርባጃን ኤምባሲ  የአዛርባጃንን ብሄራዊ ቀን በትላንትናው ዕለት አከበረ። ሰኞ...

የመንግሥትና የሃይማኖት ልዩነት መርህ በኢትዮጵያ

እንደ ኢትዮጵያ ባሉ አገሮች የሃይማኖት ተቋማት አዎንታዊ ሚና የጎላ...

ሐበሻ ቢራ ባለፈው በጀት ዓመት 310 ሚሊዮን ብር የተጣራ ትርፍ ማግኘቱን አስታወቀ

የአንድ አክሲዮን ሽያጭ ዋጋ 2,900 ብር እንዲሆን ተወስኗል የሐበሻ ቢራ...