Saturday, April 1, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊየኢትዮጵያ ምርት ገበያ አዳዲስ የቦርድ አባላት ተሾሙለት

የኢትዮጵያ ምርት ገበያ አዳዲስ የቦርድ አባላት ተሾሙለት

ቀን:

የኢትዮጵያ ምርት ገበያን በበላይነት የሚመሩ አዳዲስ የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት ሹመት ፀድቆ ሥራ ጀመሩ፡፡ የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ ሳኒ ረዲ አዲሱ የምርት ገበያው የቦርድ ሊቀመንበር ሆነው ተሰይመዋል፡፡

 

ዘጠኝ አባላት ያሉት የምርት ገበያው የቦርድ አመራሮች ውስጥ አምስቱ በቀጥታ በንግድ ሚኒስቴር በኩል በመንግሥት የሚሾሙ ሲሆን፣ ቀሪዎቹ አራቱ ደግሞ ከግል ዘርፍ የሚወከሉና ሹመታቸውም በንግድ ሚኒስቴር አማካይነት የፀደቀ ነው ተብሏል፡፡

በዚህ መሠረት በንግድ ሚኒስቴር በኩል ሹመታቸው ፀድቆ በምርት ገበያው ቦርድ ውስጥ የተካተቱት የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ገበያ ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ ሳኒ ረዲና የትራንስፖርት ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ ካሳሁን ኃይለ ማርያም ይገኙበታል፡፡ ከሁለቱ በተጨማሪ ምርት ገበያን በቦርድ አባልነት እንዲያገለግሉ የተሰየሙት አቶ ተስፋዬ መንግሥቴ፣ አቶ ጌታቸው ነጋሽ፣ አቶ ዘካሪያስ ኢርኮላ፣ አቶ ሙሉጌታ ዓለማየሁ፣ አቶ ሁሴን አራጋው፣ አቶ ዘሪሁን ቀሚሶና አቶ ካሳሁን በቀለ ናቸው፡፡

ከዚህ ሹመት ቀደም ብሎ የቀድሞው ግብርና ሚኒስትር አቶ ተፈራ ደርበው ቦርዱን በሊቀመንበርነት ሲመሩ ነበር፡፡  

የአዲሱ ቦርድ አሰያየም ከምርት ገበያው አዳዲስ አሠራር ጋር በተለይም ቡናን ሪፎርም ለማድረግ ከተያዘው ዕቅድ ጋር ተያይዞ፣ ሁሉንም ባለድርሻ አካላት ያሳተፈ እንዲሆን ታስቦ የተዋቀረ ነው ተብሏል፡፡  

ከስምንት ዓመታት በላይ ዕድሜ ያለው የኢትዮጵያ ምርት ገበያ በምሥረታው ማግሥት የመጀመርያው የቦርድ ሊቀመንበር በመሆን ሲያገለግሉ የነበሩት አቶ አዲሱ ለገሰ ሲሆኑ፣ እስካሁን ድረስ አራት ጊዜ የቦርድ ሊቀመናብርት ተፈራርቀዋል፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ ከቡና ሪፎርም ጋር በተያያዘ በተለይ የወጪ ንግዱን ያግዛሉ፣ አዳዲስ አሠራሮችን ተግባራዊ ለማድረግ ያስችላሉ የተባሉ የሕግ ረቂቆች እየተዘጋጁ ሲሆን፣ የበጀት ዓመቱ ከመጠናቀቁ በፊት ይፀድቃሉ ተብለው እየተጠበቁ ነው፡፡ ተግባራዊ ይሆናሉ ተብለው ከሚጠበቁት አዳዲስ አሠራሮች መካከል ቡናን በቀጥታ ከተሽከርካሪ ላይ መሸጥ አንዱ ነው፡፡ ስፔሻሊቲ ቡና የሚያስተዳድር ማለትም ከምርት ገበያው ውጪ በቀጥታ ወደ ውጭ ለመላክ የሚያስችሉ አሠራሮችን የሚፈቅድ አካሄድ ማስተዋወቅና ሌሎች አዳዲስ የማስፈጸሚያ መመርያዎች ይገኙበታል፡፡

 በምርት ገበያው የቡና ዋና የግብይት አስፈጻሚ በመሆን በከፍተኛ ገንዘብ ወንበሮች በገዙ አገበያዮች በኩል የግዴታ ግብይት እንዲፈጸም ያስገድድ የነበረው የምርት ገበያውን አሠራር ይለውጣል የተባለ መመርያም ይፀድቃል ተብሎ እየተጠበቀ ነው፡፡ ይኼ መመርያ ከፀደቀ ባለወንበር አገበያዮችን በውድድር ግብይት እንዲፈጽሙ ያደርጋቸዋል፡፡     

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ተወግዘው የነበሩ ሦስቱ ሊቀጳጳሳትና 20 ተሿሚ ኤጲስ ቆጶሳት ውግዘት ተነሳ

_ቀሪዎቹ ሦስት ህገወጥ ተሿሚዎች የመጨረሻ እድል ተሰጥቷቸዋል ​ ጥር 14...

በሕወሓት አመራሮች ላይ ተመስርቶና በሂደት ላይ የነበረው የወንጀል ክስ ተቋረጠ

በቀድሞ የትግራይ ክልል ፕሬዚደንት ደብረጽዮን ገብረሚካኤ,(ዶ/ር)ና ባለፈው ሳምንት በተሾሙት...

[የምክር ቤቱ አባል ላቀረቡት ጥያቄ በተሰጣቸው ምላሽ አቤቱታቸውን ለክቡር ሚኒስትሩ እያቀረቡ ነው]

ክቡር ሚኒስትር እየሆነ ያለው ነገር ትክክል ነው? ምነው? ምክር ቤቱም ሆነ...

የጉራጌ የክልልነት ጥያቄ ትኩሳት

ቅዳሜ መጋቢት 16 ቀን 2015 ዓ.ም. በጉራጌ ዞን ወልቂጤ...