Friday, June 9, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ስፖርትአዳነ ግርማና አሠልጣኝ ውበቱ አባተ ዕገዳ ተጣለባቸው

አዳነ ግርማና አሠልጣኝ ውበቱ አባተ ዕገዳ ተጣለባቸው

ቀን:

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የዲስፕሊን ጥሰት ፈጽመዋል ባላቸው የቅዱስ ጊዮርጊስ ተጫዋች አዳነ ግርማና የሐዋሳ ከተማ አሠልጣኝ ውበቱ አባተ ላይ ቅጣት ጣለ፡፡

በፕሪሚየር ሊጉ 19ኛ ሳምንት ጨዋታ ሻምፒዮኑ ቅዱስ ጊዮርጊስ ከፋሲል ከነማ ጋር ሲጫወት፣ አምበሉ አዳነ ግርማ ጨዋታውን የመራውን ዳኛ ለመደባደብ በመጋበዙና ምራቁን በመትፋቱ ፌዴሬሽኑ ከሚያዘጋጀው ውድድር ለስድስት ወራት አግዶታል፡፡ በተጨማሪም የ10 ሺሕ ብር ቅጣትም ተላልፎበታል፡፡

ብሔራዊ ፌዴሬሽኑ ግንቦት 30 ቀን 2009 ዓ.ም. ይፋ እንዳደረገው፣ አዳነ ከፍተኛ ቅጣት ያልተጣለበት ለብሔራዊ ቡድንና ለክለቡ ለረጅም ጊዜ የሰጠውን አገልግሎት ከግምት ውስጥ በማስገባት ነው፡፡

በሌላ በኩልም አሠልጣኝ ውበቱ አባተ ግንቦት 10 ቀን 2009 ዓ.ም. ድሬዳዋ ከተማ ከሐዋሳ ከተማ ጋር የፕሪሚየር ሊግ 2ኛ ዙር እግር ኳስ ጨዋታውን ባደረገበት ዕለት፣ በ35ኛው ደቂቃ ዋና ዳኛው ለድሬዳዋ ከተማ ቡድን የሰጡት ፍፁም ቅጣት ምት በመቃወም ያልተገባ ድርጊት በመፈጸሙ ለአንድ ዓመት ከአሠልጣኝነት እንዲታገድና 30 ሺሕ ብር እንዲቀጣ ተወስኖበታል፡፡

 በተመሳሳይ ሁኔታ ወላይታ ድቻ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጋር ወላይታ ላይ በተጫወቱበት ዕለት የድቻ ደጋፊዎች ከስፖርታዊ ጨዋነት ውጪ በፈጸሙት ድርጊት ጥፋተኛ ሆነው በመገኘታቸው የወላይታ ድቻ እግር ኳስ ክለብ 25 ሺህ ብር እንዲቀጣ ፌዴሬሽኑ ውሳኔ አስተላልፏል፡፡

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በላከው የዲስፕሊን ኮሚቴ ውሳኔ መሠረት፣ ግንቦት 5 ቀን 2009 ዓ.ም. መቐለ ከተማ ከባህር ዳር ከተማ የከፍተኛ ሊግ ሁለተኛ ዙር 23ኛ ሳምንት የእግር ኳስ ጨዋታቸውን እያካሄዱ እያለ ደጋፊዎች ወደ ሜዳ በመግባታቸውና ከተጫዋቾች ጋር በመደባደባቸው 100 ሺሕ ብር መቀጣታቸውን አስታውቋል፡፡ እንዲሁም የባህር ዳር ከተማ ክለብን በተመለከተ በዕለቱ በተፈጠረው ሁከት ላይ ተሳትፈዋል ያላቸው ተጫዋቾች እንዲሁም የክለቡ የተለያዩ ባለሙያዎችን እያንዳንዳቸውን አራት ሺሕ ብር ቅጣት ወስኖባቸዋል፡፡

 

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ