Wednesday, July 24, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ስፖርትበዓለም ሻምፒዮና የሚወዳደሩ የማራቶን አትሌቶች ዝርዝር ይፋ ተደረገ

በዓለም ሻምፒዮና የሚወዳደሩ የማራቶን አትሌቶች ዝርዝር ይፋ ተደረገ

ቀን:

  በመጪው ሐምሌ 2009 ዓ.ም. በለንደን በሚካሄደው 16ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ላይ ኢትዮጵያን በማራቶን ወክለው የሚቀርቡ ብሔራዊ አትሌቶች ዝርዝር ይፋ ሆኗል፡፡ የኦሊምፒክና የዓለም ሻምፒዮናዎቹ ቀነኒሳ በቀለና ጥሩነሽ ዲባባ የመጀመርያዎቹ ሆነዋል፡፡

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ምርጫውን አስመልክቶ በላከው መግለጫ መሠረት፣ ምርጫው ከመስከረም 2009 ዓ.ም. ጀምሮ የለንደን ማራቶን እስከተካሄደበት ያለውን የውድድር ውጤት ያካተተ ነው፡፡

በዚሁ መሠረትም በወንዶች ቀነኒሳ በቀለ በበርሊንና ለንደን ማራቶኖች አንደኛና ሁለተኛ ሆኖ ያጠናቀቀበት ሰዓት የመጀመሪያ ተመራጭ አድርጎታል፡፡ በሁለተኛ ደረጃ የተመረጠው ታምራት ቶላ ሲሆን፣ በዱባይ ማራቶን አንደኛ ሆኖ ያጠናቀቀበት ሰዓት ተወስዶለታል፡፡ ሦስተኛው ፀጋዬ መኰንን ደግሞ በጀርመን ሐምቡርግ ማራቶን ያሸነፈበት ሰዓት ተወስዶለታል፡፡ በተጠባባቂነት የማነ ፀጋዬና ሙሴ ዋሲሁን ተይዘዋል፡፡

በሴቶች ጥሩነሽ ዲባባ በለንደን ማራቶን ሁለተኛ የወጣችበት ሰዓት የመጀመሪያ አድርጎ ሲያስመርጣት፣ ብርሃኔ ዲባባ በቶኪዮና በርሊን ማራቶኖች ሁለተኛ በመሆን ያጠናቀቀችበት ሰዓት ተወስዶላታል፡፡ በሦስተኛ ደረጃ ደግሞ ሹሬ ደምሴ በካናዳ ቶሮንቶና በዱባይ ማራቶኖች አንደኛና ሁለተኛ የወጣችበት ሰዓት አስመርጧታል፡፡ በለንደን ኦሊምፒክ የነሐስ ሜዳሊያ አሸናፊዋ ማሬ ዲባባ ቀጥታ ተሳታፊ እንደምትሆንም ተነግሯል፡፡ በተጠባባቂነት አሰለፈች መርጊያና አማኔ ጎበና መያዛቸው ታውቋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

[ክቡር ሚኒስትሩ ከተቋሙ የሠራተኞች ማኅበር አመራር ጋር እየተወያዩ ነው]

ጤና ይስጥልኝ ክቡር ሚኒስትር? ሰላም! በአስቸኳይ እንደፈለጉኝ መልዕክት ደርሶኝ ነው የመጣሁት። አዎ።...

የሱዳን ጦርነትና የኢትዮጵያ ሥጋት

የሱዳን ጦርነት ከጀመረ አንድ ዓመት ከአራት ወራት አስቆጠረ፡፡ ጦርነቱ...

ግለሰብ ነጋዴዎችን በአስገዳጅነት የንግድ ምክር ቤት አባል ለማድረግ ያለመው ረቂቅ አዋጅ ተከለሰ

በምትኩ የንግድ ተቋማት በአስገዳጅነት የንግድ ምክር ቤት አባል ይሆናሉ...

አሳርና ተስፋ!

ከቱሉ ዲምቱ ወደ ቦሌ ጉዞ ልንጀምር ነው፡፡ ገና ከመንጋቱ...