Tuesday, July 23, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ስፖርትኦሊምፒክ ኮሚቴ ጥቅማ ጥቅምን በተመለከተ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ያቀረበው ጥያቄ ይሁንታ አገኘ

ኦሊምፒክ ኮሚቴ ጥቅማ ጥቅምን በተመለከተ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ያቀረበው ጥያቄ ይሁንታ አገኘ

ቀን:

የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ በስፖርቱ መስክ አንኳር ያላቸውን ችግሮች ለጠቅላይ ሚኒስትሩ አቅርቦ ቀና ምላሽ ማግኘቱ ተገለጸ፡፡ በአትሌቲክስ ውጤት አልባ ካደረጉ ምክንያቶች መካከል ቀድሞ ለአትሌቶች ይሰጡ የነበሩ ማበረታቻና ጥቅማ ጥቅሞች መቋረጣቸው አንዱ ነው፡፡

ብሔራዊ ኦሊምፒክ ኮሚቴው ባለፈው ሐሙስ ግንቦት 24 ቀን 2009 ዓ.ም. በጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ ጽሕፈት ቤት በመገኘት ያቀረባቸው ጥያቄዎች ቀድሞ ውጤታማ አትሌቶች ያገኙት የነበረው የቤት፣ የቦታ፣ የገንዘብና የመሳሰሉት ሽልማቶችና ጥቅማ ጥቅሞች መቋረጣቸው ውጤቱ ላይ ተፅዕኖ ማሳደሩንና ይኼው ለወደፊቱ እንዲታይና ዳግመኛ እንዲጀመር የሚለው ይገኝበታል፡፡

ከዚህም ባሻገር በዘርፉ የሚመለከታቸውን ተቋማት እያነታረከ የቆየውና በደብረ ዘይት መንገድ ሪቼ (እምቧይ መስክ) ተብሎ የሚታወቀው ማዘውተሪያ ጉዳይም በጠቅላይ ሚኒስትሩ ምላሽ ተሰጥቶበታል ተብሏል፡፡ ብሔራዊ ኦሊምፒክ ኮሚቴው እንዳስታወቀው፣ ሪቼ (እምቧይ መስክ) የሚገኘው የስፖርት ማዘውተሪያ ቦታ ለኦሊምፒክ አካዴሚ መገንቢያ እንዲውልና በባለቤትነትም የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ እንዲያስተዳድረው ይሁንታና ማረጋገጫ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ መገኘቱ ተናግሯል፡፡

በሌላው በኩልም በተለይም ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ መንግሥት ለውጤታማ አትሌቶች ይሰጥ የነበረው ጥቅማ ጥቅም በጊዜ ሒደት እየቀነሰና እየተቋረጠ መምጣቱ፣ ስፖርተኞች ከአገራዊ ውድድሮች ይልቅ የተለያዩ የገንዘብና ሌሎች ጥቅማ ጥቅሞችን ለሚያስገኝላቸው የግል ውድድር ትኩረት የሚሰጡበትን አስመልክቶ ለቀረበው ጥያቄም በተመሳሳይ በጠቅላይ ሚኒስትሩ ሽልማቱና ጥቅማ ጥቅሙ እንደሚቀጥል ይሁንታ ማግኘቱ ተገልጿል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

‹‹በየቦታው ምርት እየገዙ የሚያከማቹ ከበርቴ ገበሬዎች ተፈጥረዋል››

አቶ ኡስማን ስሩር፣ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በምክትል ርዕሰ መስተዳድር...

ኢትዮጵያዊ ማን ነው/ናት? ለምክክሩስ መግባባት አለን?

በደምስ ጫንያለው (ዶ/ር) የጽሑፉ መነሻ ዛሬ በአገራችን ውስጥ በተለያዩ አካባቢዎች ግጭቶችና...

ዴሞክራሲ ጫካ ውስጥ አይደገስም

በገነት ዓለሙ የዛሬ ሳምንት ባነሳሁት የኢሰመኮ ሪፖርት መነሻነትና በዚያም ምክንያት...

ኢትዮጵያ በምግብ ራሷን የምትችለው መቼ ነው?

መድረኩ ጠንከር ያሉ የፖሊሲ ጉዳዮች የተነሱበት ነበር፡፡ ስለረሃብ፣ ስለምግብ፣...