Tuesday, October 3, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ኪንና ባህልየማኅበረሰብ ሚዲያን ለበጎ ያዋሉ ይሸለማሉ

የማኅበረሰብ ሚዲያን ለበጎ ያዋሉ ይሸለማሉ

ቀን:

በማኅበረሰብ ድረ ገጽ በዋነኛነት በፌስቡክ የሚለቋቸውን መልዕክቶች ማኅበረሰቡን ለሚጠቅም ዓላማ ያዋሉ ሰዎችን ሰኔ 20 ቀን 2009 ዓ.ም. እንደሚሸልም ሳልቃን ፊልም ፕሮዳክሽን አስታውቋል፡፡ ሽልማቱ በዘጠኝ ዘርፎች ሲሆን፣ አዘጋጆቹ እስከ አሁን ወደ 60 የሚጠጉ የማኅበረሰብ ድረ ገጽ ተጠቃሚዎችን ለውድድር አቅርበዋል፡፡ የውድድሩ የመጨረሻ ዙር ዕጩዎች እስከሚታወቁ ሕዝቡም መጠቆም ይችላል፡፡ እስካሁን ከታጩት መካከል በጤና ዘርፍ ዶ/ር ሆለንያት ኤፍሬምና ሔሎ ዶክተር፣ ወቅታዊና ታማኝ መረጃዎችን በማድረስ ጌጡ ተመስገንና ተሻገር ጣሰው፣ በበጎ አድራጎት ዘርፍ ዋልተንጉሥ ዘሸገርና አቤል የወይኗ ልጅ፣ በታሪክ ዘርፍ ያሬድ ሹመቴንና ኢዮብ ዘለቀ፣ በስፖርት ዘርፍ ስኮር ኢትዮጵያና ብርሃን ስፖርት፣ በግጥም ዘርፍ ረድኤት ተረፈና በላይ በቀለ ወያ፣ በአስቂኝ ዘርፍ አዱኛ ከቤና ማሂ፣ በአነቃቂና ማኅበራዊ ጉዳዮች ዘርፍ አቤል ብርሃኑና ብሩክ የሺጥላ፣ በወግ ዘርፍ ዲያቆን ዳንኤል ክብረትና አሌክስ አብርሃም፣ በቲዩብ ዘርፍ ድሬ ቲዩብና የኛ ቲዮብ ይገኙበታል፡፡  በማኅበረሰብ ድረ ገጽ ስማቸው የተጠቀሱት ግለሰቦችና ተቋምን የወከሉትም ተወዳዳሪዎች በጋዜጠኝነትና ሥነ ጽሑፍ ምሩቃን ተገምግመው ያሸነፉት ለሽልማት እንደሚበቁ አዘጋጆቹ ገልጸዋል፡፡

 

*****

‹‹ኃሠሣ››

በሕይወት ተፈራ የተጻፈው ‹‹ማይን ቱ ዊን›› ወደ አማርኛ ‹‹ኃሠሣ›› በሚል ርዕስ ተተርጉሟል፡፡ ተርጓሚዋ ሕይወት ታደሰ ስትሆን፣ 180 ገጾች ያሉት መጽሐፉ ከግንቦት 28 ቀን 2009 ዓ.ም. ጀምሮ በ120 ብር ይሸጣል፡፡

*****

‹‹እንደ ሐባሻ››

በአብርሃም ዘነበ የተጻፈውና በመሐመድ ዳውድ የተዘጋጀው ‹‹እንደ ሐባሻ›› የተሰኘ ፊልም ግንቦት 28 ቀን 2009 ዓ.ም. ከ10፡30 ጀምሮ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር እንደሚመረቅ ግሎባል ፒክቸርስ ገልጿል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ተመድንና ዓለም አቀፋዊ ሕግን ከእነ አሜሪካ አድራጊ ፈጣሪነት እናድን!

በገነት ዓለሙ በእኔ የተማሪነት፣ የመጀመርያ ደረጃ ተማሪነት ጊዜ፣ የመዝሙር ትምህርት...

የሰላም ዕጦትና የኢኮኖሚው መንገራገጭ አንድምታ

በንጉሥ ወዳጅነው ፍራንክ ቲስትልዌይት የተባሉ አሜሪካዊ ጸሐፊ ‹‹The Great Experiment...

ድህነት የሀብት ዕጦት ሳይሆን ያለውን በአግባቡ ለመጠቀም አለመቻል ነው

በአንድነት ኃይሉ ድህነት ላይ አልተግባባንም፡፡ ብንግባባ ኖሮ ትናንትም ምክንያት ዛሬም...