ጥሬ ዕቃዎች
ግማሽ ኪሎ ግራም በስሎ የቀዘቀዘ ሩዝ
300 ግራም ቱና (4 ትንንሽ የታሸገ ቆርቆሮ)
1 ቆርቆሮ በቆሎ
2 ፍሬ ካሮት
4 እንቁላል
7 የሾርባ ማንኪያ የወይራ ዘይት
4 የሾርባ ማንኪያ አቼቶ
ጨውና ቁንዶ በርበሬ
አዘገጃጀት
- ካሮቱንና እንቁላሉን መቀቀልና መላጥ፣
- የተቀቀለውን ካሮት በደቃቁ መክተፍ፣
- እንቁላሉን ልጦ በደቃቁ መክተፍ፣
- በጐድጓዳ ሰሀን ተቀቅሎ የቀዘቀዘውን ሩዝ መጨመር፣
- የተከተፈውን ካሮትና እንቁላል ከሩዙ ጋር መደበላለቅ፣
- ቱናውን ከፍቶ ዘይቱን አጥልሎ ሩዙ ውስጥ መጨመር፣
- የቆርቆሮውን በቆሎ ውኃውን አጥልሎ ሩዙ ውስጥ መጨመር፣
- የወይራ ዘይት፣ አቼቶ፣ ጨውና ቁንዶ በርበሬ ጨምሮ በደንብ መደበላለቅና ለገበታ ማቅረብ
- ጆርዳና ኩሽና ‹‹የምግብ አዘገጃጀት›› (2007)