Saturday, April 20, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ዝንቅአብረን ይግባኝ እንበል

አብረን ይግባኝ እንበል

ቀን:

አብረን ይግባኝ እንበል

ገባኝ፣

እሱ ነው ብለኸኝ የለ?

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

ተወዳል ወጣች ፀሐይ የፈለቀ፣

ጊዜን እንዳሻው የሚያሾር

ተኔፍሊምም የረቀቀ፣

ዘመኔ ምኩን ቢመስለው

ሊያዳቅልልኝ የፀደቀ፣

ባይኑ ሰማዬ ቢጨልም

ኩራዝ ሊሆነኝ የበረቀ?

ገባኝ!

መጣ’ልከኝ አይደል ሊታደገኝ፣

የኋሊት-ኋሊት-ኋሊት በ’ሮ፣

ያያቱን-አያቱን-…አያት ሊያድን

እልፍ አድማሳትን አሳብሮ?

ነገርህ ገባኝ ልጄ! . . . 

ግና . . .

ተ’ኔ ዓለም ሸክላ ልቡ ታልተሠራ፣

በ’ኔ ሰማይ ፀሐይ ሕሊናው ታልበራ፣

ምኑን መጣሁ አለ፣

የዘመንን ኬላ ምኑን ተሻገርኩት?

ምኑን አሠለጠንኩ ምኑን አፀደቅሁት?

ዕውቀቱ ብቃቱስ ምኑን ተኔ ሰፋ?

ሰዓቴን ጠምዝዞ ሰዓቱን ታጠፋ!

እንዲያው ለመሆኑ፣

ቀኔን ሊያስጥለኝ የተባለ

በማን ቀን ሊያኖረኝ ከጀለ?

ቀንህን ልሙላልህስ ያለ

የቀን ጎደሎስ የታለ?

ቆየኝማ፣

ተገናኝተን ቢሆንስ እመንገድ

ለየቅል፣

ባልቦ ዘመድ፣

በጊዜ ክበብ ላይ ስንነጉድ?

‹‹ዘለቃ-መጥ››፣ ‹‹ኋላ-መጥ›› እምትል

ተጠየቅ ነፍሴን አታቃል፤

ዋልታ ለዋልታ ለመደልደል

ምን አስመዘዘህ ዕጣ?

አብረን ይግባኝ እንበል

መጣፍ አጣቅስ እማኝ ላምጣ!’

ስንቅነህ እሸቱ ‹‹40 ጠብታዎች›› (1996)

***

በላሞች የተወረረ መንደር

እሑድ ጠዋት በአብዛኛው የዓለም ክፍል የሚገኙ በክርስትና እምነት ተከታዮች ወደ ቤተ እምነታቸው በማቅናት የእምነታቸውን ሥርዓት የሚፈጽሙበት ነው፡፡ በመሆኑም በዕለቱ ጠዋት ላይ ሰዎች በእግርም ሆነ በመኪና በአቅራቢያቸው ወደሚገኝ ቤተ እምነት ያቀናሉ፡፡ በእንግሊዝ ቼሻየር በምትገኘው ትንሿ የቦሊንግቶን ከተማ ነዋሪ የሆኑት የ61 ዓመቷ አዛውንትም ማልደው የተነሱት ወደ ቤተ ክርስቲያን ለማቅናት ነበር፡፡ ሆኖም ከቤታቸው እንዳሉ መጋረጃ ሲገልጡ ያስተዋሉት ነገር እንዳበሳጫቸውና እንዳናደዳቸው ይናገራሉ፡፡

ሜትሮ ዩኬ እንደዘገበው፣ አዛውንቷ መጋረጃ ሲገልጡ ያስተዋሉት በመንደራቸው የሚኖሩ ሰዎች ወደ ቤተ ክርስቲያን ሲያቀኑ ሳይሆን፣ አካባቢያቸው በሙሉ በላሞች ተወሮ ነው፡፡

የአካባቢው ፖሊስ እንደገለጸው፣ መንደሩ በ40 ላሞች ተወሮ የነበረ ቢሆንም፣ በሰዎች ላይ ጉዳት ሳያደርሱ፣ ከመንደሩ ራቅ ብሎ ወደሚገኘው በረታቸው ተመልሰዋል፡፡ በእንግሊዝ እ.ኤ.አ. ከ2000 እስከ 2015 ባሉት ጊዜያት 74 ሰዎች በላሞች ተገድለዋል፡፡ ላሞችም አደገኛ ከሆኑ የቤት እንስሳት የሚመደቡ ናቸው፡፡

* * *

አስተማሪን የመጨበጥ ፖሊሲ በትምህርት ቤት

ተማሪዎች ክፍል በገቡ ቁጥር አስተማሪያቸውን የሚጨብጡበት አግባብ የተለመደ ባይሆንም የቱንብሪጅ ዌልስ ትምህርት ቤት ግን ይህንኑ ፖሊሲ ተግባራዊ አድርጓል፡፡

እንደ ሚረር ዘገባ፣ ትምህርት ቤቱ ፖሊሲውን ከሳምንት በፊት ተግባራዊ ያደረገው፣ ተማሪዎች ለመምህራን ክብር እንዲያሳዩ ታስቦ ቢሆንም፣ ከወላጆች ግን ተቃውሞ ገጥሞታል፡፡

የመከባበሩ ጉዳይ ሁሉንም የሚያስማማ ቢሆንም፣ በተለይ ጉንፋን በሚበዛባቸው ወቅቶች በግቢው የሚገኙ 150 ተማሪዎች በአንዴ ሊጠቁ እንደሚችሉም እያነሱ ነው፡፡ ከዚህ ባለፈ እጅ በመጨባበጥ ጊዜ ሊተላለፉ የሚችሉ ባክቴሪያዎችና ኢንፌክሽኖች መኖራቸው ሥጋት ፈጥሯል፡፡  

ለዚህም አንዳንድ መምህራን እጃቸውን የሚቀቡት ፀረ ባክቴሪያ ይዘው መምጣት መጀመራቸው ተዘግቧል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ሰላማዊ የፖለቲካ ትግልና ፈተናው

የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) የፖለቲካ ኦፊሰር የአቶ በቴ ኡርጌሳን...

አበጀህ ማንዴላ! አበጀሽ ደቡብ አፍሪካ!

በአየለ ት. የፍልስጤም ጉዳይ የዓለም አቀፍ ፖለቲካንም ሆነ የተባበሩት መንግሥታትን...

የውጭ ባለሀብቶች ለኢትዮጵያውያን ብቻ በተፈቀዱ የንግድ ዘርፎች እንዲገቡ የመወሰኑ ፋይዳና ሥጋቶች

ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አዓመድ (ዶ/ር) የውጭ ኩባንያዎች በጅምላና ችርቻሮ...