Tuesday, December 5, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ስፖርትየመሠረት ደፋር የቤጂንግ የነሐስ ሜዳሊያ ወደ ብር ተቀየረ

የመሠረት ደፋር የቤጂንግ የነሐስ ሜዳሊያ ወደ ብር ተቀየረ

ቀን:

ከዘጠኝ ዓመት በፊት በቤጂንግ ኦሊምፒክ በታዋቂው የወፍ ጎጆ ስታዲየም ከተስተናገዱ ውድድሮች መካከል የ5,000 ሜትር የሴቶች የሩጫ ውድድር ይጠቀሳል፡፡ በወቅቱ ለአሸናፊነት እልህ አስጨራሽ ትንቅንቅ ያደረጉት ጥሩነሽ ዲባባ፣ መሠረት ደፋርና ቱርካዊቷ ኤልቫን ዓብይ ለገሰ ነበሩ፡፡ ለአሸናፊነት ትልቅ ግምት ከተሰጣቸው ኢትዮጵያውያኑ እንስቶች መካከል ሳትታሰብ የገባችው ቱርካዊቷ ዓብይ ለገሰ፣ መሠረት ደፋርን አስከትላ የብር ሜዳሊያ ባለቤት መሆኗም አይዘነጋም፡፡ ይሁንና አትሌቷ በሁለተኛነት ያስመዘገበችው የብር ሜዳሊያ እንደማይገባት የዓለም አቀፉ ኦሊምፒክ ኮሚቴ (አይኦሲ) ከሰሞኑ ይፋ አድርጓል፡፡

አይኦሲ ይፋ ባደረገው መረጃ መሠረት ቱርካዊቷ ዓብይ ለገሰ፣ በወቅቱ ሜዳሊያውን ለማግኘት ያስቻላት ብቃት አበረታች ቅመሞችን ተጠቅማ መሆኑን አረጋግጦ ውጤቱን ሰርዞታል፡፡ በምትኩም ሦስተኛ የወጣች መሠረት ደፋር ሁለተኛነቱ ይገባታል በማለት የመሠረት የኦሊምፒክ ሽልማት ወደ ብር ሜዳሊያ እንዲቀየር መወሰኑንና አትሌቷ ሽልማቷን በአዲስ አበባ በልዩ ሥነ ሥርዓት እንዲሰጣት መወሰኑን አስታውቋል፡፡ የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴም ለዚሁ ሥነ ሥርዓት ዝግጅት እያደረገ መሆኑን በላከው መግለጫ ይፋ አድርጓል፡፡

በዚሁ የዘመኑ አትሌቲክስ ላይ በከፍተኛ ሁኔታ ጥላውን እያጠላ በሚገኘው አበረታች ቅመሞች (ዶፒንግ) ዙሪያና በርካታ አትሌቶች በኦሊምፒክና በዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ያገኟቸውን ሽልማቶች እያሳጣቸው መሆኑን ሪፖርተር መዘገቡ አይዘነጋም፡፡ በዚሁ መሠረት የዓለም አቀፍ አትሌቲክስ ፌዴሬሽኖች ማኅበር (አይኤኤኤፍ) በመጋቢት 20 ቀን 2009 ዓ.ም. ከዙሪክ በለቀቀው ዜና በ5,000 እና በ10,000 ሜትር በቤጂንግ ኦሊምፒክ ሁለት የብር ሜዳሊያዎችን ያገኘችው ዓብይ ለገሰ የተከለከለ ቅመም መውሰዷ በመረጋገጡ ውጤቷን ሰርዟል፡፡ በትውልድ ኢትዮጵያዊቷ በዜግነት ቱርካዊቷ ዓብይ ለገሰ ከኢሊምፒክ በተጨማሪ በ1999 ዓ.ም. በኦሳካ በተካሄደ የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና በ10,000 ሜትር ባለድሏን ጥሩነሽ ዲባባን ተከትላ ሁለተኛ የወጣችበት ውጤቷም በተመሳሳይ መሰረዙ ሪፖርቱ መዘገቡ ይታወሳል፡፡

አትሌቷ በተደረገላት ምርመራ የተከለከለውን ስቴሪዮ ስታኖዞል የተሰኘ ቅመም በመውሰዷ ዳግም በተደረገው ፍተሻ በመረጋገጡ ከ1999 ዓ.ም. እስከ 2001 (እ.ኤ.አ. 2007 እስከ 2009) ያስመዘገበቻቸው ውጤቶች በሙሉ ውድቅ ተደርገዋል፡፡

በዚህ መሠረት ኢትዮጵያ በቤጂንግ ኦሊምፒክ ያስመዘገችው አራት የወርቅ፣ አንድ የብርና ሁለት የነሐስ ሜዳሊያዎች የመሠረት ነሐስ ወደ ብር በማደጉ ደረጃዋም በአንድ ደረጃ ይሻሻላል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

በዓለም አቀፍ ደረጃ ሕይወታቸውን በኤድስ ምክንያት ላጡ ሰዎች 35ኛ ዓመት መታሰቢያ

ያለፍንበትን እያስታወስን በቁርጠኝነት ወደፊት እንጓዝ - በኧርቪን ጄ ማሲንጋ (አምባሳደር) በየዓመቱ...

እዚያ ድሮን… እዚህ ድሮን…

በዳንኤል ካሳሁን (ዶ/ር) ተዓምራዊው የማዕበል ቅልበሳ “በሕግ ማስከበር” ዘመቻው “በቃ የተበተነ...

ለፈርጀ ብዙ የማንነት ንቃተ ህሊናችን የሚጠቅሙ ጥቂት ፍሬ ነገሮች

በበቀለ ሹሜ ከጨቅላነት ጅምሮ ያለ የእያንዳንዳችን የሰብዕና አገነባብ ከቤተሰብ እስከ...