አስፈላጊ ጥሬ ዕቃዎች
- 75 ግራም አይብ
- 1/3 ኩባያ ካሮት፣ የተከተፈ
- ¼ የሻይ ማንኪያ ጨው
- 1 የሾርባ ማንኪያ ሽንኩርት የተከተፈ
- ትንሽ ሚጥሚጣ
- የፐርሰሜሎ ቅጠል
አዘገጃጀት
- አይብና ካሮት ማደባለቅ፡፡
- ጨው፣ ሚጥሚጣና ሽንኩርት ድብልቁ ውስጥ መጨመር፡፡
- በተራ ቁጥር 1 እና 2 የተዘጋጀውን ድብልቅ በደንብ አዋሕዶ የካሮት ቅርጽ እንዲይዝ አድርጎ ማድቦልቦል፡፡
- ቅርጹን እንዲጠብቅ በረዶ ቤት ውስጥ ማቀዝቀዝ፡፡
- የፐርሰሜሎውን ቅጠል ከጫፉ በኩል በመሰካት ካሮት አስመስሎ ማቅረብ፡፡
ስምንት ሰው ይመግባል፡፡
- ጽጌ ዑቁባሚካኤል ‹‹የእናት ጓዳ›› (1984)