Saturday, December 3, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - Advertisement -
  - Advertisement -
  ዜናመንግሥት የአውሮፓ ፓርላማ በዶ/ር መረራ ጉዲና የፍርድ ሒደት ላይ ያወጣውን መግለጫ ተቃወመ

  መንግሥት የአውሮፓ ፓርላማ በዶ/ር መረራ ጉዲና የፍርድ ሒደት ላይ ያወጣውን መግለጫ ተቃወመ

  ቀን:

  • 14 የአሜሪካ ሴናተሮች የተቃዋሚዎች መብት እንዲከበር ጠይቀዋል

   

  ሐሙስ ግንቦት 10 ቀን 2009 ዓ.ም. የተሰበሰበው የአውሮፓ ፓርላማ አባላት፣ የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግሬስ (ኦፌኮ) ሊቀመንበር ዶ/ር መረራ ጉዲና በአስቸኳይ የዋስትና መብታቸው ተከብሮ  እንዲለቀቁና የተመሠረቱባቸው ክሶች በሙሉ ውድቅ እንዲደረጉ ጠየቁ፡፡ መንግሥት ደግሞ ጉዳያቸው በፍርድ ቤት እየታየ ባሉት የዶ/ር መረራ ጉዲና የፍርድ ሒደት ላይ ፓርላማው ያወጣው መግለጫ ሚዛናዊነት የጎደለው ብቻ ሳይሆን፣ አግባብነት የሌለው ነው ብሏል፡፡

  ዶ/ር መረራ በመንግሥት የታሰሩት እ.ኤ.ኤ. ኖቬምበር 9 ቀን 2016 ከሌሎች የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮች ጋር በአውሮፓ ፓርላማ ከተሳተፉ በኋላ ወደ ኢትዮጵያ ሲመለሱ መሆኑን ያስታወሰው የፓርላማው መግለጫ፣ ከዚያ በኋላ ዶ/ር መረራ ‹‹መንግሥት ላይ ጫና በመፍጠር›› እና ‹‹ብጥብጥ በመፍጠር ኅብረተሰቡን ሥጋት ላይ በመጣል›› ወንጀሎች ክስ እንደተመሠረተባቸው ይገልጻል፡፡

  የፓርላማው መግለጫ እ.ኤ.አ. በ2015 በመቶዎች የሚቆጠሩ ተቃውሞ አድራጊዎች የሞቱበት፣ መንግሥት ላይ ተቃውሞ እንዳላቸው የሚታመኑ የኦሮሞ ማኅበረሰብና የሌሎች ብሔሮች አባላት ላይ የተፈጸመው የሰብዓዊ መብት ጥሰት በተዓማኒ፣ ግልጽና ገለልተኛ አዳሪ እንዲገመገምም ይጠይቃል፡፡ የፓርላማው አባላት የኢትዮጵያ መንግሥት የፀረ ሽብርተኝነት ሕጉን በመጠቀም ተቀባይነት ያላቸውና ሰላማዊ ተቃዋሚዎችን ከመጨቆን እንዲቆጠብ፣ ሐሳብን በነፃነት የመግለጽና የመደራጀት መብት ላይ የሚጥለውን ገደብ እንዲያነሳ አሳስበዋል፡፡

  የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ግንቦት 10 ቀን 2009 ዓ.ም. ለሪፖርተር በላከው መግለጫ፣ ኢትዮጵያ ከኅብረቱ ጋር ያላትን ግንኙነት እየተጠናከረ ባለበት ወቅት  ፓርላማው ግንቦት 10 ቀን 2009 ዓ.ም. ያወጣው መግለጫ የኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ ካልተገነዘቡ አባላቱ ዕይታ በመነሳት የተሰጠ እንደሆነ ገልጿል፡፡ ‹‹የፓርላማው መግለጫ ሕገ መንግሥታዊ ሥርዓትን ለማሳነስ ከመሞከር የዘለለ ፋይዳ የለውም፤›› ሲልም ያትታል፡፡

  መግለጫው በመጨረሻም፣ ‹‹ሰላምና መረጋጋት እንዲሰፍን፣ እንዲሁም ሕዝቡ የልማቱ ተጠቃሚ እንዲሆንና የሕዝቡን ጥያቄ ለመመለስ በመንግሥት በኩል ጥረት እየተደረገ ባለበት ወቅት መግለጫው መውጣቱ፣ በኢትዮጵያና በአውሮፓ ኅብረት መካከል ላለው የትብብር መንፈስ ገንቢ አይደለም፡፡ በሕግ ጥላ ሥር ያሉ ወገኖችን በተመለከተ የተሰጠው አስተያየትም የኢትዮጵያን የፍትሕ አካሄድና ሥርዓት ያላገናዘበ ነው፡፡ በመሆኑም የኅብረቱ ፓርላማ መግለጫ በአገራችን የዕድገት ጎዳና ላይ ትርጉም ያለው ተፅዕኖ የሚያሳድር ባይሆንም፣ ኢትዮጵያ ከአውሮፓ ኅብረት ጋር እያሳየች ላለችው ስትራቴጂያዊ ግንኙነት የሚመጥን በመከባበር፣ በጋራ ጥቅም፣ በእኩልነት ላይ የተመሠረተና የአገራችንን ወቅታዊ ሁኔታ ያገናዘበ አመለካከት እንዲሰፍን በተጠናከረ መልኩ ከኅብረቱ ጋር ምክክር ትቀጥላለች፤›› ሲል አብራርቷል፡፡

  ይህ በዚህ እንዳለ 14 የአሜሪካ ሴናተሮች በጋራ ባወጡት መግለጫ፣ የኢትዮጵያ መንግሥት የተቃዋሚዎችን መብት እንዲያከብርና ማዋከቡን እንዲያቆም ጠይቀዋል፡፡ በሴናተሮች ቤን ካርዲንና ማርኮ ሩቢዮ የሚመራው ቡድን የፀጥታ ኃይሎች ከዓመት በፊት በነበረው ከፍተኛ ፀረመንግሥት የተቃውሞ እንቅስቃሴ የወሰዱት ዕርምጃ ተመጣጣኝ ስለመሆኑ ወይም አለመሆኑ በተዓማኒ አካል እንዲጣራ ጠይቀዋል፡፡ ሴናተሮቹ በመግለጫቸው፣ ‹‹በፀረ ሽብርተኝነት ላይ ከኢትዮጵያ ጋር በአጋርነት እንሠራለን ማለት የገዛ ሕዝቦቿን መብት ስትጥስ ዝም እንላለን ማለት አይደለም፤›› ብለዋል፡፡ መንግሥት የፖለቲካ ምኅዳሩን እንዲያሰፋም በአፅንኦት አሳስበዋል፡፡ 

  spot_img
  - Advertisement -

  ይመዝገቡ

  spot_img

  ተዛማጅ ጽሑፎች
  ተዛማጅ

  [በተቋሙ ሠራተኞች የተወከሉ አንድ ባልደረባ ሚኒስትሩን ለማነጋገር ቀጠሮ ይዘው ወደ ቢሯቸው ገቡ]

  ጤና ይስጥልኝ ክቡር ሚኒስትር? ሰላም ሰላም ... ተቀመጥ! አመሠግናለሁ ክቡር ሚኒስትር!...

  የጉራጌ ዞን ጥያቄና የክላስተር አደረጃጀት የገጠመው ተቃውሞ

  መንግሥት የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል አካል የነበሩ ዞኖችንና...

  አዋሽ ባንክ ካፒታሉን ወደ 55 ቢሊዮን ብር ለማሳደግ ያስገደደው ምክንያት ምንድን ነው?

  ባለፈው ቅዳሜ ጠቅላላ ጉባዔውን ያካሄደው አዋሽ ባንክ የ43 ቢሊዮን...

  አቢሲኒያ ባንክ ካለፈው ዓመት የ127 በመቶ ብልጫ ያለው ትርፍ በማግኘት አዲስ ታሪክ አስመዘገበ

  አቢሲኒያ ባንክ ከቀደሚ የሒሳብ ዓመት የ127 በመቶ ብልጫ ያለው...