Tuesday, February 27, 2024
- ማስታወቂያ -
- ማስታወቂያ -

ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ለመሰብሰብ ያቀደው ገቢ በ20 ቢሊዮን ብር ጉድለት አሳየ

ተዛማጅ ፅሁፎች

የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ባለፉት አሥር ወራት ውስጥ ለመሰብሰብ ያቀደው ገቢ በ20.49 ቢሊዮን ብር ጉድለት አሳየ፡፡

ባለሥልጣኑ ለዚህ ዓመት እንዲሰበሰብ በሕግ የሚጠበቅበት 173.19 ቢሊዮን ብር ነው፡፡ ከዚህ ውስጥ 140 ቢሊዮን ብር በአሥር ወራት ውስጥ ለመሰብሰብ ባለሥልጣኑ አቅዶ እንደነበር፣ ዋና ዳይሬክተሩ አቶ ከበደ ጫኔ የሥራ አፈጻጸም ሪፖርታቸውን ማክሰኞ ግንቦት 15 ቀን 2009 ዓ.ም. ለፓርላማ ሲያቀርቡ አስረድተዋል፡፡

በአሥር ወራት ውስጥ መሰብሰብ የተቻለው 113.56 ቢሊዮን ብር ነው፡፡ ይህም ከዕቅዱ 20.49 ቢሊዮን ብር ጉድለት አሳይቷል፡፡

ከተሰበሰበው ገቢ ውስጥ የአገር ውስጥ ታክስ ገቢ 57.8 በመቶ፣ የወጪ ንግድ ቀረጥና ታክስ ገቢ 42.1 በመቶ፣ የሎተሪ ሽያጭ የተጣራ ገቢ 0.10 በመቶ ድርሻ አበርክተዋል፡፡

የገቢ አሰባሰቡ አስተማማኝነት ወዳለው የአገር ውስጥ ታክስ እየተሸጋገረ መሆኑን አቶ ከበደ ቢገልጹም፣ ከዓለም አቀፍ የወጪ ንግድ ቀረጥ ድርሻ የተገኘው ገቢ አሁንም ከፍተኛ መሆኑ አሳሳቢ እንደሆነ ጠቁመዋል፡፡ 

spot_img
- Advertisement -spot_img

የ ጋዜጠኛው ሌሎች ፅሁፎች

- ማስታወቂያ -

በብዛት ከተነበቡ ፅሁፎች