አስፈላጊ ጥሬ ዕቃዎች
- 2 ኩባያ ሥጋ፣ ተቀቅሎ የተከተፈ
- 1 ½ የሾርባ ማንኪያ የፋርኖ ዱቄት
- 1 ኩባያ አተር፣ የተቀቀለ
- 1 ኩባያ ካሮት፣ ተቀቅሎ የተከተፈ
- 1 ኩባያ እንጉዳይ
- 2 ሽንኩርት፣ የተከተፈ
- 2 የሾርባ ማንኪያ ቅቤ
- 1 ¼ ኩባያ ወተት ወይም መረቅ
- ½ ረሲፒ ፔስትሪ ጨው ቁንዶ በርበሬ
አዘገጃጀት
- ሽንኩርቱን አቁላልቶ ሥጋውን ጨምሮ ማብሰል
- የተጣደውን ሽንኩርት ሥጋ አውጥቶ ከዱቄት፣ ከወተት ወይም ከመረቅ ጋር በደንብ ማደባለቅ
- አተር፣ ካሮትና እንጉዳዩን ጨምሮ ማደባለቅ
- የመጋገሪያ ዕቃውን ዘይት ወይም ቅቤ መቀባት
- በተራ ቁጥር 3 እና 4 የተዘጋጀውን ሥጋና አትክልት መጋገሪያ ዕቃው ላይ አድርጎ ጨውና ቁንዶ በርበሬ ላዩ ላይ መነስነስ
- ፔስትሪውን ላዩ ላይ ሸፍኖ ጠርዙን በደንብ መግጠም
- ሙቀቱ 425 ድግሪ ፋራንሃይት በሆነ ምድጃ ውስጥ ለሰላሳ ደቂቃ ማብሰል
ለስድስት ሰው ይሆናል፡፡
- ጽጌ ዑቁባሚካኤል ‹‹የእናት ጓዳ›› (1984)