Thursday, May 23, 2024
- ማስታወቂያ -
- ማስታወቂያ -

ለገቢ ንግድ የሚፈቀደውን የውጭ ምንዛሪ ከተወሰኑ አስመጪዎች እጅ ለማላቀቅ 215 የክልል አስመጪዎች ተመለመሉ

spot_img

ተዛማጅ ፅሁፎች

መንግሥት ለገቢ ንግድ በየዓመቱ የሚፈቅደውን የውጭ ምንዛሪ ከተወሰኑ የአዲስ አበባ አስመጪዎች እጅ ውስጥ ለማስለቀቅ፣ 215 የክልል አስመጪዎችን መመልመሉ ተሰማ፡፡

የሪፖርተር ምንጮች እንደገለጹት አስመጪዎቹ የተመለመሉት ከመቐለ፣ ከባህር ዳር፣ ከጅማና ከሐዋሳ ከተሞች ነው፡፡

በአሁኑ ወቅት የአስመጪነት ንግድ በተወሰኑ የአዲስ አበባ ነጋዴዎች ውስጥ በመውደቁና ይህም የጎንዮሽ የዋጋ አሻጥር መፍጠር እንዲችሉ እንዳደረጋቸው፣ የአገሪቱን ውስን የውጭ ምንዛሪም በብቸኝነት እንዲቀራመቱ እንዳስቻላቸው የንግድ ሚኒስቴር የሪፖርተር ምንጮች ገልጸዋል፡፡

ይህንን ችግር ለመቅረፍና አዲስ አበባ ላይ የተወሰነውን የአስመጪነት ንግድ ለመበተን ሲባል፣ ከተመረጡ የክልል ከተሞች ባለሀብቶችን በመመልመልና በማሠልጠን መንግሥት በ2010 ዓ.ም. ወደ ትግበራ እንደሚገባ ምንጮች ተናግረዋል፡፡

ባለሀብቶችን ለመምረጥ የንግድ ሚኒስቴር የተለያዩ መሥፈርቶችን የተጠቀመ ሲሆን፣ ከእነዚህም መካከል ዋነኞቹ በሕገወጥ ንግድ ያልተሳተፈና ካፒታሉ ተዓማኒነት ያለው የሚሉ ናቸው፡፡

ለሙከራ ትግበራው ከተመለመሉት 215 ባለሀብቶች ውስጥ የተመረጡት ከተሞች እያንዳንዳቸው 15 ባለሀብቶችን እንዲወክሉ መደረጉንም ምንጮች ገልጸዋል፡፡

በአሁኑ ወቅት ከብሔራዊ ባንክ ጋር ንግግር እየተደረገ ሲሆን፣ ብሔራዊ ባንክ በክልሎች ቅርንጫፍ የሌለው በመሆኑ ውክልና ለኢትዮጵያ ንግድ ባንክ መስጠት በሚቻልበት ወይም ሌላ አማራጮችን ለማየት ንግግር እየተደረገ መሆኑንም ምንጮች አክለዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -spot_img

የ ጋዜጠኛው ሌሎች ፅሁፎች

- ማስታወቂያ -

በብዛት ከተነበቡ ፅሁፎች