Friday, May 24, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -

ስፖርትብሔራዊ ፌዴሬሽኖች በፖሊሲ አፈጻጸም ችግር ውስጥ እየገቡ መሆኑ ታወቀ

ብሔራዊ ፌዴሬሽኖች በፖሊሲ አፈጻጸም ችግር ውስጥ እየገቡ መሆኑ ታወቀ

ቀን:

  • አገር አቀፉ የስፖርት ፖሊሲ ክለሳ ሳይደረግለት ሁለት አሠርታት አስቆጥሯል

 የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽንና ሌሎችም ብሔራዊ ፌዴሬሽኖች በፖሊሲ አፈጻጸም ክፍተት ለውድቀት እየተጋለጡ መሆኑ ተገለጸ፡፡ ለዚህ በዋናነት ምክንያት ተደርጎ የሚጠቀሰው ደግሞ በ1990ዎቹ መጀመርያ በአገር አቀፍ ደረጃ ሥራ ላይ እንዲውል የተደረገው የስፖርት ፖሊሲ እስካሁን ድረስ ምንም ዓይነት የማሻሻያ ክለሳ ሳይደረግለት ሁለት አሠርታትን ማስቆጠሩ እንደሆነ እየተጠቀሰ ይገኛል፡፡

በዚህም የተነሳ እግር ኳስ ፌዴሬሽንም ሆነ ሌሎች ፌዴሬሽኖች ‹‹ፖሊሲ›› የሚለውን ከስሙ ባለፈ ለስፖርቱ የሚሰጠው ፋይዳ የዘነጉት ከመሆኑም ባሻገር ተቋማቱ ከዘመናዊ ይልቅ ዘልማዳዊ የአሠራር ሥርዓትን እንዲከተሉ እያደረገ መሆኑ በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የሚገኙ የየዘርፉ ሙያተኞች ይናገራሉ፡፡

ሙያተኞቹ ይህንን ለማለት በዋናነት ያነሳሳቸው መንግሥት ከሰሞኑ በሐዋሳ ለአትሌቶች ባከናወነው የዕውቅናና የሽልማት ሥነ ሥርዓት ላይ የታደሙት ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ፣ በተለይ የስፖርት ፌዴሬሽኖች በስፖርቱ ያለፉ፣ ዕውቀቱና አቅሙ ያላቸው ሊመሩት እንደሚገባ የተናገሩትን መነሻ በማድረግ ነው፡፡

- Advertisement -

ከአገር አቀፉ የስፖርት ፖሊሲ ጀምሮ ለአገሪቱ ስፖርት ትልቅ የሥልጣን አካል ተደርጎ የሚወሰደው ስሙ ብቻ ያለው ብሔራዊ የስፖርት ምክር ቤት ኃላፊነት ድርሻ በማይታወቅበት፣ እንዲሁም ከጊዜው ጋር መራመድ የሚችል ደንብና መመርያዎች ከአገር አቀፍ ፖሊሲው ጋር ተጣጥመው እንዲሄዱ ባልተደረገበት በዚህ ወቅት መሆኑ ተግባራዊነቱ ላይ ጥርጣሬ እንዲያድርባቸው ያደረገ ስለመሆኑ ጭምር ያስረዳሉ፡፡

አስተያየት ሰጪዎቹ ለሚያቀርቡት ቅሬታና አስተያየት መነሻ የሚያደርጉት ደግሞ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽንን ነው፡፡ ተቋሙ የፋይናንስ ገቢና ወጪን በሚመለከት ካልሆነ የብሔራዊ ፌዴሬሽኑን ዝርዝር የሥራ ዕቅድ የሚያመለክት የፖሊሲ ማዕቀፍ የለውም፡፡ ለምሳሌ ችግሮች ቢፈጠሩ የችግር አፈታት ፖሊሲ፣ የተጨዋዎች የዝውውር ፖሊሲ፣ የሜዳ አጠቃቀም ፖሊሲ የብሔራዊ ቡድን ተጫዋቾችና አሠልጣኞች ፖሊሲ፣ የሰው ሀብት አጠቃቀም ፖሊሲና ሌሎችም ትርጉም ያለውና ይህ ነው ሊባል የሚችል እንደሌለው ያስረዳሉ፡፡

ለዚህ ሌላው ተጨማሪ ማሳያ የሚሉት ደግሞ ብሔራዊ ፌዴሬሽኑ በተለይም በመብራት መቆራረጥ ምክንያት በተለይ በአሁኑ ወቅት የተቋሙን የዕለት ተዕለት ሥራዎች ለመሥራት እየተቸገረ መሆኑ፣ ይሁንና ለስብሰባና መሰል እንቅስቃሴዎች ለሆቴልና ተያያዥ ጉዳዮች ግን 100 ሺሕ ብርና ከዚያም በላይ ወጪ እንደሚያወጣ፣ ሆኖም ቀደም ሲል ለተጠቀሱት የቢሮ ሥራዎች ግን አነስተኛ ጄኔሬተር መግዛት ያልቻለ መሆኑ ተቋሙ በምን ያህል ችግር ውስጥ እንደሚገኝም ይናገራሉ፡፡

ከውድድር ጋር ተያይዞ የሚነሱ አለመግባባቶችንና ግጭቶችን በሚመለከት፣ ተቋሙ በባለድርሻ አካላት ሳይቀር ተዓማኒነት እያጣ ስለመሆኑም ይናገራሉ፡፡ ለዚህ ማሳያ የሚያደርጉ ሌላው የፖሊሲ ክፍተት፣ በ2009 ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 30ኛ ሳምንት በተለይ ከጨዋታ ማጭበርበር ጋር ተያይዞ በሐዋሳ ከነማና በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ክለቦች ላይ የጅማ አባ ቡና እግር ኳስ ክለብ ለፌዴሬሽኑ ያቀረበው የፍትሕ ጥያቄ ይህ ዘገባ እስከተጠናቀረበት ድረስ ምንም ዓይነት ውሳኔ ማግኘት እንዳልቻለ ያስረዳሉ፡፡ ክለቦች ለ2010 የውድድር ዓመት ቅድመ ዝግጅት ጀምረዋል፡፡ አስተያየት ሰጪዎቹ ለእነዚህ ሁሉ ችግሮች ተቋሙ የፖሊሲ ማስፈጸሚያ ምንም ዓይነት የፖሊሲ ማዕቀፍ የሌለው መሆኑ ማረጋገጫ እንደሆነም ያክላሉ፡፡

 

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የማዳበሪያ አቅርቦትና ውጣ ውረዱ

በቅፅል ስሙ “The Father of Chemical Warfare” እየተባለ የሚጠራው...

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ የትርፍ ምጣኔውን ከ70 በመቶ በላይ አሳደገ

ከሁለቱ መንግሥታዊ ባንኮች መካከል አንዱ የሆነው የኢትዮጵያ ልማት ባንክ...