Tuesday, July 23, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ስፖርትያንሰራራው የብሔራዊ አትሌቶች ሽልማት

ያንሰራራው የብሔራዊ አትሌቶች ሽልማት

ቀን:

  ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በየውድድር አውድማ ታላላቅ ስፖርታዊ ድሎችን ባስመዘገቡ ቁጥር ብሔራዊ ደስታና ፈንጠዝያው ደምቆ የሚጎላው ወደ አገር ቤት ሲመለሱ እንደነበር የቅርብ ጊዜ ትውስታ ነው፡፡ ሕዝብ ባለፉበት አደባባይና ጎዳና እየተጋፋ የሚመለከታቸው፣ በጩኸትና በእልልታ እያጀበ የሚከተላቸው ባለ ድል አትሌቶች አቀባበል ከጊዜ ወደ ጊዜ እየደበዘዘ መጥቶ ነበር፡፡

      መንግሥትም እንደ ቀድሞ ሁሉ ለአትሌቶቹ የድል ስጦታ የሚሰጠው ልዩ ልዩ የዕውቅናና የሽልማት ጥቅማ ጥቅም ቀስ በቀስ አስቀርቶት ቆይቷል፡፡ በቅርቡ የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴን የተረከበው አዲሱ አመራር ግን ለአትሌቶች ይሰጥ የነበረው ጥቅማ ጥቅም እንደገና እንዲያንሰራራና መንግሥትም ያቋረጠውን የሽልማት ሥነ ሥርዓት ዳግመኛ እንዲያስጀምር ጠይቆም ነበር፡፡

በቀረበው ጥያቄ መሠረት አትሌቶችም በቅርቡ በለንደኑ የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ባስመዘገቡት ውጤት መሠረት የተቋረጠው ዕውቅናና ሽልማት እንደ አዲስ ተጀምሯል፡፡ ባለፈው ማክሰኞ መስከረም 2 ቀን 2010 ዓ.ም. በሐዋሳ ኃይሌ ሪዞርት የወጣቶችና ስፖርት ሚኒስቴር ባዘጋጀው ሥነ ሥርዓት ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ ለአትሌቶቹ የተዘጋጀላቸውን የመሬትና የገንዘብ ሽልማት አበርክተዋል፡፡

      ሽልማቱን አስመልክቶ ሪፖርተር ያነጋገራቸው አትሌቶችና ሙያተኞች የመንግሥት ውሳኔ አትሌቲክሰን ጨምሮ ቀስ በቀስ እየቀዘቀዘ ለመጣው ስፖርት መነቃቃት የጎላ ድርሻ እንደሚኖረው ተናግረዋል፡፡

መንግሥት ቀደም ባሉት ዓመታት ጀምሮ ሲከውነው የቆየውና ወደ ኋላ ላይ ተቋርጦ የነበረው ዕውቅናና ሽልማት አሁን በተጀመረው መስክ እንደገና እንዲጀምር ጥያቄውን ለመንግሥት ያቀረበው የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ፕሬዚዳንት አሸብር ወልደ ጊዮርጊስ (ዶ/ር)  በበኩላቸው፣ ለስፖርቱ ዕድገት የመንግሥት ድርሻ ዋናውና መሠረታዊ መሆኑን ነው ያስረዱት፡፡ የብሔራዊ ኦሊምፒክ ኮሚቴ አመራርም ይህንኑ ግምት ውስጥ በማስገባት ለጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ ያቀረበው ጥያቄ ተቀባይነት አግኝቶ ዕውን መሆኑ ለአመራሩም ሆነ ለስፖርቱ ትልቅ ጠቀሜታ እንዳለው ጭምር ተናግረዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሥነ ሥርዓቱ ካስተላለፉዋቸው መልዕክቶች መካከል የስፖርት ተቋማት በሙያው ያለፉ ሰዎች መመራት እንደሚገባቸው መግለጻቸውን አስመልክቶ ዶ/ር አሸብር፣ እነዚህና መሰል ክፍተቶች መስተካከል እንዳለባቸው ብሔራዊ ኦሊምፒክ ኮሚቴውም ሆነ ሌሎች የስፖርት ተቋማት በግምገማቸው ያስቀመጡት እንደሆነም ተናግረዋል፡፡

እንደ ፕሬዚዳንቱ በተለይ ብሔራዊ ፌዴሬሽኖች ለዚህ ኃላፊነት የሚያበቋቸው ሰዎች ስፖርቱን ማገዝ የሚችሉ እንጂ በስፖርቱ የሚታገዙ መሆን እንደሌለባቸው ጠቅላይ ሚኒስትሩም ይህንኑ ታሳቢ አድርገው የተናገሩትን እንደ አቅጣጫ ወስዶ ተግባራዊ ማድረግ እንደሚያስፈልግም አስረድተዋል፡፡ 

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

‹‹በየቦታው ምርት እየገዙ የሚያከማቹ ከበርቴ ገበሬዎች ተፈጥረዋል››

አቶ ኡስማን ስሩር፣ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በምክትል ርዕሰ መስተዳድር...

ኢትዮጵያዊ ማን ነው/ናት? ለምክክሩስ መግባባት አለን?

በደምስ ጫንያለው (ዶ/ር) የጽሑፉ መነሻ ዛሬ በአገራችን ውስጥ በተለያዩ አካባቢዎች ግጭቶችና...

ዴሞክራሲ ጫካ ውስጥ አይደገስም

በገነት ዓለሙ የዛሬ ሳምንት ባነሳሁት የኢሰመኮ ሪፖርት መነሻነትና በዚያም ምክንያት...

ኢትዮጵያ በምግብ ራሷን የምትችለው መቼ ነው?

መድረኩ ጠንከር ያሉ የፖሊሲ ጉዳዮች የተነሱበት ነበር፡፡ ስለረሃብ፣ ስለምግብ፣...