Tuesday, April 23, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -

ዝንቅተፋራጅ ያጣች ከተማ

ተፋራጅ ያጣች ከተማ

ቀን:

 በአቡቴ ደቦጭ

 በአገራችን ካሉት ከተሞች ምርጥ ማስተር ፕላን የተጎናፀፉ ተብለው ከሚጠቀሱት ጥቂት ከተሞች ማለትም እንደ መቐለ፣ ባህር ዳርና ሐዋሳ አንዷ ናዝሬት (አዳማ) ከተማ ናት፡፡ ማስተር ፕላኗም ዕውን የሆነው በንጉሡ ዘመነ መንግሥት ነበር፡፡ የናዝሬት ከተማ ማስተር ፕላን ድንቅ ሊባል የሚችልና አማላይ (መሳጭ) ነበር፡፡ የመንገዶቿ ቅያስ፣ ወጥ፣ ሰፊና ምቾት ያላቸው ነበሩ፡፡ በዋና ዋና መንገዶቿ አለፍ አለፍ ብሎ ለፓርኮች ግልጋሎት ታስቦ (ለመኪና፣ ለብስክሌት፣ ለፈረስ ጋሪ) የተዘጋጀው ሰፊ ቅያስ ከተሽከርካሪና ከእግረኛ ጋር በማይጋፋና ከዋናው መንገድ ገባ ያለ ነበር፡፡ ረድፋቸውን ጠብቀው የተተከሉ ዛፎች (ድሬ ሜላኖ . . . ) ከጽዱ ውበቷ ጋር ግርማ ሞገሷ ነበሩ፡፡

ከንጉሡ ዘመን አንስቶ የደርግ መንግሥት ማብቂያው ሁለት ዓመታት እስከ ቀሩበት 1981 ዓ.ም. ድረስ በነበሩት ዓመታት በከተማዋ የተሾሙ የአስተዳደር ባለሥልጣናት ገዢም ሆኑ ከንቲባ ከተማዋንና ነዋሪውን በጥልቀት የሚያውቁ ፍላጎቱን የሚረዱ ነበሩ፡፡ በጠቀስኳቸው ዓመታት የነበሩ ገዢም ሆኑ ከንቲባ ሠርተው የሚያሠሩ፣ የማስተባበር ችሎታ የነበራቸው፣ የሚከበሩ፣ የሚደመጡ፣ ተሰሚነት የነበራቸው፣ ከግል ጥቅም ይልቅ የሕዝብና የአገር ጥቅም የሚያስቀድሙ ድንቅና ታላቅ ራዕይ ያነገቡ ነበሩ፡፡

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

በወቅቱ የነበሩት ገዢዎች (ከንቲባዎች) ናዝሬት የእኔ ናት (መቆርቆርን ለመግለጽ የተጠቀምኩበት ቃል ብቻ መሆኑ ይታወቅ) የሚል እጅግ ጥልቅ ፍቅር እምነትና ፅናት የነበራቸው በፍቅሯ ያበዱ ነበሩ፡፡ ዛሬ እነዚህ ሁሉ በነበር ትዝታ ኤንቨሎፕ ውስጥ ታሽገው ከተቀመጡ እነሆ 26 ዓመታት ተቆጠሩ፡፡

ከ1983 ዓ.ም. የመንግሥት ሥርዓት ለውጥ ከተከሰተ ወዲህ (26 ዓመታት) ያለመታደል ሆነና የናዝሬት ከተማ ይኼ ነው ተብሎ በጉልህ ሊነገር በሚችል መልኩ የተሠራና የተገነባ የመሠረተ ግንባታ ሥራ እንዳልተካሄደባት በከተማዋ ተወልደው፣ አድገውና ለአዛውንትነት የበቁ አባቶችና ነዋሪዎቿ በልበ ሙሉነት ይናገራሉ፡፡ እንደ ዕድሜዋና እንደ እኩያዎቿ ከተማዋ አለማደጓ ፀሐይ የሞቀው ጉዳይ ነው ይላሉ፡፡ ይባስ ብሎ ከትናትናዋ ታዳጊ ሕፃን ከተማ ከሐዋሳ አንሳለች ሲሉ ቁጭት ባዘለ ንፅፅር ይገልፃሉ፡፡

  የናዝሬት ከተማ ውበት ዛሬ ላይ ደብዛው ጠፍቷል፡፡ እነዚያ በድንቅ ፕላኗ ውስጥ የተገነቡ ሕንፃዎቿ፣ የተዘረጉ መንገዶቿ፣ የተከለሉ (ፓርክና መናፈሻ) ሥፍራዎቿ፣ ሁሉ . . . ዛሬ ባለቤት የሌላት ከተማ እስክትመስል ድረስ የነበረው እንዳልነበረ ሆኗል፡፡ ለከተማዋ ውድቀትና ኋላ ቀርነት በግንባር ተጠያቂው መንግሥት መሆኑ አያጠያይቅም፡፡ መንግሥት ከተማዋ እስከመፈጠሯ የረሳት እስኪመስል ድረስ ተሾመ የተባለው ሹመኛ ማንነቱ ሳይታወቅ ወጥቶ ይወርዳል፣ ሌላውም እንዲሁ ይተካና ወጥቶ ይወርዳል፡፡

 መንግሥት በየጊዜው እያመጣ የሚመድባቸው የከተማው ሹመኞች ከተማ ውስጥ ያላደጉ (ያልኖሩ) አልያም የከተማ ጽንሰ ሐሳብ ግንዛቤ ያልተረዱና ያላወቁ በዕውቀትና በልምድ ያልበለፀጉ በመሆኑ የሚሠሩትን ሥራ በውል ተረድተው አያውቁትም፡፡ ከኅብረተሰቡ ጋር  በቀላሉ አይግባቡም፡፡ ከዚህ ይልቅ ለእነሱ የሚቀላቸው በ«ይዟት ይዟት በረረ» ዜማ ቅኝታቸውን ቃኝተው እንደ ጭልፊት አሞራ ሚሊዮን ብሮች ጨልፈው መብረር ብቻ ነው የሚታያቸው፡፡ ምክንያቱም ውስጣቸው የአገርና የሕዝብ ፍቅር እትብት የሌላቸው መሆኑ አንዱ ገጽታቸው ሲሆን፣ ሌላው ተጠያቂና ሕግ ፊት ከመቅረብ ፋንታ የሚጠብቃቸው ቅጣት ዞር መደረግ (ከተማ መቀየር) መሆኑን ጠንቅቀው ስለሚያውቁ ከተማዋ አደገች ወይም ወደቀች ቁብ አይሰጣቸውም፡፡

አገሬ ናዝሬት ከተማ አልባ ሆና ተፋራጅ በማጣቷ የከተማነት ቅርጿ እየሟሸሸ ሄዶ በነበር ልታሸልብ አንድ ሐሙስ የቀራት መስላለችና መንግሥትና ተወላጇ እንታደጋት እያልኩ ለአብነት ያህል ይህን ፎቶግራፍ ይመልከቱ መገንባት፣ መጠገን፣ ያልተሟላን ማሟላት ይቀድማል . . .  ወይስ የተሠራውን ማፍረስ??

  • ፡- ጽሑፉ የጸሐፊውን አመለካከት ብቻ የሚያንፀባርቅ መሆኑን እንገልጻለን፡፡

* * *

 

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ሰው መሆን ምንድን ነው? ቅርስና ማኅበራዊ ፍትሕ

በሱራፌል ወንድሙ (ዶ/ር) ዳራ ከጎራዎች፣ ከመፈራረጅ፣ ነገሮችን ከማቅለልና ከጊዜያዊ ማለባበስ ወጥተን...

ኢኮኖሚው ኢትዮጵያን እንዳያፈርሳት ያሠጋል

በጌታቸው አስፋው ኢትዮጵያን እንዳያፈርሱ የሚያሠጉኝ አንድ ሁለት ብዬ ልቆጥራቸው የምችላቸው...

የኢትዮጵያ የፖለቲካ ትግል በሕግ አምላክ ይላል

በገነት ዓለሙ የአገራችንን ሰላም፣ የመላውን ዓለም ሰላም ጭምር የሚፈታተነውና አደጋ...

በሽግግር ፍትሕ እንዲታዩ የታሰቡ የወንጀል ጉዳዮች በልዩ ፍርድ ቤት ሳይሆን በልዩ ችሎት እንዲታዩ ተወሰነ

የኤርትራ ወታደሮች በሌሉበትም ቢሆን ይዳኛሉ ተብሏል በፅዮን ታደሰ የሽግግር ፍትሕ የባለሙያዎች...