አስፈላጊ ጥሬ ዕቃዎች
- 2 ኩባያ ሥጋ፣ ተቀቅሎ የተከተፈ
- 2 ኩባያ ሩዝ፣ የተቀቀለ
- ½ ኩባያ ፎርማጆ
- 2 የሾርባ ማንኪያ ቅቤ
- 1 የሻይ ማንኪያ ጨው ወተት ወይም መረቅ ትንሽ ቁንዶ በርበሬ
አዘገጃጀት
- ሥጋውን ቀቅሎ መክተፍ
- ትንሽ ወተት ወይም መረቅ ከሥጋው ጋር ማደባለቅ
- በቅባት የታሰሰ መጋገሪያ ላይ ሩዙን ማድረግ
- ሩዙ ላይ ቅቤና ፎርማጆ መጨመር
- ቁንዶ በርበሬና ጨው ነስንሶ ተዘጋጀውን ሥጋ ላዩ ላይ ማድረግ
- ቀሪውን ቅቤና ፎርማጆ ጨምሮ ሙቀቱ 350 ድግሪ ፋራንሃይት በሆነ ምድጃ ከአሥራ አምስት እስከ ሃያ ደቂቃ ማብሰል፡፡ ስድስት ሰው ይመግባል፡፡
- ጽጌ ዑቁባሚካኤል ‹‹የእናት ጓዳ›› (1984)