Monday, July 15, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ስፖርትእግር ኳሱ የሁከትና የብጥብጥ መድረክ መሆኑ ለምን?

እግር ኳሱ የሁከትና የብጥብጥ መድረክ መሆኑ ለምን?

ቀን:

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ክለቦች በየጊዜው የአቋም፣ የብቃትና የክህሎት ለውጦችን ለማስመዝገብ አገር አቀፍና አህጉር አቀፍ ሲያልፍም በዓለም አቀፍ መድረኮች ላይ ተፎካካሪነታቸውን ከማስመስከር ይልቅ እርስ በርሳቸው ብሎም ደጋፊዎቻቸውን በሚያበጣብጡ ተግባራት ውስጥ ሲሳተፉ እየታዩ ነው፡፡

በሌሎች አገሮች ከውድድር ውጭ የሆኑ ክለቦች ከአቅም በታች በማይጫወቱበት የስፖርቱ ዲሲፕሊን በሚከበርበት በዚህ ወቅት፣ በኢትዮጵያ በተለያዩ ደረጃ በመጫወት ላይ የሚገኙ ሊጎች ማለትም በብሔራዊ ሊግ፣ በከፍተኛ ሊግ (ሱፐር ሊግ) እና በፕሪሚየር ሊግ የሚሳተፉ የአገሪቱ ክለቦች እንኳን ከመጪው ዓመት ውድድር ተሳታፊነታቸው ተገቶ ቀርቶ፣ ቆይታቸውን ካረጋገጡም በኋላ የሚያሳዩት የሥነ ምግባርና የሥነ ሥርዓት ጉድለት ከዓመት ወደ ዓመት እየተባባሰ መጥቷል፡፡

‹‹በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ›› እንደሚባለው በዝቅተኛና ከፍተኛ ዲቪዚዮኖች የሚጫወቱትም ሳይቀሩ መድረኩን የብጥብጥና የሁከት ምንጭ እያደረጉት ይገኛሉ፡፡ በክለቦች መካከል በሚፈጠሩ የዲሲፕሊን ጉድለቶች ሳቢያ፣ ደጋፊዎች የሚያስነሱት ረብሻና አምቧጓሮ  መልኩን እየቀያየረና እያገረሸ ወደ ብሔር ተኮር ግጭት ሲያመራም መታዘብ እየተቻለ ነው፡፡

ከሰሞኑ መቐለ ከተማ ላይ በመቐለ ከተማና በባሕር ዳር ከተማ መካከል በተደረገው የከፍተኛ ሊግ የጨዋታ መርሐ ግብር የተከሰተው አላስፈላጊ ሁከትና ብጥብጥ ለዚህ በማሳያነት ሊጠቀስ እንደሚችል የብዙዎች እምነት ሆኗል፡፡ እነዚሁ አስተያየት ሰጪዎች የችግሩን አሳሳቢነት በመጥቀስ የውድድሩ ባለቤትና አስተዳዳሪ ከሆነው ብሔራዊ ፌዴሬሽኑ ጀምሮ የሚመለከተው አካል መፍትሔ ሊሰጡበት እንደሚገባ ይመክራሉ፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ሚዲያው በሕዝብ የህሊና ችሎት ከተዳኘ በቂ ነው!

መሰንበቻውን ድንገት ሳይታሰብ ያለ ማስጠንቀቂያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ...

የባህር በር ጉዳይ

በታምሩ ወንድም አገኘሁ ድሮ ድሮ ገና ልጅ ሆኜ ፊደል እንደቆጠርኩ...

አገሩ ፖለቲካዊ ስክነትና መደማማጥ ያስፈልገዋል

በንጉሥ ወዳጀነው    ኢትዮጵያ የሁላችንም የጋራ ቤት ነች፡፡ ‹‹ጥያቄዬ ተመለሰልኝ››፣...

የመንግሥት የሰብዓዊ መብት ተቋም ለምን የመንግሥት ሚዲያን ማስተማር አቃተው

በገነት ዓለሙ የአገራችን የ2016 የበጀት ዓመት መሰናበቻና የአዲሱ የ2017 በጀት...