Thursday, July 25, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናየአማራ ክልል ጤና ቢሮ በ159 የግል ጤና ተቋማት ላይ የተለያዩ ዕርምጃዎች ወሰደ

የአማራ ክልል ጤና ቢሮ በ159 የግል ጤና ተቋማት ላይ የተለያዩ ዕርምጃዎች ወሰደ

ቀን:

የአማራ ክልል ጤና ቢሮ በክልሉ ውስጥ ካሉ የግል ጤና ተቋማት መካከል 159 ላይ ዕርምጃ መውሰዱን አስታወቀ፡፡

በአማራ ክልል ጤና ቢሮ የጤና ተቋማትና ባለሙያዎች ቁጥጥር ጊዜያዊ ኃላፊ አቶ መንበሩ ፍፁም ዓርብ ግንቦት 4 ቀን 2009 ዓ.ም. ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ 21 የመድኃኒት መደብሮች፣ አምስት የባህል ሕክምና ተቋማት፣ ሃያ ዘጠኝ ክሊኒኮችና 104 የምግብና ጤና ነክ ተቋማት ከባድ ማስጠንቀቂያ ተሰጥቷቸዋል፡፡

እንደ አቶ መንበሩ ገለጻ ቢሮው አምስት የመድኃኒት ችርቻሮ መደብሮችና ሰባት የጤና ተቋማትንም እንዲዘጉ አድርጓል፡፡ የአማራ ክልል ጤና ቢሮ የዘጠኝ ወራት ሪፖርቱን ሲያቀርብ እንደገለጸው፣ ከ21,651 ብር በላይ የሚገመቱ ሕገወጥና ጊዜው ያለፈባቸው መድኃኒቶችና 741,665 ብር በላይ የሚያወጡ የተበላሹ ምግቦች እንዲወገዱ አድርጓል፡፡

እንደ አቶ መንበሩ ገለጻ፣ እነዚህ የግል የጤና ተቋማት ከከባድ ማስጠንቀቂያ እስከ መዝጋት ድረስ ዕርምጃ የተወሰደባቸው አራቱን የጥራት ማረጋገጫ መሥፈርቶች አሟልተው ባለመገኘታቸው ነው፡፡ እነዚህም መስፈርቶች የተቋማቱ መገልገያ ሕንፃዎች ጥራት፣ የሕክምና መገልገያዎች በበቂ ሁኔታ መሟላት፣ የሰው ኃይልና በተሰጣቸው የንግድ ፈቃድ መሠረት መሥራት ናቸው፡፡

የመንግሥት የጤና ተቋማትን በተመለከተም ከደረጃ በታች የነበሩትን ከ400 በላይ የሚሆኑ ተቋማት ወደ ደረጃ እንዲገቡ ጥረት እየተደረገ እንደሆነ ገልጸዋል፡፡ ከዓመታት በፊት 400 የመንግሥት የጤና ጣቢያዎች በከባድ ማስጠንቀቂያ ተሰጥቷቸው እንደነበር፣ አሁን በተደረገው ድጋፍና ክትትል ቁጥሩን ወደ 113 ዝቅ ማድረግ መቻሉን ጠቁመዋል፡፡ ሃያ መካከለኛ የመንግሥት ክሊኒኮች ግን አሁንም ድረስ አደገኛ በሚባል ደረጃ ላይ እንደሚገኙ አቶ መንበሩ አስረድተዋል፡፡

 

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

“ከሁለት ሳምንት በፊት ወደ ኤርትራ የማደርገውን በረራ እንዳሳድግ ተጠይቄ ነበር” የኢትዮጵያ አየር መንገድ

ኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ኤርትራ የሚያደርገውን በረራ እንዲያሳድግ የሚጠይቅ...
00:06:46

የኤርትራ አቪዬሽን ባለሥልጣን የኢትዮጵያ አየር መንገድ በረራዎችን ማገዱን አስታወቀ

የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለሥልጣን ጉዳዩን እያጣራሁ ነው ብሏል በኤርትራ ትራንስፖርትና...

[ክቡር ሚኒስትሩ ከተቋሙ የሠራተኞች ማኅበር አመራር ጋር እየተወያዩ ነው]

ጤና ይስጥልኝ ክቡር ሚኒስትር? ሰላም! በአስቸኳይ እንደፈለጉኝ መልዕክት ደርሶኝ ነው የመጣሁት። አዎ።...

የሱዳን ጦርነትና የኢትዮጵያ ሥጋት

የሱዳን ጦርነት ከጀመረ አንድ ዓመት ከአራት ወራት አስቆጠረ፡፡ ጦርነቱ...