አስፈላጊ
- 6 የቡና ስኒ ፉርኖ ዱቄት
- 1 የቡና ስኒ ቅቤ
- 3 የሾርባ ማንኪያ ስኳር
- 2 የቡና ስኒ ዘቢብ
- 5 ዕንቁላል
- 1 የሻይ ማንኪያ ቫኒላ
- ½ ብርጭቆ ወተት
- 3 የሻይ ማንኪያ ቤኪንግ ፓውደር
አሠራር
- ቅቤ እና ስኳሩን ደባልቆ በደንብ ማሸት
- በላዩ ላይ የዕንቁላል አስኳል አንድ በአንድ መጨመርና ባንድ አብሮ ማሸት
- ዱቄቱንና ቤኪንግ ፓውደሩን አንድ ላይ በወንፊት መንፋትና ከዘቢቡ ጋር መደባለቅ
- ሎሚውንና ወተቱን መቀላቀል
- የሚጋገርበትን ዕቃ ቅቤ ቀብቶ ዱቄት መነስነስ
- የተሰናዳውን ሊጥ ማብሰያ ዕቃ ውስጥ መገልበጥና ዕቃውን በአሉሚኒየም ወረቀት ሸፍኖ መካከለኛ ሙቀት ባለው ምድጃ ውስጥ ለግማሽ ሰዓት ያህል ማብሰልና ወረቀቱን ማንሣት
- ምድጃው ውስጥ ማቆየትና መብሰል አለመብሰሉን በቀጭን እንጨት ወጋ አድርጎ ማየት
- ከወጣ በኋላ ለአምስት ደቂቃ አቆይቶ የሚቀርብበት ዕቃ ላይ ማስቀመጥ
- ምንጭ ‹‹ባህላዊ ምግቦችና አሠራራቸው››