Sunday, January 29, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊየውኃ ሀብት ልማት ፈንድ ለአራት የክልል ከተሞች 300 ሚሊዮን ብር የሚጠጋ ብድር...

የውኃ ሀብት ልማት ፈንድ ለአራት የክልል ከተሞች 300 ሚሊዮን ብር የሚጠጋ ብድር ለቀቀ

ቀን:

  • ከአውሮፓ ኢንቨስትመንት ባንክና ከሁለት ኤጀንሲዎች ከ150 ሚሊዮን በላይ ዩሮ በብድር አግኝቷል

በልዩ የብድር ማዕቀፍ ለከተሞች የንፁህ መጠጥ ውኃ አቅርቦት የሚውሉ ፕሮጀክቶችን ፋይናንስ ለማድረግ የሚንቀሳቀሰው የውኃ ሀብት ልማት ፈንድ፣ ለአራት አነስተኛ የክልል ከተሞች የ300 ሚሊዮን ብር ብድር ሰጠ፡፡

ሐሙስ ሚያዝያ 26 ቀን 2009 ዓ.ም. በተካሄደ የብድር ስምምነት ሥነ ሥርዓት ብድሩን ያገኙት በኦሮሚያና በደቡብ ክልሎች የአርጆ፣ የዶዶላ፣ የጂንካና የሺንሺቾ ከተሞች ናቸው፡፡ በብድር ስምምነቱ ወቅት የውኃ ሀብት ልማት ፈንድ ዋና ዳይሬክተር አቶ ዋና ዋኬ እንደገለጹት፣ ከተሞቹ በብድር የሚሰጣቸው ገንዘብ በመጪዎቹ 20 ዓመታት ውስጥ የሚከፈልና ዝቅተኛ ወለድ የሚታሰብበት ነው፡፡ በመሆኑም በአራቱም ከተሞች ውስጥ ለሚኖሩ 300 ሺሕ ሰዎች የመጠጥ ውኃ ፕሮጀክቶችን ለመገንባት ከሚያስፈልገው 426.6 ሚሊዮን ብር ውስጥ፣ የውኃ ሀብት ልማት ፈንድ 300 ሚሊዮን የሚጠጋውን በብድር አቅርቧል፡፡

የተቀረውን 126.6 ሚሊዮን ብር ከተሞቹ ከራሳቸው፣ ከዞን እንዲሁም ከክልል በጀት እንደሚሸፍኑ ስምምነት ተደርሷል፡፡ በዚህ አግባብ የጂንካ ከተማ በብድር ያገኘው 75 በመቶ ሲሆን፣ ቀሪውን 25 በመቶ ወጪ በራሱና በክልሉ በጀት ይሸፍናል ማለት ነው፡፡ የአርጆ ከተማ 60 በመቶ፣ የዶዶላና የሺንሺቾ ከተሞች እያንዳንዳቸው 70 በመቶ የፕሮጀክት ወጪያቸውን በብድር የሚሸፍኑ ሲሆን፣ ቀሪውን 30 በመቶ በራሳቸው ወይም በክልል በጀት እንደሚያሟሉ ይጠበቃል፡፡

የውኃ ሀብት ልማት ፈንድ በገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስቴር አማካይነት የሚያገኛቸውን የውጭ ብድሮች መልሶ በማበደር የውኃና የሳኒቴሽን ፕሮጀክቶችን ፋይናንስ ማድረግ ከጀመረ ወዲህ፣ በተለይ በጥቂት ወራት ውስጥ አራቱን ከተሞች ጨምሮ ለ12 ከተሞች 760 ሚሊዮን ብር ብድር መስጠቱ ታውቋል፡፡ ከአራት ወራት በፊት በትግራይ፣ በደቡብ እንዲሁም በኦሮሚያ ክልሎች ውስጥ ለሚገኙ ስምንት ከተሞች 188.4 ሚሊዮን ብር ሲያበድር፣ ከተሞቹም 120 ሚሊዮን ብር ማዋጣታቸውን መዘገባችን ይታወሳል፡፡

በአሁኑ ወቅት ከ90 ከተሞች ውስጥ የመበደር አቅም እንዳላቸው ተለይተው የተመሩ 43 ያህል ከተሞች እየተጠኑ እንደሚገኙ ተገልጾ፣ ከእነዚህ ውስጥ ግን ተገቢውን የብድር መሥፈርቶች በማሟላት አዋጭ ፕሮጀክቶችን ያቀረቡ 12 ከተሞች እንደሆኑና ብድሩንም እንዲያገኙ መደረጉን ተቋሙ አስታውቋል፡፡

የአውሮፓ ኢንቨስትመንት ባንክ፣ የጣሊያን ዓለም አቀፍ ልማት ኤጀንሲና የፈረንሣይ ልማት ኤጀንሲ በመተባበር ከዚህ ቀደም ለስምንቱ ከተሞች 75 ሚሊዮን ዩሮ ብድር የፈቀዱ ሲሆን፣ አሁን ያፀደቁት ተጨማሪ 81.4 ሚሊዮን ዩሮ ተደምሮ በአጭር ጊዜ ውስጥ ለውኃ ልማት ፈንድ ያቀረቡት ብድር 156.4 ሚሊዮን ዩሮ እንደደረሰ ለማወቅ ተችሏል፡፡

ከተመሠረተ 15 ዓመታት ያስቆጠረው የውኃ ሀብት ልማት ፈንድ፣ ከስድስት ሚሊዮን ብር በላይ ብድር ለተለያዩ ከተሞች በማቅረብ ከ60 በላይ ፕሮጀክቶችን ፋይናንስ እንዳደረገ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡  

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የገጠር መሬት ማሻሻያና የመሬት ባለቤትነት ጥያቄ በኢትዮጵያ

በኢትዮጵያ ከቅርብ ወራት ወዲህ መሬትን በተመለከተ ጠንከር ያሉ የለውጥ...

በፖለቲከኞች እጅ ያለው ቁልፍ

ኢትዮጵያ በተለይ ካለፉት አምስት ዓመታት ወዲህ ሰላሟ መረጋጋት አቅቶታል፡፡...

የኤክሳይስ ታክስ ረቂቅ አዋጅ ፓርላማው ያፀደቀውን አዋጅ የሚጥሱ ድንጋጌዎችን በማካተቱ እንዳይፀድቅ ተጠየቀ

ሰሞኑን ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የቀረበው የኤክሳይስ ታክስ ማሻሻያ...

በፀጥታ ችግር ሳቢያ ከተለያዩ አካባቢዎች ተፈናቅለው አማራ ክልል የገቡ ዜጎች ቁጥር 800 ሺሕ መድረሱ ተነገረ

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል 112 ሺሕ ተማሪዎች ከትምህርት ገበታ ውጪ...