- ግማሽ ኪሎ በስሱ የተቆራረጠ የጥጃ ሥጋ
- 1 እንቁላል
- 4 የሾርባ ማንኪያ ማርገሪን
- 1 የሾርባ ማንኪያ ወተት
- 1 የሾርባ ማንኪያ ጨው
- ሩብ ኩባያ የፉርኖ ዱቄት
- 1 ኩባያ የተፈጨ ዳቦ
ትንሽ ቁንዶ በርበሬ፣ ለማቅለሚያ የሚሆን ዘይትና ለማጌጫ የሚሆን ፐርሰሜሎ
አሠራር
- የጥጃው ሥጋ ውስጥ ማርገሪና ፐርሰሜሎ ጨምሮ ማደባለቅ
- ወተትና እንቁላል አንድ ላይ አደባልቆ በሹካ ማዋሐድ
- ጨው፣ ቁንዶ በርበሬ፣ የፉርኖ ዱቄት በሣህን ማደባለቅ
- የተፈጨ ዳቦ ለብቻው ሣህን ውስጥ ማድረግ
- ሥጋውን በየተራ በተደባለቀው የፉርኖ ዱቄት፣ በተመታው እንቁላልና በተዘጋጀው ወተት ውስጥ መንከር፣ እንደገና በተፈጨው ዳቦ ውስጥ መንከር፡፡
- ጽጌ ዑቁባሚካኤል ‹‹የእናት ጓዳ›› (1984)