አስፈላጊ ጥሬ ዕቃዎች
- 5 ካሮት፣ ተልጦ በቁመቱ የተቆረጠ
- ¼ ኪሎ ተልጦ በቁመቱ የተቆረጠ ድንች
- ¼ ፔፐሮኒ ፍሬው ወጥቶ በቁመቱ የተቆረጠ
- 2 ዝኩኒ በክብ የተቆረጠ
- ¼ ኪሎ ጭቅና ሥጋ፣ የተዘለዘለ
- 5 ፍንካች ነጭ ሽንኩርት፣ የተፈጨ
- 2 የሾርባ ማንኪያ ፐርሰሜሎ የተፈጨ
- 1 ቀይ ሽንኩርት በደቃቁ የተከተፈ
- 4 የሾርባ ማንኪያ ዘይት፣ የሱጎ መሥሪያ
- ¼ ኪሎ የተፈጨ ቲማቲም
ጨው፣ ቁንዶ በርበሬ ዘይት ለጎመን መጥበሻ
አሠራር
- ካሮት፣ ድንች፣ ፔፐሮኒ፣ ዝኩኒ በሙሉ አጥቦ በንፁሕ ጨርቅ ማድረቅ፣
- በመጥበሻ ላይ አድርጎ ለየብቻው በዘይት መጥበስ
- በአንድ ድስት ውስጥ ቀይ ሽንኩርት፣ ነጭ ሽንኩርት፣ ዘይት ፐርሰሜሎና ሥጋ አንድ ላይ ማቁላላት፡፡
- የተፈጨ ቲማቲም መጨመር፣ ጨውና ቁንዶ በርበሬ ጨምሮ ማውረድ
- የተጠበሰውን ጎመን በአንድ ሰፊ ድስት ውስጥ ማደባለቅ፣ በተራ ቁጥር 3 ከተዘጋጀው ሱጎ ጋር ማዋሐድ፡፡ ደረቅ እስኪል ድረስ በምድጃ ውስጥ ወይም በፎርኔሎ ላይ አቆይቶ በትኩሱ ማቅረብ፡፡
ስምንት ሰው ይመግባል፡፡
- ጽጌ ዑቁባሚካኤል ‹‹የእናት ጓዳ›› (1984)
* * *