Thursday, July 25, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናግጭት ውስጥ የነበሩት የኦሮሚያና የሶማሌ ክልል ነዋሪዎች የሰላም ኮንፍረንስ አካሄዱ

ግጭት ውስጥ የነበሩት የኦሮሚያና የሶማሌ ክልል ነዋሪዎች የሰላም ኮንፍረንስ አካሄዱ

ቀን:

ለአሥር ዓመታት ያህል በወሰን ምክንያት ሲጋጩ የቆዩት የኦሮሚያና የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ነዋሪዎች የጋራ ኮንፈረንስ ማካሄዳቸው ታወቀ፡፡

ሁከትና ግጭት ተቀስቅሶባቸው የነበሩ የሐረርጌና የባሌ፣ የፋፈን፣ የሲቲ፣ የአፍዴራና የነጎብ ዞኖች ውስጥ ይኖሩ የነበሩ ዜጎች ከፍተኛ የመንግሥት አመራሮች፣ የሁለቱ ክልሎች ርዕሳነ መስተዳድሮችና የመንግሥት ተወካዮች፣ አባ ገዳዎች፣ የአገር ሽማግሌዎችና ወጣቶች በተገኙበት ሚያዝያ 18 ቀን 2009 ዓ.ም. በድሬዳዋ ከተማ ኮንፈረንስ ማካሄዳቸውን የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት የኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ አዲሱ አረጋ ለሪፖርተር ተናግረዋል፡፡

አቶ አዲሱ የውይይቱ ዓላማ በፌዴራልና በአርብቶ አደር ልማት ሚኒስቴር አማካይነት፣ በሁለቱ ክልሎች ርዕሳነ መስተዳድሮች መካከል የተደረሰበትን ስምምነት ወደ መሬት ለማውረድና የነበረውን አለመግባባት ወደ ሰላም ለመመለስ ያለመ እንደነበር ገልጸዋል፡፡

የኮንፈረንሱ ይዘትም በ1997 ዓ.ም. በተደረገው ሕዝበ ውሳኔ መሠረት፣ ግልጽ የሆነ የወሰን ማካለል ባልተካሄደባቸው አካባቢዎች የወሰን ማካለል እንዲደረግባቸው የሚያግዝ የጋራ ስምምነት ለመፍጠር ነው ሲሉ አቶ አዲሱ ገልጸዋል፡፡

ስምምነቱም ለዘመናት በፍቅርና በሰላም ይኖሩ የነበሩ ወንድማማች ሕዝቦችን ዳግመኛ የሚያቀራርብ ጠቃሚ መድረክ መሆኑን አቶ አዱሱ ገልጸው፣ ተሳታፊዎቹም ይህንኑ መገንዘባቸውን አክለዋል፡፡

መድረኩ የተሳካና የሕዝብ ለሕዝብ ትስስርን ለማጠናከር የረዳ እንደነበር ተነግሮለታል፡፡ በኮንፈረንሱ ተሳታፊ የነበሩ አካላት ሰላምን ለማስፈን ጠንክረው እንዲሠሩ፣ ወደፊትም የሪፈረንደም እንቅስቃሴውን ተግባራዊ ከማድረግ አኳያ ሚናቸውን እንዲወጡ ያስቻለ በመሆኑ፣ ‹‹የሰላም ኮንፈረንስ›› ተብሎ ሊጠራ እንደሚችል አቶ አዱሱ ገልጸዋል፡፡

አቶ አዲሱ እንዲዚህ ዓይነቱ ኮንፈረንስ ጠቃሚነቱን ለመነጋገር ውይይት ብቻ ሳይሆን፣ በሁለቱ ክልሎች አዋሳኝ አካባቢዎች ውስጥ የሚኖሩ ወገኖች በልማት የሚተሳሰሩበትን ዕድል እንደሚፈጥርም ተናግረዋል፡፡

‹‹በሁለቱ ክልል አዋሳኝ አካባቢዎች የሚኖሩ ወገኖች በአካባቢው የሰው ደም ከሚፈስበት ይልቅ፣ የልማት ቦታ መሆን እንዳለበት የተስማሙበት ነው፤›› ብለዋል፡፡

አቶ አዲሱ አክለውም፣ ‹‹መንስዔው የሕዝብ ለሕዝብ ግጭት ሳይሆን፣ የተወሰኑ የመንግሥት አካላት መሬትን ለማስፋፋትና የኢኮኖሚ ፍላጎቶቻቸውን ለማርካት የሚያከናውኑት ድርጊት ነው፤›› በማለት ገልጸዋል፡፡

በተካሄደው ኮንፈረንስ በሁለቱ ክልሎች መካከል የሚኖሩ ሽማግሌዎች ከዚህ ቀደም ለሰላም ያደርጉት የነበረውን ጥረት እንደሚገፉበትና ወንጀለኞችንም አጋልጠው እንደሚሰጡ መግለጻቸውን፣ አቶ አዲሱ አስታውቀዋል፡፡

መንግሥት አጥፊ ወገኖችን ተጠያቂ ለማድረግ እየሠራ መሆኑን ጠቁመው፣ ከግጭቱ ጋር በተያያዘ እጃቸው አለበት የተባሉ አካላት በሕግ ጥላ ሥር አውሎ ምርመራ እያካሄደ መሆኑን ወደፊትም እንደሚገፋበት ገልጸዋል፡፡

ግጭቱ እስከ ቅርብ ጊዜ የቀጠለና የኮማንድ ፖስቱ ልዩ ኃይል እስካሁን ድረስ በአካባቢው በመኖሩ ምክንያት የሟቾችን ቁጥርና የወደመውን ንብረት ለማወቅ እንደሚስቸግር አቶ አዲሱ ተናግረዋል፡፡

በኦሮሚያና በሶማሌ ክልሎች መካከል በነበረው ይገባኛል ጥያቄ ሰበብ በተከሰተው ግጭት የሰው ሕይወትና ንብረት የጠፋ ሲሆን፣ ግጭቱ እንዲቆም ሚያዝያ 11 ቀን 2009 ዓ.ም. በፌዴራል አርብቶ አደርና ልማት ጉዳዮች ሚኒስቴር አማካይነት ሁለቱ ክልሎች ስምምነት ማድረጋቸው ይታወሳል፡፡

 

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

“ከሁለት ሳምንት በፊት ወደ ኤርትራ የማደርገውን በረራ እንዳሳድግ ተጠይቄ ነበር” የኢትዮጵያ አየር መንገድ

ኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ኤርትራ የሚያደርገውን በረራ እንዲያሳድግ የሚጠይቅ...
00:06:46

የኤርትራ አቪዬሽን ባለሥልጣን የኢትዮጵያ አየር መንገድ በረራዎችን ማገዱን አስታወቀ

የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለሥልጣን ጉዳዩን እያጣራሁ ነው ብሏል በኤርትራ ትራንስፖርትና...

[ክቡር ሚኒስትሩ ከተቋሙ የሠራተኞች ማኅበር አመራር ጋር እየተወያዩ ነው]

ጤና ይስጥልኝ ክቡር ሚኒስትር? ሰላም! በአስቸኳይ እንደፈለጉኝ መልዕክት ደርሶኝ ነው የመጣሁት። አዎ።...

የሱዳን ጦርነትና የኢትዮጵያ ሥጋት

የሱዳን ጦርነት ከጀመረ አንድ ዓመት ከአራት ወራት አስቆጠረ፡፡ ጦርነቱ...