Friday, December 8, 2023
- ማስታወቂያ -
- ማስታወቂያ -

የኦሮሚያ ዝቅተኛ ግብር ከፋዮች የተሻሻለውን የግብር አዋጅ ተግባራዊ እንዲያደርጉ ማሳሰቢያ ተሰጠ

ተዛማጅ ፅሁፎች

ዓመታዊ የሽያጭ ገቢያቸው 100,000 ብር የነበረው በአዲሱ የግብር አዋጅ ወደ 500,000 ብር ከፍ ካለ በኋላ፣ ዝቅተኛ ግብር ከፋዮችና የሚመለከታቸው ነጋዴዎች አዋጁን ተግባራዊ ለማድረግ ተግተው መሥራት እንዳለባቸው፣ የኦሮሚያ ክልል ገቢዎች ባለሥልጣን አሳሰበ፡፡

የኦሮሚያ ገቢዎች ባለሥልጣን አዋጁን ተግባራዊ ለማድረግ ከክልሉ የንግድ ምክር ቤቶች ጋር በቅንጅት እየሠራ መሆኑን ጠቁሞ፣ በተሻሻለው የገቢ ግብር አዋጅ ምንነት፣ አስፈላጊነትና በአማካይ የቀን ገቢ ላይ እየመከረ መሆኑንም  ገልጿል፡፡

የባለሥልጣኑ ዋና ዳይሬክተር አቶ አህመድ ቱሳ እንደተናገሩት፣ ዓመታዊ የሽያጭ መጠን ከ100,000 ብር ወደ 500,000 ብር ሲሻሻል የንግዱ ማኅበረሰብ በሚያንቀሳቅሰው ሀብትና ገቢ አቅሙን ያገናዘበ ግብር እንዲከፍል ያስችለዋል፡፡

የዕለት ገቢ ተመንን በሚመለከትም የግብር አወሳሰን አዋጁ ቀጥተኛ ካልሆኑ የገቢ ምንጮች የሚሰበሰበውን ታክስ በአግባቡ ለመንግሥት ገቢ እንዲሆን እንደሚያስችልም አክለዋል፡፡ እንደ ዳይሬክተሩ ገለጻ ከኢንቨስትመንት፣ ከመሬት፣ ከቤቶች ዝውውር፣ ከማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎቶችና ሌሎች የታክስና የግብር ዓይነቶች አሟጦ ለመንግሥት ለማስገባት የተጀመረውን ዘመቻ ያጠናክረዋል፡፡

የንግዱ ማኅበረሰብ በአዋጁ ላይ በቂ ግንዛቤና ዕውቀት እንዲኖረው ከባለሥልጣኑ ጋር በቅርበት እየሠራ መሆኑም ተጠቁሟል፡፡

የዕለት ገቢ ተመንና የግብር አወሳሰን ኮሚቴ ሕጉንና ደንቡን ተክትሎ በመሥራት የንግድ ማኅበረሰቡን ቅሬታ የሚፈታ፣ ፍትሐዊ ተመን ሊወስን እንደሚገባ የንግድ ምክር ቤቶች አባላት ተናግረዋል፡፡

አዲሱ አዋጅ በትክክል ተግባራዊ ከተደረገ ነጋዴው ትክክለኛና ፍትሕዊ የዕለት ገቢ ተመን እንዲሰጥ ከማስቻሉም በላይ፣ በግብር ከፋዩና በመንግሥት መካከል ግልጽነትና መተማመን እንዲኖር እንደሚያስችል የምክር ቤቶች ተወካዮች ገልጸዋል፡፡

 

spot_img
- Advertisement -spot_img

የ ጋዜጠኛው ሌሎች ፅሁፎች

- ማስታወቂያ -

በብዛት ከተነበቡ ፅሁፎች