Wednesday, February 21, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ዝንቅበምድረ ቀደምት ፀሐይ ሥር

በምድረ ቀደምት ፀሐይ ሥር

ቀን:

  • የንግሥተ ሳባና የቀዳማዊ ምኒልክ መቀመጫ፣ የታቦተ ሕጉ መንበሯን ጥንታዊቷ አክሱምን ከወር በፊት በማለዳ እየጎበኙ ከነበሩት ቱሪስቶች ሁለቱ (ፎቶ በሔኖክ ያሬድ)

ለቀናት እንቁላሎች ታቅፎ ጫጩት ያስፈለፈለው አርቲስት

ፈረንሳዊው አርቲስት አብርሃም ፖይንቺሻል እንደ ፕሮጀክት ይዞ አስገራሚ ነገሮችን በመሥራት ይታወቃል፡፡ አሁን ደግሞ አሥር እንቁላሎችን ለቀናት እንደ እናት ዶሮ በመታቀፍ ጫጩቶች እንዲፈለፍሉ ማድረጉን ሮይተርስ ዘግቧል፡፡ አርቲስቱ ጫጩቶቹ እንዲፈለፈሉ ከ21-26 ቀን ያህል እንደወሰደበት ገልጾ የነበረ ቢሆንም ብዙዎቹ እንቁላሎች ቀድመው መፈለጋቸውን የሮይተርስ ዘገባ ያመለክታል፡፡

                        ***

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

በሥልጣን ላይ ሳሉ የሞቱ አሥር አፍሪካውያን ፕሬዚዳንቶች

1) ሚሻኤል ሳታ፣ የዛምቢያ ፕሬዚዳንት

በ77 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም የተለዩት ሚሻኤል ሳታ፤ በምን በሽታ እንደሞቱ በግልፅ አልተነገረም። ሳታ እ.ኤ.አ 2014 እንግሊዝ ውስጥ ነው ያረፉት። እ.ኤ.አ 2011 በዛምቢያ ውስጥ ምርጫ ከተካሄደ በኋላ የሳታ ጤንነት አሳሳቢ ደረጃ ላይ መሆኑ ይወራ ነበር። ሳታ በአገሪቱ መድረኮች ሁሉ ለሕዝብ ባለመታየታቸው ማኅበረሰቡ ሥጋት ላይ ወድቆ ነበር። ቃል አቀባያቸው በበኩላቸው ለተደጋጋሚ ጊዜ ወደ መድረክ እየቀረቡ ሳታ ጥሩ ጤና ላይ እንደሚገኙ ይገልፁ ነበር።

2) መለስ ዜናዊ፣ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር

ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ በ2004 ዓ.ም. ነሐሴ ወር ቤልጂየም ውስጥ ነው ያረፉት። መለስ ዜናዊ ኢትዮጵያን ለ 21 ዓመታት መርተዋል። መለስ 1983 ዓ.ም. እስከ 1987 ዓ.ም. ፕሬዚዳንት ነበሩ። ከ1988 ዓ.ም. እስከ 2004 ዓ.ም. ድረስ በጠቅላይ ሚኒስትርነት አገልግለዋል። መለስ ዜናዊ በኢትዮጵያ መድብለ ፓርቲ ሥርዓትን በማስተዋወቃቸው ይታወቃሉ። ይሁንና መንግሥታቸው ሰብዓዊ መብትን በመርገጥ ትችት ይሰነዘርበታል።

3) ጆን አታ ሚልስ፣ የጋና ፕሬዚዳንት

የጋናው ፕሬዚዳንት ጆን አታ ሚልስ ከዚህ ዓለም የተለዩትም እ.ኤ.አ. 2012  ነው። በ2008 በጋና የተካሄደውን ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ያሸነፉት ጆን አታ ሚልስ በልብ መታወክና ደም ግፊት እንዲሁም የሳምባ ነቀርሳ በሽታ ነው በ 69 ዓመታቸው የሞቱት። አታ በጋና ሰፊ ኢኮኖሚያዊና ማኀበራዊ ተሃድሶ በማካሄዳቸው በአገራቸውም ሆነ በዓለም አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ ውደሳን ተቸረዋል።

4) ቢንጉ ዋ ሙታሪካ፣ የማላዊ ፕሬዚዳንት

የማላዊው ፕሬዚዳንት ቢንጉ ዋ ሙታሪካ የሞቱት እ.ኤ.አ. በ2012 ሚያዝያ ወር ውስጥ ነው። በ78 ዓመታቸው በድንገተኛ የልብ ሕመም ከዚህ ዓለም የተለዩት ሙታሪካ ማላዊን ለስምንት ዓመታት በፕሬዚዳንት አገልግለዋል። ሙታሪካ በሥልጣን ዘመናቸው በአገሪቱ ስኬታማ የነበረ የምግብና እርሻ ፖሊሲ አራምደዋል። ሙታሪካ የነበራቸውን ጥሩ ስም ያጎደፉት 13 ሚሊዮን ዩሮን አውጥተው የግል ጀት አውሮፕላንን በመግዛታቸው ነበር።

5) ማላም ባቺ ሳና፣ የጊኒ ቢሳው ፕሬዚዳንት

የጊኒ ቢሳው ፕሬዚዳንት ማላም ባቺ ሳና እ.ኤ.አ. 2012 ዓ.ም በሥልጣን ላይ ሳሉ ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩት አራተኛው ፕሬዚዳንት ናቸው። ከአራት ዓመት የሥልጣን ዘመን በኋላ በ64 ዓመታቸው ፓሪስ ዉስጥ የሞቱት ማላም ባቺ ሳና በስኳር በሽታ ይሰቃዩ ነበር። በሥልጣን ዘመን ላይ ሳሉ በተለያዩ በሽታዎች ይሰቃዩ ስለነበር ለተደጋጋሚ ጊዜ ሆስፒታል ይገቡ ይወጡ ነበር።

6) ሙአመር ኧል ጋዳፊ፣ የሊቢያ አብዮታዊ መሪ

ራሳቸውን የሊቢያ አብዮታዊ መሪ ሲሉ ይጠሩ የነበሩት ሙአመር ኧል ጋዳፊ ሥልጣን ላይ ሳሉ በ 69 ዓመታቸው ወደ ሊቢያዋ ከተማ ሲርት ሽሽት ላይ ሳሉ ነው በአማፅያን የተገደሉት። ሙአመር ኧል ጋዳፊ የሊቢያን በትረ ሥልጣን ለ42 ዓመታት ተቆናጠው ገዝተዋል። እ.ኤ.አ. በ1969 ወደ ሥልጣን የመጡት የሊቢያውን የንጉሠ ነገሥት መንግሥት ከሥልጣን ገልብጠው ነበር። በ2011 ዴንሃግ ኔዘርላንድ የሚገኘው የዓለም አቀፉ የጦር ወንጀለኞች ፍርድ ቤት ጋዳፊ በሰው ልጆች ላይ ፈፀሙት ባለው ወንጀል እንዲያዙ የእስር ማዘዣ ቆርጦባቸው ነበር።

7) ኡመር ሙሳ ያር አድዋ፣ የናይጀርያ ፕሬዚዳንት

የናይጀርያው ፕሬዚዳንት ኡመር ሙሳ ያር አድዋ እ.ኤ.አ. 2011 በ58 ዓመታቸው በልብ ሕመም ከዚህ ዓለም ተለዩ። ኡመር ሙሳ በሥልጣን ላይ ለሦስት ዓመት ብቻ ነው የቆዩት። በአገሪቱ በተካሄደው ፕሬዚዳንታዊ የምረጡኝ ዘመቻ ወቅት ብዙም ያልታዩት ሟቹ ፕሬዚዳንት፣ ምርጫውን ካሸነፉ በኋላ በ2007 ሚያዝያ ወር ላይ እጅግ ፈጣን በሚባል ሁኔታ የጤንነታቸው ይዞታ አሽቆልቁሎ ነበር።

8) ዥዋው ቤርናዶ ቪራ፣ የጊኒ ቢሳው ፕሬዚዳንት

የጊኒ ቢሳው ፕሬዚዳንት ዥዋው ቤርናዶ ቪራ በ69 ዓመታቸው እ.ኤ.አ. 2009  አገራቸው ውስጥ በወታደሮች ተገድለው ነው የሞቱት። የጊኒ ቢሳውን በትረ ሥልጣን ለ31 ዓመታት ተቆናጠው የቆዩት ፕሬዚዳንት ዥዋው ቤርናዶ ቪራ፣ በ1978 ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው ተመርጠው ለ19 ዓመታት ሥልጣን ላይ ቆይተዋል። ቆየት ብሎም የፕሬዚዳንትነቱን ሥልጣን ጨበጡ። ቪራ በአገሪቱ የእርስ በርስ ጦርነት በመከሰቱ በ1999 ወደ ፖርቱጋል ተሰደዱ። ከስደት መልስ ዥዋው ቤርናዶ ቪራ በ2005 ዳግም ፕሬዚዳንት ሆነው ተመርጠው ነበር።

9) ኦማር ቦንጎ፣ የጋቦን ፕሬዚዳንት

በአንጀት ነቀርሳ በሽታ ሲሰቃዩ የነበሩት የጋቦኑ ፕሬዚዳንት ኦማር ቦንጎ በ72 ዓመታቸው እ.ኤ.አ. በ2009 ስፔን ውስጥ ነው የሞቱት። ለ42 ዓመታት ጋቦንን በፕሬዚዳንትነት የመሩት ኦማር ቦንጎ፣ በዓለማችን ለረጅም ጊዜ መንበረ ሥልጣን ተቆጣጥረው የቆዩ የዓለማችን የመጀመርያው ፕሬዚዳንት ናቸው። ኦማር ቦንጎ በከፍተኛ ሙስና የሚታወቁም ናቸዉ። በተፈጥሮ ነዳጅ ዘይት ሀብት የበለፀገችዋ ጋቦን ማኅበረሰብዋ በድህነት ሲማቅቅ ቦንጎ እጅግ ከፍተኛ ሀብትን ያካበቱም ነበሩ።

10) ላንሳና ኮንቴ፣ የጊኒ ፕሬዚዳንት

ከ24 ዓመት የሥልጣን ዘመን በኋላ በሞት የተለዩት የ74 ዓመቱ የጊኒ ፕሬዚዳንት ላንሳና ኮንቴ ለረጅም ጊዜ የልብና የስኳር በሽታ ታማሚ ነበሩ። እ.ኤ.አ. ከ1984 እስከ 2008 ድረስ ጊኒን በፕሬዚዳንትነት የመሩት አላሳና ኮንቴ ጊኒ ከፈረንሳይ ቅኝ ግዛት ከተላቀቀች በኋላ ሁለተኛው ፕሬዚደንት ናቸው። ሦስት ጊዜ የፕሬዚዳንት ምርጫን ያሸነፉት ኮንቴ በብዙ ዓይነት በሽታዎች በመታወካቸው ለተደጋጋሚ ጊዜ ለሕክምና ወደ ውጭ አገር ይጓዙ ነበር።

  • ከዶቼ ቬሌ ድረ ገጽ
spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የካቲት አብዮት – ጥያቄዎችሽ ዛሬም እየወዘወዙን ነው!

በበቀለ ሹሜ አጭር መግቢያ የዚህ ጽሑፍ አቅራቢ ከ1960ዎች ወጣቶች ርዝራዦች አንዱ...

የሰሞኑ የ“መኖሪያ ቤቶች” የጨረታ ሽያጭ ምን ዓይነት ሕጋዊ መሠረት አለው?   

በዳዊት ዮሐንስ ሰሞኑን በአዲስ አበባ ከተማ አየር ላይ ከሚንሸረሸሩ ዜናዎች...

ሁለቱ ወጎች፡ ከሰማየ ሰማያት አድርሶ መላሹ ቋንቋ! እስከ በዓሉ ቤርሙዳ

በተክለ ጻድቅ በላቸው ሰማየ ሰማያት አድርሶ መላሹ ቋንቋ! ከሁለት ሦስት ዓመት...

ለትግራይ ክልል ድርቅ ተፈናቃዮች አፋጣኝና ቀጣይነት ያለው ድጋፍ እንዲደረግ ተጠየቀ

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የውጭ ግንኙነትና የሰላም ጉዳዩች ቋሚ...