Friday, June 2, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ስፖርትታላቁ ሩጫ ያዘጋጀው ግማሽ ማራቶን በሐዋሳ ተካሄደ

ታላቁ ሩጫ ያዘጋጀው ግማሽ ማራቶን በሐዋሳ ተካሄደ

ቀን:

የሩጫ ውድድሮችን በማዘጋጀት የሚታወቀው ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ፣ በዓለም አቀፍ ደረጃ ዕውቅና ያገኘውን ግማሽ ማራቶን የሩጫ ውድድር ባለፈው እሑድ ሚያዝያ 15 ቀን 2009 ዓ.ም. በሐዋሳ አካሂዷል፡፡ በውድድሩ የአገር ውስጥና የውጭ አገር አትሌቶች ተሳታፊ እንደነበሩ ከዝግጅት ክፍሉ የተገኘው መረጃ አመልክቷል፡፡

በሐዋሳ ከተማ ዘንድሮ ለስድስተኛ ጊዜ የተካሄደው ይኼው የሐዋሳ ዓለም አቀፍ ግማሽ ማራቶን የሩጫ ውድድር፣ በ2002 ዓ.ም. ተጀምሮ እስከ 2006 ዓ.ም. ድረስ ከዘለቀ በኋላ ለሁለት ተከታታይ ዓመታት ተቋርጦ መቆየቱ ይታወቃል፡፡ ከታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ዝግጅት ክፍል እንደተገለጸው ከሆነ ለሁለት ዓመት ተቋርጦ የቆየው የሐዋሳ ግማሽ ማራቶን ከከተማ አስተዳደሩ ጋር በተደረሰው ስምምነት መሠረት ለሚቀጥሉት ሦስት ተከታታይ ዓመታት እንደሚቀጥል ተገልጿል፡፡

በዚህ መሠረት እሑድ ሚያዝያ 15 ቀን 2009 ዓ.ም. በሐዋሳ በተካሄደው ግማሽ ማራቶን ከተለያዩ ክለቦች በሁሉም ጾታ የተውጣጡ ከ350 በላይ በግል የተወዳደሩትን አትሌቶችን ጨምሮ 21 ኪሎ ሜትር በሚሸፍነው የሩጫ ውድድር ተሳታፊ የነበሩ ሲሆን፣ ሰባት ኪሎ ሜትር በሚሸፍነው የሩጫ ውድድር ደግሞ ከ3,500 በላይ የከተማው ነዋሪዎች ተሳትፈዋል፡፡ ዕድሜያቸው ከ11 ዓመት በታች 750 ሕፃናትም የዝግጅቱ አካል መሆናቸው ጭምር ታውቋል፡፡

በዓለም አቀፍ ደረጃ ዕውቅና በተሰጠው 21 ኪሎ ሜትር ወንዶች ከኢትዮ ኤሌክትሪክ ቢራ ሰቦቃ ርቀቱን 1 ሰዓት 04፡ 09 ሰከንድ አጠናቆ አንደኛ ወጥቷል፡፡ በግል የቀረቡት ገብሬ ሮባ 1 ሰዓት 04፡ 19 እና ጅግሳ ታደሰ 1 ሰዓት 04፡ 22 ሰከንድ በማጠናቀቅ ሁለተኛና ሦስተኛ በመሆን አጠናቀዋል፡፡

በሴቶች መካከል በተደረገው ተመሳሳይ የሩጫ ውድድር ከቤቴል ቲችንግ ሰአዳ ከድር ርቀቱን 1 ሰዓት 16፡ 56 ሰከንድ አንደኛ በመሆን አጠናቃለች፡፡ ውድድሩን ሁለተኛና ሦስተኛ በመሆን ያጠናቀቁት ደግሞ በግል ቀለልቱ ኬያሞ 1 ሰዓት 17፡ 02 ሰከንድ፣ ከካራማ ገዳምነሽ መኳንት 1 ሰዓት 17፡ 10 ሰከንድ ናቸው፡፡

ዝግጅት ክፍሉ በሁለቱም ጾታ ከአንደኛ እስከ አሥረኛ ደረጃ ይዘው ላጠናቀቁ አትሌቶች በአጠቃላይ 100 ሺሕ ብር የገንዘብ ሽልማት የመደበ ሲሆን፣ ለአሸናፊዎቹ እያንዳዳንዳቸው የ20 ሺሕ ብር ሽልማት ተበርክቷል፡፡ ከቻይናው ኮንስትራክሽን ካምፓኒ ሲሲኢሲሲ ጋር በጋራ በተዘጋጀው ውድድር የርቀቱ ክብረ ወሰን የ2017 ዱባይ ማራቶን አሸናፊ ታምራት ቶላ በ2005 ዓ.ም. ያስመዘገበው 1 ሰዓት 02፡ 44 ሰከንድ ተይዞ ሲገኝ፣ በሴቶች ደግሞ ጽጌሬዳ ግርማ በተመሳሳይ 1 ሰዓት 13፡ 19 ሰከንድ እንደተያዘ ይገኛል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የአዛርባጃንን ብሄራዊ ቀን በአዲስ አበባ በድምቀት ተከበረ

የአዛርባጃን ኤምባሲ  የአዛርባጃንን ብሄራዊ ቀን በትላንትናው ዕለት አከበረ። ሰኞ...

የመንግሥትና የሃይማኖት ልዩነት መርህ በኢትዮጵያ

እንደ ኢትዮጵያ ባሉ አገሮች የሃይማኖት ተቋማት አዎንታዊ ሚና የጎላ...

ሐበሻ ቢራ ባለፈው በጀት ዓመት 310 ሚሊዮን ብር የተጣራ ትርፍ ማግኘቱን አስታወቀ

የአንድ አክሲዮን ሽያጭ ዋጋ 2,900 ብር እንዲሆን ተወስኗል የሐበሻ ቢራ...