Friday, September 22, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ሥነ ፍጥረትውኃ ከሁሉ ይልቅ

ውኃ ከሁሉ ይልቅ

ቀን:

ወርቅ፣  አልማዝ፣ ብር፣ መዳብ፣ ነሐስ፣ የደንጊያ ከሰል፣ ብረት፣ ባዚቃ፣ ታኒካ፣ ቆርቆሮ፣ እርሳስ፣ ደንጊያ፣ ዕብነ በረድ፣ ፕላቲን፣ ቤንዝን፣ ጋዝ፣ በጠቅላላው ዘይታዘይት፣ እንጨት፣ ሣር፣ እንስሳት፣ አራዊት፣ አዕዋፍ፣ አንሥርት፤ ይህን የመሰለው ሁሉ የምድር ሀብት ነው፡፡ ከእነዚህ የሚገኘው ዝርዝር ሀብት ግን ተጽፎ የሚያልቅ አይደለም፡፡

ከምድርም ሀብት ዋናዎቹ እህልና ውኃ ናቸው፡፡ ከእህል ይልቅ ውኃ በተለየ አንድ ጊዜ በተፈጥሮ ለሰው ከእግዚአብሔር የተሰጠ ስለሆነ በዚህ ረገድ ያለው ሰብአዊ ትግል ቀላል ነው፡፡

ውኃ  አንድ ጊዜ የተሰጠ ሀብት ነው፡፡ በዓመት በዓመቱ ዘርታችሁ አብቅላችሁ፣ አግኙኝ የሚል አይደለም፡፡ በየምንጩ፣ በየወንዙ፣ በባሕሩ ይገኛል፡፡ በረሃና ጭንቀኛ ሥፍራ ካልሆነ በቀር ውኃ ያለዋጋ ሊገኝ ይቻላል፡፡ ዋጋም ቢያስፈልገው በቀላል ዋጋ የሚገኝ በመሆኑ ሰው እንደ ቀላል ሀብት ይቆጥረዋል፡፡ የውኃም ምግብነት አንሶ ከምድር ሀብት የሚወጣ የንጥር መጠጥ ተጨመረ፡፡

ነገር ግን ከውኃ የበለጠ ሀብት የለም፡፡ ጠቃሚነቱም በመጠጥ ብቻ አይደለም፡፡ ልብስም ገላም ያለውኃ ንጽሕናን አያገኝም፤ መንፈሳዊ ልደትና ንጽሕናም በውኃ ነው፡፡

እንዲሁም በውኃ ውስጥ ያለው ሀብት ብዙ ነው፡፡ ከብዙውም ጥቂቱ ዓሳ፣ ዓሳ ነባሪና፣ አዞ፣ ጉማሬ፣ ሉል ይህንንም የመሰለው ነው፡፡

ሐዲሳዊውም ጥበብ  ከውኃ ጋር የተያያዘ ስለሆነ በዘመናዊ ኢንዱስትሪ ለተገኙት መኪናዎች ሁሉ መንቀሳቀሻቸው ውኃ ነው፡፡ ከላይ እንዳልነው የውኃን አገልግሎት የማይፈልግ የለም፡፡ ተክልና እህል ያለውኃ ሊበቅሉና ሊያፈሩ አይችሉም፡፡

ስለዚህ በውኃ ዳር መሬት ያለው ባለርስት ሁሉ በውኃ አገልግሎት የሚገኘውን ሀብት አለመዘንጋት ነው፡፡ ውኃ ለከንቱ አልተፈጠረም፡፡ በራሱ በኩል ያለውን ጥቅም ሳያጓድል በሌላም ወገን ጠቃሚ ነው፡፡

ወልደጊዮርጊስ ወልደዮሐንስ ‹‹ብልጽግና በግብርና›› (1942)

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ባለሙያዎች ኮሚሽን ሪፖርት ምን ይዟል?

ለአሜሪካ ድምፅ አማርኛ ዝግጅት የስልክ አስተያየት የሰጡ አንድ የደንበጫ...

መንግሥት በአማራ ክልል ለወደሙ የአበባ እርሻዎች ድጋፍ እንዲያደርግ ተጠየቀ

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በአማራ ክልል የተፈጠረው ግጭትና አለመረጋጋት በቢዝነስ...

አምናና ዘንድሮ!

እነሆ መስከረም ጠብቶ በአዲስ መንፈስ ተሞልተን መንገድ ጀምረናል። ‹‹አዲስ...