Friday, September 29, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ኪንና ባህል11ኛው አዲስ ኢንተርናሽናል ፊልም ፌስቲቫል

11ኛው አዲስ ኢንተርናሽናል ፊልም ፌስቲቫል

ቀን:

በስደት፣ በወጣቶች ሥነ ተዋልዶ ጤና፣ በአካባቢ ደኅንነት እንዲሁም ሌሎችም ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች ዙሪያ የሚያጠነጥኑ ዘጋቢ ፊልሞችን የሚያስተናግደው አዲስ ኢንተርናሽናል ፌስቲቫል፣ 11ኛ ዙር ከሚያዝያ 20 እስከ 25 ቀን 2009 ዓ.ም. ይካሄዳል፡፡

ባለፉት ዓመታት የአገር ውስጥና የውጪም ዘጋቢ ፊልሞችን በማቅረብ የሚታወቀው ፌስቲቫሉ፣ ዘንድሮ የሚካሄደው በጣልያን ባህል ማዕከልና በአገር ፍቅር ቴአትር ነው፡፡ የፌስቲቫሉ አዘጋጅ ኢኒሽየቲቭ አፍሪካ ለሪፖርተር በላከው መግለጫ እንዳስታወቀው፣ ሚያዝያ 20 በጣልያን ባህል ማዕከል የሚከፈተው ፌስቲቫሉ ከ30 በላይ ዘጋቢ ፊልሞች ያስተናግዳል፡፡

ባለፉት አሥር ዓመታት በፌስቲቫሉ ከ400 በላይ ፊልሞች በባህል ማዕከላት፣ ዩኒቨርሲቲዎችና በክልል ከተሞች የታየ ሲሆን፣ ዘንድሮም ለኦስካር ሽልማት ዕጩ የሆኑ ፊልሞችን ጨምሮ በርካታ ፊልሞች ይቀርባሉ፡፡ ተመልካቾች ከፊልም አዘጋጆች ጋር ጥያቄና መልስ ያደርጋሉ፡፡ ከፊልም ሥራ ጋር በተያያዙ ርዕሰ ጉዳዮች ውይይት የሚደረግባቸው ወርክሾፖችም አሉ፡፡ በዘንድሮው ፌስቲቫል ተሞክሯቸውን ከሚያካፍሉ ፊልም ሠሪዎች መካከል የ‹‹ኤ ቢሊየን ላይቭስ›› ፊልም አዘጋጅ አሮን ቢበርትና የ‹‹ቦይ 23›› አዘጋጅ ቤሊሳርዮ ፍራንካ ይገኙበታል፡፡

በአገርኛ ጉዳዮች ዙሪያ ከተሠሩ ዘጋቢ ፊልሞች መካከል የመኮንን ሚካኤል ‹‹ሔቨን ኤንድ ኧርዝ››፣ የኪዊኖ ፒኔሮ ‹‹ሮሪንግ አቢስ›› እና የቬንቹራ ዱራል ‹‹ዘ ዋይልድ ይርስ›› ይጠቀሳሉ፡፡ አምና የኦስካር ሽልማት ዕጩ ከነበሩ ፊልሞች መካከል ‹‹ፋየር አትሲ›› እና ‹‹ዘ ሶልት ኦፍ ዘ ኧርዝ›› እንደሚታዩም በመግለጫው ተመልክቷል፡፡

***

ጉማ የፊልም ሽልማት

የሚሼል ፓፓቲከስን ‹‹ጉማ›› ፊልም መጠሪያው ያደረገው ጉማ ፊልም አዋርድስ ላለፉት ሦስት ዓመታት በዘርፉ የላቁ ባለሙያዎችን በመሸለም ይታወቃል፡፡ ጉማ የፊልም ሽልማት አራተኛ ዙር ሚያዝያ 23 ቀን 2009 ዓ.ም. በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር እንደሚካሄድ አዘጋጆቹ ለሪፖርተር በላኩት መግለጫ አስታውቀዋል፡፡

አምና ለዕይታ ከበቁ 120 ፊልሞች መካከል 71 ፊልሞች በውድድሩ ለመሳተፍ ቢመዘገቡም፣ ለውድድሩ የተቀመጠውን ደረጃ ባለመመጠንና የተሟላ መረጃ ባለማቅረብ ውድቅ የተደረጉ ፊልሞች አሉ፡፡ በወድድሩ ለመሳተፍ ብቁ የሆኑት 18 ፊልሞች በዳኞች ከተመዘኑ በኋላ የድምፅ ብልጫ ያገኙት ለሽልማት ይበቃሉ፡፡

ውድድሩ የዕድሜ ዘመን ሽልማትን ጨምሮ በ16 ምድቦች እንደሚካሄድ አዘጋጆቹ አመልክተዋል፡፡ በፊልም አዘጋጁ ዮናስ ብርሃነ መዋ የተመሠረተው ጉማ፣ በፊልም ጽሑፍ፣ ዝግጅት፣ አርትኦት፣ ትወናና ሌሎችም ዘርፎች የተሻለ ብቃት ላሳዩ ባለሙያዎች ዕውቅና በመስጠት ለዘርፉ አስተዋጽኦ ከሚያበረክቱ ውድድሮች መካከል ይጠቀሳል፡፡ ፊልም ሠሪዎችን በማበረታታትና የኢትዮጵያ ፊልሞችን ተደራሽነት በማስፋትም የድርሻውን እየተወጣ ይገኛል፡፡

****

‹‹መንገደኛ››

የሥነ ሕዝብና የማኅበራዊ ሳይንስ ባለሙያው ዮርዳኖስ አልማዝ ሰይፉ፣ በስደተኞች ሕይወት ዙሪያ ያተኮረ ‹‹መንገደኛ›› የተሰኘ መጽሐፍ ለንባብ አብቅቷል፡፡ መጽሐፉ ሚያዝያ 16 ቀን 2009 ዓ.ም. በ11፡30 በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር በልዩ ልዩ ጥበባዊ መሰናዶዎች ይመረቃል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የአማራ ክልል ወቅታዊ ሁኔታ

እሑድ ጠዋት መስከረም 13 ቀን 2016 ዓ.ም. የፋኖ ታጣቂዎች...

ብሔራዊ ባንክ ለተመረጡ አልሚዎች የውጭ አካውንት እንዲከፍቱ ለመጀመሪያ ጊዜ የፈቀደበት መመርያና ዝርዝሮቹ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የውጭ ምንዛሪ አጠቃቀምንና ተያያዥነት ያላቸው ጉዳዮችን...

እነ ሰበብ ደርዳሪዎች!

ከሜክሲኮ ወደ ዓለም ባንክ ልንጓዝ ነው። ሾፌርና ወያላ ጎማ...