Wednesday, March 22, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊአራት ሚሊዮን የሚጠጉ ተንቀሳቃሽ ስልኮች ከጥቅም ውጪ ሊሆኑ ነው

አራት ሚሊዮን የሚጠጉ ተንቀሳቃሽ ስልኮች ከጥቅም ውጪ ሊሆኑ ነው

ቀን:

በዳዊት እንደሻው

በደንበኞች እጅ የሚገኙ ወደ አራት ሚሊዮን የሚጠጉ ተንቀሳቃሽ ስልኮች፣ ኢትዮ ቴሌኮም ተግባራዊ ያደርገዋል ተብሎ በሚጠበቀው አዲስ ወደ አገር ውስጥ የሚገቡ የተንቀሳቃሽ ስልኮች የመመዝገቢያ ሥርዓት አማካይነት ከጥቅም ውጪ እንደሚሆኑ ተገለጸ::

ከዚህ ጋር በተያያዘ የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር መመርያ ያዘጋጀ ሲሆን፣ የአዲሱን ሥርዓት ተግባራዊነት ያግዛል ተብሏል::

ከአንድ ወር በፊት ተግባራዊ ይሆናል ተብሎ ሲጠበቅ የነበረው ይኼ አዲስ ሥርዓት ከጥቅም ውጪ የሚሆኑትን አራት ሚሊዮን ስልኮችን እንዴት መተካት አለባቸው? በሚለው ጉዳይ በኢትዮ ቴሌኮምና በአገር ውስጥ ሞባይል አምራቾች መካከል ሲደረግ የነበረው ድርድር መቋጨት ባለመቻሉ፣ ተግባራዊነቱ ሊዘገይ እንደቻለ ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው የሪፖርተር ምንጮች ገልጸዋል::

በዚህም መሠረት ተንቀሳቃሽ ስልካቸው ከጥቅም ውጪ የሚሆንባቸው ደንበኞች ከጥቅም ውጪ የሚሆነው ስልካቸው በሌላ ስልክ እንደሚቀየርላቸው ተነግሯል::ደንበኞች የያዟቸው ስልኮች ዓይነት ግምት ውስጥ ሳይገባ በሌላ ተንቀሳቃሽ ስልኮች እንዲቀይሩ ይደረጋል ተብሏል::

በኢትዮ ቴሌኮምና በአገር ውስጥ ተንቀሳቃሽ ስልኮች አምራቾች መካከል ሲደረግ የነበረው ድርድር የዘገየው በዚሁ ወጪ ምክንያት እንደሆነ ተገልጿል::በዋናነት ስልካቸው ከጥቅም ውጪ ለሚሆንባቸው ደንበኞች ተቀያሪ ስልኮች በሚሰጡበት ጊዜ፣ የተቀያሪ ስልኮቹን ወጪ ማን ይሸፍነው? የወጪ ክፍፍሉ በሁለቱ አካላት መካከል በምን ያህል መጠን መሆን አለበት? የሚለው ድርድር አፈጻጸሙን እንዳዘገየው እነዚሁ ምንጮች ይገልጻሉ::

እስካሁን ስምምነት ላይ እንዳልተደረሰና ኢትዮ ቴሌኮም 55 በመቶ ወጪውን እንዲሸፍን፣ አምራቾች ደግሞ ቀሪውን ወጪ እንዲሸፍኑ የሚል አማራጭ እንደቀረበ ለድርድሩ ቅርበት ያላቸው ምንጮች ለሪፖርተር ተናግረዋል::

 

የዚህ ድርድር መዘግየት ለመመርያው አለመፅደቅ ምክንያት እንደሆነ ምንጮች ይናገራሉ::

‹‹መመርያው ከመፅደቁ በፊት በመጀመሪያ መዘጋጀት ያለብን ብዙ ጉዳዮች አሉ፤›› ሲሉ ሪፖርተር ያናገራቸው የሚኒስቴሩ አንድ የሥራ ኃላፊ ይገልጻሉ::

በአሁን ጊዜ በኢትዮጵያ ወደ 14 የሚጠጉ የተንቀሳቃሽ ስልኮች አምራቾች እንዳሉ ይታወቃል::በአገር ውስጥ የተንቀሳቃሽ ስልኮች አምራቾች ማኅበር አማካይነት በተደረገ ጥናት መሠረት፣ 65 በመቶ የሚሆነው የኢትዮጵያ የተንቀሳቃሽ ስልኮች ገበያ በሕገወጥ መንገድ ከጎረቤት አገሮች በሚገቡ ስልኮች ቁጥጥር ሥር ነው::ቀሪው 31 በመቶ የሚሆነው ብቻ በአገር ውስጥ አምራቾች ተይዟል::ቀሪው ደግሞ በሕጋዊ መንገድ የሚገቡ ስልኮች ይዘውታል::

ካሉት 14 የአገር ውስጥ አምራቾች እንደ ቴክኖ ሞባይል ያሉት ከአገር ውስጥ ገበያ ባለፈ ወደ ተለያዩ የአፍሪካ አገሮች ምርቶችን መላክ ጀምረዋል::ከዚህም ጋር በተያያዘ በዚህ ዓመት ብቻ ድርጅቱ 40 ሚሊዮን ዶላር ያህል ገቢ ከወጪ ንግድ እንደሚያስገባ ይጠበቃል::

ባለፉት ስድስት ወራት ውስጥ የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን 83 ሚሊዮን ብር የሚጠጉ በሕገወጥ መንገድ የገቡ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች መያዙን መግለጹ ይታወሳል::

የተንቀሳቃሽ ስልኮች አገልግሎት በኢትዮጵያ ከ18 ዓመታት በፊት በ36 ሺሕ መስመሮች በአዲስ አበባ የተጀመረ ሲሆን፣ በአሁኑ ጊዜ ቁጥሩ ወደ 47 ሚሊዮን እንደደረሰ ይታወቃል::

ባለፈው ዓመት በተደረገ ጥናት 25 ሚሊዮን የሚጠጉ ተንቀሳቃሽ ስልኮች በተጠቃሚዎች እጅ እንደሚገኙ ታውቋል::ከእነዚህም ውስጥ ቴክኖ፣ ኖኪያ፣ ሳምሰንግ እንዲሁም ሁዋዌ የተባሉ የተንቀሳቃሽ ስልክ ምርቶች በብዛት ከአንድ እስከ አራት ያለውን ደረጃ ይዘው ይገኛሉ::

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

[ክቡር ሚኒስትሩ ከሚያከብሯቸው አንድ የቀድሞ ጉምቱ ፖለቲከኛ ስልክ ተደውሎላቸው እያወሩ ነው]

አንዳንድ ነገሮች ቢያሳስቡኝ ነው ቀጠሮ ሳልይዝ ላወራህ የፈለኩት ክቡር...

የትግራይ ክልል የሽግግር አስተዳደር ምሥረታና የሰላም ስምምነቱ ሒደት

በትግራይ ክልል ጊዜያዊ የሽግግር መንግሥት ለመመሥረት ደፋ ቀና እየተባለ...

ጥራዝ ነጠቅነት!

ከሜክሲኮ ወደ ጀሞ እየሄድን ነው፡፡ የተሳፈርንበት አሮጌ ሚኒባስ ታክሲ...

አወዛጋቢነቱ የቀጠለው የአዲስ አበባ የጤፍ ገበያ

ሰሞኑን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በጤፍ የተከሰተውን የዋጋ ንረት...