Sunday, October 1, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ስፖርትበአፍሪካ እግር ኳስ ተሳትፎው 50ኛ ዓመት ላይ የሚገኘው ቅዱስ ጊዮርጊስ ምድብ ታወቀ

በአፍሪካ እግር ኳስ ተሳትፎው 50ኛ ዓመት ላይ የሚገኘው ቅዱስ ጊዮርጊስ ምድብ ታወቀ

ቀን:

በአፍሪካ ክለቦች ሻምፒዮና ተሳታፊነት 50ኛ ዓመቱን እያከበረ የሚገኘው ቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ማኅበር በዘንድሮው የአፍሪካ ሻምፒዮንስ ሊግ ምድቡ ይፋ ሆነ፡፡

የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን (ካፍ) በሳምንቱ አጋማሽ ጽሕፈት ቤቱ ከሚገኝበት ከካይሮ እንዳስታወቀው፣ ቅዱስ ጊዮርጊስ በምድብ ሐ ከዓምናው ሻምፒዮን ማሜሎዲ ሰንዳውንስ (ደቡብ አፍሪካ)፣ ኤስፔራንስ ደ ቱኒዝ (ቱኒዝያ) እና ኤኤስ ቪታ (ዲሞክራቲክ ኮንጎ) ጋር ተመድቧል፡፡

ከ21ኛው ቶታል ካፍ ሻምፒዮንስ ሊግ፣ ከ16ቱ የመጨረሻ ምድብተኞች መካከል ቅዱስ ጊዮርጊስን ጨምሮ አራት ክለቦች በአስደናቂ ሁኔታ ለመጀመሪያ ጊዜ የ20 ዓመት ታሪክ ባለው የአፍሪካ ሻምፒዮንስ ሊግ መካተት ችለዋል፡፡ እነሱም ፌሬቪያሪዮ ቢዬራ (ሞዛምቢክ)፣ ዛናኮ (ዛምቢያ) እና ካፕስ ዩናይትድ (ዚምባቡዌ) ናቸው፡፡ ከ16ቱ ክለቦች ዘጠኙን የሰሜን አፍሪካ አገሮች ተቆጣጥረውታል፡፡

በወጣው ፕሮግራም መሠረት የመጀመርያዎቹ ግጥሚያዎች የሚከናወኑት ከግንቦት 4 እስከ 6 ይሆናል፡፡ ጊዮርጊሶች የመጀመሪያውን ጨዋታ በደቡብ አፍሪካ እንደሚያካሂዱ ታውቋል፡፡

ቅዱስ ጊዮርጊስ ለምድብ የበቃው የሲሼልሱን ኮትዲዮርን ባጠቃላይ ውጤት 5 ለ0፣ እንዲሁም የኮንጎውን ኤሲ ሊዮፓርድስን ባጠቃላይ ውጤት 3 ለ1 በመርታት ነው፡፡

ጊዮርጊስ በአፍሪካ ሻምፒዮንስ ሊግ እስካሁን ያስመዘገበው ውጤት አንደኛው ዙር ድረስ የዘለቀበት ተጠቃሹ ነው፡፡ ምድብተኞቹ ሰንደውንስ በሊጉ 10 ጊዜ ተሳትፎ አንዴ ዋንጫ ሲያነሳ፣ ኤስፔራንስ 21 ጊዜ ተሳትፎ ሁለቴ ዋንጫን አግኝቷል፡፡ ቪታም በ14 ጊዜ ተሳትፎው አንዴ ዋንጫ ጨብጧል፡፡

ቅዱስ ጊዮርጊስ ከ52 ዓመት በፊት በተጀመረው የአፍሪካ ክለቦች እግር ኳስ ሻምፒዮና ፍጻሜ ግማሽ የደረሰበት በታላቁ ውጤትነት ተመዝግቦለታል፡፡ በ1959 ዓ.ም. የዑጋንዳና የግብፅ (እስማኤሊያ) ክለቦች አሸንፎ በፍጻሜው ግማሽ ከዛየሩ አንግበልርት ነበር የተጋጠመው፡፡ ኪንሳሻ ላይ 3 ለ1 ተሸንፎ፣ በመልሱ ጨዋታ አዲስ አበባ 2 ለ1 ቢረታም በአንድ ግብ ልዩነት አንግበልርት ፍጻሜ ደርሷል፡፡ ለፍጻሜ የቀረበው የጋናው አሻንቲ ኮቶኮ ፎርፌ በመስጠቱ ዋንጫውን አግኝቷል፡፡

ከኢትዮጵያ ክለቦች በአፍሪካ ክለቦች ሻምፒዮና በመካፈል በ1957 እና 1958 ዓ.ም. ቀዳሚ የነበሩት የድሬዳዋዎቹ ጥጥ ማኅበር (ኮተን) እና ኢትዮ ሲሜንት እንደነበሩ ይታወሳል፡፡

ድልድሉ

ምድብ ሀ፡ ፌሮቪያሪዮ ቤይራ፣ አልሜሪክ፣ አልሂላል፣ ኢቶሌ ደ ሳህል

ምድብ ለ፡ ካፕስ ዩናይትድ፣ አህሊ ትሪፖሊ፣ ዩኤስ ኤም አልጀር፣ ዛማሌክ

ምድብ ሐ፡ ቅዱስ ጊዮርጊስ፣ ኤኤስ ቪታ፣ ኤስፔራንስ፣ ማሜሎዲ ሰንዳውንስ

ምድብ መ፡ ዛናኮ፣ ኮተን ስፖርት፣ ውያድ ካዛብላንካ፣ አል አህሊ 

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ተመድንና ዓለም አቀፋዊ ሕግን ከእነ አሜሪካ አድራጊ ፈጣሪነት እናድን!

በገነት ዓለሙ በእኔ የተማሪነት፣ የመጀመርያ ደረጃ ተማሪነት ጊዜ፣ የመዝሙር ትምህርት...

የሰላም ዕጦትና የኢኮኖሚው መንገራገጭ አንድምታ

በንጉሥ ወዳጅነው ፍራንክ ቲስትልዌይት የተባሉ አሜሪካዊ ጸሐፊ ‹‹The Great Experiment...

ድህነት የሀብት ዕጦት ሳይሆን ያለውን በአግባቡ ለመጠቀም አለመቻል ነው

በአንድነት ኃይሉ ድህነት ላይ አልተግባባንም፡፡ ብንግባባ ኖሮ ትናንትም ምክንያት ዛሬም...