Wednesday, September 28, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - Advertisement -
  - Advertisement -
  ስፖርትየመረብ ኳስ የደረጃ ሁለት የአሠልጣኞች ሥልጠና ተከናወነ

  የመረብ ኳስ የደረጃ ሁለት የአሠልጣኞች ሥልጠና ተከናወነ

  ቀን:

  የኢትዮጵያን መረብ ኳስ ውጤታማ ለማድረግ የሚረዳ የአሠልጣኞች ሥልጠና በኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴና በብሔራዊ ፌዴሬሽኑ፣ በዓለም አቀፍ ፌዴሬሽንና በኦሊምፒክ ሶሊዳሪቲ ትብብር ተከናወነ፡፡

  የብሔራዊ ኦሊምፒክ ኮሚቴ አዲሱ ሥራ አስፈጻሚ ቦርድ ሥራውን በጀመረ ለመጀመሪያ ጊዜ፣ ከሚያዝያ 17 ቀን እስከ ሚያዝያ 21 ቀን 2009 ዓ.ም. በትብብር ባዘጋጀው የአሠልጣኞች ሥልጠና ላይ ከዘጠኝ ክልሎችና ሁለት የከተማ አስተዳደሮች የተውጣጡ 30 አሠልጣኞች ተሳትፈውበታል፡፡ በሥልጠናው በፕሪሚየር ሊግ ክለቦች የያዙ አሠልጣኞች ይገኙበታል፡፡

  “በየጊዜው አሠልጣኞችን ማሠልጠን ማለት ከወቅቱ የስፖርት ሳይንስ ዕድገት ጋር ባለሙያዎች ራሳቸውን እንዲያጣጥሙና ለውጤታማነት እንዲተጉ ያግዛቸዋል፤” በማለት በሥልጠናው ላይ የተናገሩት፣ የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ፕሬዚዳንት ዶ/ር አሸብር ወልደጊዮርጊስ ናቸው፡፡

   ሥልጠናውን በጋራ የሰጡት የዓለም አቀፍ የመረብ ኳስ ፌዴሬሽን ኮርስ ዳይሬክተር ቡልጋሪያዊው ጄኮቭ ፓቫሎቭና ኢትዮጵያዊው የአሠልጣኞች ኢንስትራክተር አቶ ዓለማየሁ ሸዋታጠቅ ናቸው፡፡

  ሥልጠናው በአገር ውስጥ፣ በአህጉርና ዓለም አቀፍ የመረብ ኳስ ውድድሮች ትልቅ አቅም በመፍጠር ወደ ውጤታማነት ጎዳና ለመጓዝ መደላድል ይፈጥራልም ተብሏል፡፡

  - Advertisement -

  ይመዝገቡ

  spot_img
  spot_img

  ተዛማጅ ጽሑፎች
  ተዛማጅ

  በቤንዚንና ነጭ ናፍጣ ላይ ጭማሪ ተደረገ

  ከዛሬ መስከረም 18 ቀን 2015 ዓም እኩለ ሌሊት ጀምሮ...

  ‹‹ለሰላምና ለዕርቅ መሸነፍ የለብንም›› ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ

  የሰው ልጅ ጠብን በዕርቅ፣ በደልን በይቅርታ፣ ድህነትን በልማት፣ ክህደትን...

  መፍትሔ አልባ ጉዞ የትም አያደርስም!

  ኢትዮጵያ ችግሮቿን የሚቀርፉ አገር በቀል መፍትሔዎች ላይ ማተኮር ይኖርባታል፡፡...

  ጦርነቱና ውስጣዊ ችግሮች

  መስከረም 14 ቀን 2015 ዓ.ም. የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት ባወጣው...