Friday, June 9, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናየእስራኤል የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ የዲፕሎማሲ አጭር ሥልጠና ሊሰጡ ይመጣሉ

የእስራኤል የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ የዲፕሎማሲ አጭር ሥልጠና ሊሰጡ ይመጣሉ

ቀን:

የእስራኤል መንግሥት የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አማኑኤል ናህሾን፣ ለኢትዮጵያ ዲፕሎማቶችና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሠራተኞች በፐብሊክ ዲፕሎማሲ ላይ አጭር ሥልጠና ሊሰጡ እንደሆነ ታወቀ፡፡

የእስራኤል የሕግ ባለሙያዎች ማኅበር አባልና ታዋቂ ዲፕሎማት የሆኑት የአገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃለ አቀባይ አማኑኤል ናህሾን፣ ሐሙስ ሚያዚያ 19 ቀን 2009 ዓ.ም. በኢትዮጵያ የአንድ ቀን ቆይታ ሲያደርጉ ከከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣናት ጋር ይገናኛሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

በኢትዮጵያ የእስራኤል አምባሳደር ወይዘሮ በላይነሽ ዚቫድያ ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ በእስራኤል የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የቃል አቀባይ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ከፍተኛ ሥልጣን ነው፡፡ ቃል አቀባዩ ኢትዮጵያ ሲመጡም በሁለቱ አገሮች የሁለትዮሽ ግንኙነት፣ በአካባቢው የፀጥታ ሁኔታና ተያያዥ ጉዳዮች ላይ ከመንግሥት ባለሥልጣናት ጋር ይመክራሉ ብለዋል አምባሳደሯ፡፡

ቃል አቀባዩ በአንድ ቀን ውሏቸው በፐብሊክ ዲፕሎማሲ፣ በተለይ የቀውስ ጊዜ ዲፕሎማሲ ከአሁኑ የዲጅታል ዘመን ዲፕሎማሲ ጋር እንዴት መጣጣም እንዳለበት፣ እንዲሁም ቀጣዩ ዲፕሎማሲ (The Future Diplomacy) በመሳሰሉ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ተሞክሯቸውን ለኢትዮጵያውያን ዲፕሎማቶች ያካፍላሉ ተብሏል፡፡

መረጃዎች እንደሚጠቁሙት፣ ቃል አቀባዩ ሚስተር ናህሾን  እ.ኤ.አ. ከ1986 ጀምሮ በተለያዩ የመንግሥት ከፍተኛ ኃላፊነት ያገለገሉና ነባር ዲፕሎማት ናቸው፡፡ በተለይ ደግሞ በአውሮፓ ኅብረት ልዩ ልዑክ፣ በጀርመን አምባሳደር፣ በተለያዩ የመንግሥት ተቋማት ዳይሬክተር በመሆን እስራኤልን ማገልገላቸው ተገልጿል፡፡

እ.ኤ.አ. ከ2014 ጀምሮ የአገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ሆነው እየሠሩ ይገኛሉ፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ