የኢትዮጵያ ዱር እንስሳት ልማትና ጥበቃ ባለሥልጣን፣ሰሞኑን በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ያስታወቀው፡፡ ሦስቱ ፓርኮችና መጠለያ ህልውናቸው ፈተና ላይ የወደቀው በየአካባቢው የሕዝብ ቁጥር ከፍተኛ መሆን፣ የዱር እንስሳት ሕገ ወጥ አደን፣ ሕገ ወጥ ሠፈራና የእርሻ ሥራ መበራከቱ ነው፡፡ የባለሥልጣኑ የብሔራዊ ፓርኮችና የዱር እንስሳት መጠለያ ማስተባበሪያ ዳይሬክተር አቶ አረጋ መኮንን ለኢዜአ እንደገለጹት፣ ብሔራዊ ፓርኮች የተጋረጠባቸውን አደጋ ለመቅረፍ ባለሥልጣኑ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ቅንጅታዊ አሠራር በመፍጠር መከላከሉ ላይ እየሠራ ነው።‹‹ከአካባቢ ጥበቃ ሥራ ጋር ቅርበት ያላቸው ተቋማትን በማግባባት ሁሉን አቀፍ የሆነ ግብረ ኃይል በማቋቋም ፓርኮቹ እንዲያገግሙ እየተሠራ ነው፤›› ብለዋል፡፡