በዘለቀ ረዲ (ኢ/ር) ተጽፎ በቅርቡ ለንባብ የበቃው መጽሐፍ ‹‹የ21ኛው ክፍለ ዘመን መሳፍንትና ኢትዮጵያን እንደ አገር የማስቀጠል ፈተና›› ይሰኛል፡፡ ደራሲው በቅንጅትና በአንድነት የፖለቲካ ፓርቲዎች ተሳትፏቸው የሚታወቁ ሲሆን፣ በመጽሐፉ መግቢያ እንዳሠፈሩት፣ ኢትዮጵያ አሁን የምትገኝበትን አጣብቂኝና የተጋረጠባትን እንደ አገር የመቀጠል ፈተና የተመረኮዘ መጽሐፍ ነው፡፡ በ14 ምዕራፍ የተከፋፈለው መጽሐፍ፣ በታሪክ ወደኋላ በመመለስና የአገሪቱን ነባራዊ ሁኔታ በመዳሰስ፣ ኢትዮጵያን እንደ አገር ለማስቀጠል ምን መደረግ አለበት? የሚለውን ጥያቄ ለመመለስ ይሞክራል፡፡ በኢትዮጵያ ለዴሞክራሲ ማጣት ምክንያት የሆኑትን የሚፈትሽና የአገሪቱን መዳኢ ዕድል የሚያሳይ መሆኑን ያዕቆብ ወልደማርያም (ዶ/ር) በመጽሐፉ ሽፋን አስፍረዋል፡፡ 236 ገጽ ያለው መጽሐፉ፣ በ75 ብር ከ99 ይሸጣል፡፡