Tuesday, October 4, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - Advertisement -
  - Advertisement -
  ስፖርትየቦክስ ስፖርት አንድ ዕርምጃ ወደፊት

  የቦክስ ስፖርት አንድ ዕርምጃ ወደፊት

  ቀን:

  በወጣቶችና ስፖርት ሚኒስቴር ድጋፍ እየተደረገላቸው የሚተዳደሩ ቁጥራቸው ከ22 በላይ የሆኑ ፌዴሬሽኖች ይገኛሉ፡፡ ከእነዚህ መካከል ግን የኅብረተሰቡን ፍላጎትና ራስን በራስ ማስተዳደር፣ ተመልካቾችንና ተተኪዎች ማፍራት እንዲሁም በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ ለመሆን የተሳካላቸው ቁጥራቸው ከሦስት የማይበልጡ ናቸው፡፡ ምንም እንኳ አሁን ላይ የተመልካቾች ፍላጎት ወደ እግር ኳሱና አትሌቲክሱ ቢያዘነብልም፣ ካለባቸው ችግር ለመውጣትና ወደ ኅብረተሰቡ ለመግባት የሚንቀሳቀሱም ለመኖራቸው የኢትዮጵያ ቦክስ ፌዴሬሽንን መጥቀስ ይቻላል፡፡

  ቀደም ባሉ ጊዜያት በስታዲየሞች በመታደም ጠጠር መጣያ እስኪጠፋ ድረስ ለሁሉም ስፖርት ዓይነቶች ድጋፍ ሲያደርጉ የነበሩትን ተመልካቾች ለመመለስ ጥረት እያደረጉ ያሉ ሌሎችም ፌዴሬሽኖች እንዳሉ ይታመናል፡፡

  በ1954 ዓ.ም. እንደተመሠረተ የሚነገርለት የኢትዮጵያ ቦክስ ፌዴሬሽን ዓለም አቀፍ ይዘት ያላቸውን ውድድሮች በማዘጋጀት ቀድሞ የነበረውን የስፖርቱ ተመልካች እንዲሁም ተተኪ ቦክሰኞች ለማምጣት እየተንቀሳቀሰ ይገኛል፡፡

  በብሔራዊ ፌዴሬሽኑ አዘጋጅነት መጋቢት 30 ቀን 2009 ዓ.ም. በኢንተር ኮንትኔታል ሆቴል ለመጀመሪያ ጊዜ በከፊል ፕሮፌሽናል (ሰሚ ፕሮፌሽናል) የቦክስ ሻምፒዮና አዘጋጅቷል፡፡ በሻምፒዮናው በሁለቱም ፆታ በተለያዩ የዕድሜ እርከን የሚሳተፉ ተወዳዳሪዎችን ያካተተ ውድድርም ነበር፡፡ ከ51 እስከ 75 ኪሎ ግራም የዕድሜ እርከን በተወዳዳሪዎች መካከል የነበረው መሸናነፍ ፉክክር ተመልካችን ያረካ ሆኖ ተጠናቋል፡፡

  ‹‹ከቀበሌ ጀምሮ እስከ ፌዴራል ድረስ ስፖርተኞችንና በስፖርቱ መሳተፍ ፍላጎት ያላቸውን ወጣቶችን ለማነቃቃት የተዘጋጀ ውድድር ነው›› በማለት የፌዴሬሽኑ የሥራ ሒደት ዳይሬክተር አቶ ጳውሎስ ማዳ ተናግረዋል፡፡

  በኢንተር ኮንትኔንታል በተደረገው የቦክስ ሻምፒዮና ከቀኑ 10 ሰዓት ጀምሮ በሩን ክፍት ያደረገው ፌዴሬሽኑ፣ ከ1,000 እስከ 3,000 ብር እየከፈሉ ውድድሩን የተከታተሉ  ተመልካቾች በርካቶች እንደነበሩም ተገልጿል፡፡ ከዚህም ባሻገር ውድድሩን በቦታው ተገኝተው መመልከት ላልቻሉት የስፖርቱ ተመልካቾች በቴሌቪዥን መስኮት በቀጥታ እንዲመለከቱ በማድረግ የብዙዎቹን የስፖርቱ አፍቃሪዎችን ጥሩ አጋጣሚ  የፈጠረላቸው ስለመሆኑ ጭምር ፌዴሬሽኑ አስታውቋል፡፡

  በፌዴሬሽኑ ላይ ያሉትን መሠረታዊ ችግሮች ለመፍታት ባለሀብቶችን ወደ ስፖርቱ እንዲሳቡ ጥሩ አጋጣሚም እንደነበረ ገለፁት የፌዴሬሽኑ ፕሬዚዳንት አቶ ኢያሱ መሳይ፣ ፌዴሬሽኑ የሪንግ፣ የመጫወቻ ቦታ ችግር፣ የገንዘብ እንዲሁም የአደረጃጀት ችግሮች ሁሌም ሲያቀርብ መቆየቱን ግን አልሸሸጉም፡፡

  ከ50 ዓመታት በላይ ያገለገለው የቦክስ መወዳደሪያ ሪንግ የይቀየር ጥያቄና በምን ዓይነት መንገድ ወደ አገር ውስጥ ማስገባት እንደሚቻል ሲያከራክር የቆየና ለፌዴሬሽኑም የሪንግ ችግርን ለመፍታት የአገር ውስጥ አምራቾችን ሳይቀር ሲያነጋግር  እንደነበረ የቅርብ ጊዜ ትውስታ ነው፡፡

  ሐሙስ መጋቢት 28 ቀን በኢንተር ኮንቲኔታል በተሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ፣ ፌዴሬሽኑ በቀጣይ ሁሉም ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች የራሳቸው የመጫወቻ ሪንግ እንደሚኖራቸውም ፕሬዚዳንቱ አቶ ኢያሱ  አብራርተዋል፡፡ ፌዴሬሽኑ የክለቦች ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተመናመነ መምጣቱ እንዳሰጋው ገልጾ፣ የዓለም አቀፍ ይዘት ያላቸው ውድድሮችን በመፍጠር ቁጥራቸውን እንዲጨምር ማድረግ እንደሚያስፈልግና ለዚያ ደግሞ የሚመለከታቸው አካላት የበኩላቸውን እንደሚገባ ተናግሯል፡፡

  ቅዳሜ በተደረገው ግጥሚያ፣ የብዙዎቹን ቀልብ የገዛው የ75 ኪሎ ግራም ውድድር ነበር፡፡ የማራቶን ክለብ ቦክሰኛ (የቀድሞ ክለቡ ኒያላ) ገዛኸኝ ሮባ በቅጽል ስሙ ኮንሶና የአዲስ አበባ ፖሊስ መክብብ ከማል እስከ አምስት ዙር ባደረጉት ከፍተኛ ፉክክር መክብብ 147 ነጥብ ድምር ውጤት በማምጣት የውድድሩ አሸናፊ ሲሆን፣ ገዛኸኝ 138 ጠቅላላ ድምር ውጤት ሁለተኛ በመሆን አጠናቋል፡፡

  በዚህም መሠረት አንደኛ ለወጣው የ50 ሺሕ ብር ሽልማት ሲበረከትለት፣ ሁለተኛ ሆኖ ላጠናቀቀው ደግሞ የ30 ሺሕ ብር ሽልማት ተበርክቶለታል፡፡

  በዓለምና አገር አቀፍ ሻምፒዮናዎች ተፎካካሪ ሆኖ ለመቅረብ ከጥር 2001 ዓ.ም. ጀምሮ አዲስ የውድድር ሥርዓት የተቀረፀ መሆኑና የክለቦችን ውድድር የበለጠ በማስፋፋት ተመሳሳይ ውድድሮችን ቁጥር ማብዛት ሁነኛ አማራጭ እንደሆነ የፌዴሬሽኑ ፕሬዚዳንት ተናግረዋል፡፡ የቦክስ ስፖርት በዓለም በቤት ውስጥ ከሚደረጉ ዓለም አቀፍ ውድድሮች ተጠቃሽ መሆኑ ይታወቃል፡፡

  - Advertisement -

  ይመዝገቡ

  spot_img
  spot_img