Sunday, June 16, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -

ስፖርትዶፒንግና የስፖርተኞች የዕድሜ ጉዳይ አሳሳቢ ደረጃ ላይ ደርሷል ተባለ

ዶፒንግና የስፖርተኞች የዕድሜ ጉዳይ አሳሳቢ ደረጃ ላይ ደርሷል ተባለ

ቀን:

አበረታች ቅመሞች (ዶፒንግ) እና የስፖርተኞች ዕድሜ ጉዳይ እጅግ አሳሳቢና አስቸጋሪ እየሆነ መምጣቱን የወጣቶችና ስፖርት ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡ ሚኒስቴሩ ማክሰኞ ሚያዝያ 3 ቀን 2009 ዓ.ም. ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የተቋሙን የ2009 በጀት ዓመት የስምንት ወራት የዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ሲያቀርብ ይህንኑ ይፋ አድርጓል፡፡ የወጣቶችን ሁለንተናዊ ተሳትፎና ፍትሐዊ ተጠቃሚነት የሚረጋገጥባቸው በተለይም በስፖርቱ የተለያዩ የሕግ ማዕቀፎች እየተቀረፁ እንደሚገኝም ሚኒስትሩ አቶ ርስቱ ይገዙ መግለጻቸው ታውቋል፡፡

የዓለም አቀፍ የፀረ አበረታች ቅመሞች ኤጀንሲ (ዋዳ) በቅርቡ ኢትዮጵያን ጨምሮ አምስት አገሮች የችግሩ ተጠቂዎች መሆናቸውን ይፋ ማድረጉ ይታወሳል፡፡ ዋዳ ኢትዮጵያን የችግሩ አንድ አካል አድርጎ ቢጠቅሳትም፣ አገሪቱ እያደረገች ያለውን የቁጥጥርና የክትትል ሥርዓት ግምት ውስጥ በማስገባት ኤጀንሲው ለመጨረሻ ጊዜ ያስቀመጠውን ጊዜ ገደብ እንዲራዘም ማድረጉ አይዘነጋም፡፡

ኢትዮጵያ አበረታች ቅመሞችን በጽኑ ከሚቃወመው ዋዳ ጎን እንደምትቆም፣ ሰኔ 30 ቀን 1999 ዓ.ም. በአዋጅ ቁጥር 554/1999 ስፖርትን በተመለከተ የወጣውን የፀረ አበረታች ቅመሞች ዓለም አቀፍ ስምምነቶችን ተቀብላ ማጽደቋም ይታወሳል፡፡

- Advertisement -

በዚሁ መነሻነት የፀረ ዶፒንግ ሥራ በተቀናጀና በተደራጀ መልኩ ለመምራት እንዲያስችል ገለልተኛ የሆነ የፀረ ዶፒንግ ጽሕፈት ቤት ለማቋቋም በተያዘው ዕቅድ መሠረት የሚኒስትሮች ምክር ቤት በደንብ ቁጥር 400/2009 እንዲቋቋም የወሰነ መሆኑን ሚኒስቴሩ በሪፖርቱ ይፋ አድርጓል፡፡

ጽሕፈት ቤቱም ባለፉት ስምንት ወራት የተጠናከረ የስፖርት ሳይንስ፣ ሕክምና ፀረ ዶፒንግ መከላከልና መቆጣጠር የማስፈጸም አቅም ለማጎልበት ሁለት የሕክምና ኮሚቴዎች፣ ሁለት የፀረ ዶፒንግ ኮሚቴዎች ለማደራጀትና ስምንት የፀረ ዶፒንግ ተጠሪዎች በብሔራዊ ፌዴሬሽኖች ደረጃ ለመለየት ታቅዶ፣ የስፖርት ሕክምና ኮሚቴ፣ የፀረ ዶፒንግ ኮሚቴና 66 የፀረ ዶፒንግ ተጠሪዎች በብሔራዊ ፌዴሬሽኖች መለየታቸው ጭምር ለምክር ቤቱ ቀርቦ አስተያየት እንዲቀርብበት ተደርጓል፡፡

በስፖርት ሳይንስ፣ በስፖርት ሕክምናና ፀረ አበረታች ቅመሞች መከላከልና መቆጣጠር በስምንት ወር ውስጥ ለ3,425 አካላት የግንዛቤ ማስጨበጫ ትምህርትና ሥልጠና ተሰጥቷል፡፡ ከዚሁ ጎን ለጎን ለ1,874 ስፖርተኞች አገልግሎት ለመስጠት በታቀደው መሠረት ለ9,395 የተለያዩ አካላት ሥልጠና ተሰጥቷል፡፡ ለ5,158 ስፖተኞች የጤናና አካል ብቃት ምርመራ፣ በሰውነት ቅመሞች ወቅታዊ ምርመራ፣ በስፖርት ፊዚዮቴራፒ፣ ስፖርት ማሳጅ፣ ማኑፑሌሽን፣ ሪሀብሊቴሽን፣ ሥነ ልቦናና ድንገተኛ አደጋ ሕይወት አድን አገልግሎት መስጠት የሚያስችል ሥልጠና ስለመሆኑም በሪፖርቱ ተካቷል፡፡

ይሁንና ሚኒስትሩ ለተወካዮች ምክር ቤት እንደሰጡት ማብራሪያ ከሆነ፣ እነዚህ ሁሉ እንቅስቃሴዎች ባሉበት የዶፒንግ ጉዳይ እጅግ አሳሳቢና አስቸጋሪ እየሆነ መምጣቱን ነው አስምረው ያብራሩት፡፡ ከዚሁ ጎን ለጎን ከዶፒንግ ባልተናነሰ የስፖርተኞች የዕድሜ ጉዳይ  ተመሳሳይ ችግር መሆኑን መግለጻቸው ታውቋል፡፡

እንደ ሚኒስትሩ፣ ስፖርተኞችን በየዕድሜያቸው በመመልመል በማዕከላት ለማቀፍ እየተደረገ ያለው ጥረት፣ ትክክለኛ ዕድሜን በመደበቅ ዕቅዱ ዕውን እንዳይሆን ከፍተኛ ችግር እየሆነ መምጣቱን ጭምር ማብራራታቸው ታውቋል፡፡

‹‹ከ17 ዓመት በታች ያሉ ስፖርተኞችን ለመመልመል ጥረት ሲደረግ የሚመጡት ከተጠቀሰው ዕድሜ በላይ ያሉት ናቸው፡፡ አገሪቱ ውስጥ የመዝገብ አያያዝ ችግር ስላለ ሚኒስቴሩ ትክክለኛ ዕድሜያቸውን ለማወቅ ተቸግሯል፤›› ብለዋል፡፡ ችግሩን ለመቅረፍም ዓለም አቀፍ ዘመናዊ የምርመራ ስልቶችን ለመከተል አስቸጋሪ እየሆነ መምጣቱን ያስረዱ ሚኒስትሩ፣ ይህ በራሱ ወደ ትክክለኛው ዕድሜ የሚያቀርብ እንጂ እርግጠኛውን ለማወቅ እንደማያስችልም በማብራሪያቸው ማካተታቸው ታውቋል፡፡

 

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የምግብ ዋጋ ንረት አጣዳፊ ዕርምጃ ያስፈልገዋል!

መንግሥት የሚቀጥለውን ዓመት በጀት ይዞ ሲቀርብ በአንገብጋቢነት ከሚነሱ ጉዳዮች...

ከባለአንድ ዋልታ ወደ ባለብዙ ዋልታ የዓለም ሥርዓት የመሸጋገራችን እውነታ

በአብዱ ሻሎ አንገት ማስገቢያ እ.ኤ.አ. በፌብሩዋሪ 2022 የሩሲያ መንግሥት በዩክሬን ‹‹ልዩ...

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የውጭ ግንኙነት የሺሕ ዘመናት ታሪኳና እሴቶቿን የሚመጥን መሆን ይኖርበታል

(ክፍል አንድ) በተረፈ ወርቁ (ዲ/ን) እንደ መንደርደሪያ ለዛሬው የግል ትዝብቴንና ታሪክን ላዛነቀው...

ከአገር ግንባታ ጋር የተያያዙ ወሳኝ የቅርብ ታሪካችን አንጓዎች

በታደሰ ሻንቆ በአያሌው የተመረጡና ልጥ የሌላቸው ነጥቦች የተደራጁበት ይህ ታሪክ...