የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን
‹‹ከሰበታ በሬ ገዝተው ወደ አዲስ አበባ ሲያመሩ የነበሩ ግለሰብ በገዙት በሬ ተወግተው ሕይወታቸው አልፏል፡፡››
ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት
ክርስቲያኖች ሚያዝያ 8 ቀን 2009 ዓ.ም. ያከበሩት የዘንድሮው ፋሲካ፣ ፍፁም ሰላማዊ ሆኖ ማለፉን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን በሕዝብ ግንኙነት በሰጠው ቀዳሚው መግለጫ ያስታወቀበት አገላለፅ ነው፡፡ በሌላ በኩልም የአዲስ አበባ ነዋሪ የነበሩ ግለሰብ ከሰበታ በሬ ገዝተው በአይሱዙ ጭነው ወደ አዲስ አበባ ሲያመሩ፣ ከክፍት ተሽከርካሪው ላይ ዘሎ የወረደውን በሬ ለመያዝ ጥረት ቢያደርጉም በሬው ተመልሶ በማሳደድ አንገታቸውን በመውጋቱ ለኅልፈት ዳርጓቸዋል፡፡