Sunday, June 16, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -

ስፖርትየአዲስ አበባ ብስክሌት ፌዴሬሽን ጅምሮች

የአዲስ አበባ ብስክሌት ፌዴሬሽን ጅምሮች

ቀን:

በቀደሙት ኦሊምፒኮች ከአትሌቲክሱ ቀጥሎ አገሪቱ ትወከልበት እንደነበረ የሚነገርለትን ብስክሌት ወደ ቀድሞ ስምና ክብሩ ለመመለስ ከሚታትሩ የአገሪቱ ክፍሎች አዲስ አበባ ይጠቀሳል፡፡ ከሜልቦርን እስከ ባርሴሎና ኦሊምፒክ ኢትዮጵያ በብስክሌት የነበራት ተሳትፎ እስከ ቅርብ ጊዜ ጠፍቶ ቆይቷል፡፡ ሆኖም በአውሮፓ በተለያዩ አገሮች አዘውትሮ በሚካሄዱ የብስክሌት ውድድሮች ላይ በወንዶችም ሆነ በሴቶች ተስፋ የሚሰጡ ተወዳዳሪዎች ታይተዋል፡፡

ከዚህ በመነሳት ይመስላል የአዲስ አበባ ብስክሌት ፌዴሬሽን ተስፋ የሚጣልባቸው እንቅስቃሴዎች ጀምሯል፡፡ የፌዴሬሽኑ ፕሬዚዳንት አቶ ረዘነ በየነ ለዚህ ዋናውና ትልቁ ነገር አመራሩና ሙያተኛው እንዲሁም የከተማ አስተዳደሩ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ያላሰለሰ ድጋፍና ክትትል እንዲሁም የተቀናጀ የሥራ ውጤት እንደሆነ ይናገራሉ፡፡

ይህ ጅምር እንጂ የመጨረሻው ግብ እንዳልሆነ ያከሉት የፌዴሬሽኑ ፕሬዚዳንት፣ ለብስክሌት ውጤታማነት የተለያዩ ስትራቴጂካዊ ዕቅዶች ተነድፈው በመተግበር ላይ ይገኛሉ፡፡ ከዕቅዶቹ መካከል ፌዴሬሽኑ ጠንካራ የፋይናንስ አቅም እንዲኖረው የሚደረገው የስፖንሰርሽፕ ስምምነቶች ቀዳሚውን ሥፍራ እንደሚይዝ ያስረዳሉ፡፡ ሌላው ደግሞ ከመደበኛ የውድድር መርሐ ግብሮች ጎን ለጎን የታዳጊ ወጣቶች ፕሮጀክት ላይ የሚደረገው እንቅስቃሴ እንደሆነም ተናግረዋል፡፡

- Advertisement -

እንደ ኃላፊው፣ የአዲስ አበባ ብስክሌት ፌዴሬሽን ብስክሌቱን በከፍተኛ በጀት እያንቀሳቀሱ ከሚገኙት የትግራይና የአማራ ክልሎች አንፃር ይህ ነው የሚባል ጠንካራ የበጀት ድጋፍ የለውም፡፡ የፌዴሬሽኑ ዓመታዊ በጀት 180 ሺሕ ብር መሆኑንና በዚህ ደግሞ የአዲስ አበባ ብስክሌት የተፎካካሪነት አቅም የትም ማድረስ እንደማይቻል የሚናገሩት አቶ ረዘነ፣ በከተማ አስተዳደሩ ሥር በመስፋፋት ላይ ከሚገኙ ካምፓኒዎችና ድርጅቶች ጋር የጋራ ተጠቃሚነት ላይ ጠንካራ ሥራ እየተሠራ ስለመሆኑ ጭምር ይናገራሉ፡፡ እስካሁንም ከኮካ ኮላ ካምፓኒ ጋር የተደረገው ስምምነት ተጠቃሽ  እንደሆነ ያስረዳሉ፡፡

የከተማው ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ በበኩሉ፣ ወደ 60 የሚጠጉ የኮርስ ብስክሌቶችን ማበርከቱ ፌዴሬሽኑ በክፍለ ከተሞች ላይ ለጀመራቸው ፕሮጀክቶች ትልቅ መነሳሳት እንደፈጠረላቸው ያከሉት አቶ ረዘነ፣ በአሁኑ ወቅት በስድስት ክፍለ ከተሞች ጠንካራ የፕሮጀክት ጅምሮች በመንቀሳቀስ ላይ እንደሚገኙ ተናግረዋል፡፡ በዚህ መነሻነት ቀደም ባሉት ዓመታት ለትግራይና ለአማራ ብስክሌተኞች አጃቢ የነበረው የአዲስ አበባ ብስክሌት በተያዘው የውድድር ዓመት ጠንካራ ተፎካካሪ ለመሆን መብቃቱን ጭምር ይናገራሉ፡፡

አዲስ አበባ የአገሪቱ መዲና እንደመሆኗና በውስጧ አቅፋ በያዘቻቸው ካምፓኒዎችና ድርጅቶች መጠን ተጠቃሚ መሆን እንዳልቻለች የሚናገሩት የፌዴሬሽኑ ፕሬዚዳንት፣ እነዚህን አጋጣሚዎች መጠቀም ወቅቱ የሚጠይቀው የውዴታ ግዴታ መሆኑን ጭምር ያስረዳሉ፡፡

የአዲስ አበባ ብስክሌት ፌዴሬሽን የቀድሞ ኦፊሰር አቶ ፈለቀ ዋቄ በበኩላቸው፣ የአዲስ አበባ ብስክሌት ቀድሞ ከነበረበት ሁኔታ አንፃር በአሁኑ ወቅት ከፍተኛ የሆነ የአደረጃጀትና የአሠራር ለውጥ አድርጓል ሲሉ የፕሬዚዳንቱን አስተያየት ያጠናክራሉ፡፡ ከፕሮጀክት ጀምሮ የክለቦች ቁጥር እየጨመረ መምጣቱን የሚናሩት ባለሙያው፣ የተወዳዳሪዎች ቁጥር በሁለቱም ፆታ በአሁኑ ወቅት ከ35 እስከ 45 መድረሱን ጭምር ይናገራሉ፡፡

ለብስክሌቱ ውጤት መውደቅ ዓይነተኛው ምክንያት የሚሉት ባለሙያው፣ ለተወዳዳሪዎች ሲደረግ የቆየው ድጋፍና ክትትል ማነስ እንደሆነ ገልጸው፣ አሁን ባለው ሁኔታ ግን ለተወዳዳሪዎች ከወርኃዊ ክፍያ ጀምሮ ጥራት ያላቸው የመወዳደሪያ ቁሳቁሶች ደረጃቸውን የጠበቁ እንደሆኑ መደረጉን ያስረዳሉ፡፡ በዚህ መነሻነትም ከስፖርቱ ርቀው የቆዩ ተወዳዳሪዎች ወደ ቀድሞ ብቃታቸው ለመመለስ ጠንካራ ተሳትፎ እያደረጉ እንደሚገኙ ጭምር ነው ያስረዱት፡፡

በአዲስ አበባ በአሁኑ ወቅት የአፍሪካ ስደተኞች ቡድንን ጨምሮ ስድስት ክለቦች ማለትም ኢትዮ ኤሌክትሪክ፣ ጋራድ ኩባንያ፣ እህል ንግድ ድርጅት፣ የኢትዮጵያ ወጣቶች አካዴሚ፣ ኢትዮጵያ ንግድ ሥራዎችና የካ ክፍለ ከተማ በዋናነት ተጠቃሽ መሆናቸውንም ባለሙያው ይናገራሉ፡፡ የብስክሌት ተነሳሽነት አሁን ባለው ሁኔታ የሚቀጥል ከሆነ የአዲስ አበባ ብስክሌት ወደ ቀድሞ ስምና ክብሩ የሚመለስበት ጊዜ ሩቅ እንደማይሆንም እምነታቸው መሆኑን ተናግረዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የምግብ ዋጋ ንረት አጣዳፊ ዕርምጃ ያስፈልገዋል!

መንግሥት የሚቀጥለውን ዓመት በጀት ይዞ ሲቀርብ በአንገብጋቢነት ከሚነሱ ጉዳዮች...

ከባለአንድ ዋልታ ወደ ባለብዙ ዋልታ የዓለም ሥርዓት የመሸጋገራችን እውነታ

በአብዱ ሻሎ አንገት ማስገቢያ እ.ኤ.አ. በፌብሩዋሪ 2022 የሩሲያ መንግሥት በዩክሬን ‹‹ልዩ...

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የውጭ ግንኙነት የሺሕ ዘመናት ታሪኳና እሴቶቿን የሚመጥን መሆን ይኖርበታል

(ክፍል አንድ) በተረፈ ወርቁ (ዲ/ን) እንደ መንደርደሪያ ለዛሬው የግል ትዝብቴንና ታሪክን ላዛነቀው...

ከአገር ግንባታ ጋር የተያያዙ ወሳኝ የቅርብ ታሪካችን አንጓዎች

በታደሰ ሻንቆ በአያሌው የተመረጡና ልጥ የሌላቸው ነጥቦች የተደራጁበት ይህ ታሪክ...