‹‹መሰናክልህን ውደደው›› በሪያን ሆሊዴይ ተጽፎ በአካሉ ቢረዳ ወደ አማርኛ የተተረጎመ መጽሐፍ ነው፡፡ በያዝነው ዓመት የኅትመት ብርሃን ያየው መጽሐፍ፣ በሕይወት ውስጥ የሚገጥሙ መሰናክሎችን የማለፍን ጥበብ ያሳያል፡፡ በተለያየ ሙያ መስክ ስኬታማ የሆኑ ዕውቅ ሰዎችን ተሞክሮ በመመርኮዝ፣ ውጣ ውረድ የማይገጥመው የሰው ልጅ እንደሌለና ዋናው መሰናክልን ማለፊያ ብልሀት ማበጀት እንደሆነ ያስነብባል፡፡ ሦስት ክፍሎችና 196 ገጾች ያሉት መጽሐፉ፣ መሰነክሎችን ለማለፍ የሚረዱ ዘዴዎችንም ይጠቁማል፡፡