Monday, December 9, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናየተንዳሆ ስኳር ፋብሪካ ሰባት ኃላፊዎችና አንድ ባለሀብት ተከሰሱ

የተንዳሆ ስኳር ፋብሪካ ሰባት ኃላፊዎችና አንድ ባለሀብት ተከሰሱ

ቀን:

spot_img

የተሰጣቸውን ኃላፊነት ያላግባብ በመገልገልና ከሥልጣቸው በላይ በመጠቀም ከ200 ሚሊዮን ብር በላይ በመንግሥትና ሕዝብ ሀብት ላይ ጉዳት አድርሰዋል የተባሉ፣ በኢትዮጵያ ስኳር ኮርፖሬሽን የተንዳሆ ስኳር ፋብሪካ በተለያዩ የሥራ ኃላፊነት ላይ የነበሩ ሰባት ኃላፊዎችና አንድ ባለሀብት ላይ ክስ ተመሠረተ፡፡

የፌዴራል ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ መስከረም 12 ቀን 2010 ዓ.ም. በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ተረኛ ችሎት ክስ የመሠረተባቸው፣ በስኳር ኮርፖሬሽን የአገዳ ተከላና ፋብሪካ ግንባታ ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ አበበ ተስፋዬ (ኢንጂነር) ናቸው፡፡ እንዲሁም የመስኖና ቤቶች ግንባታ ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር  አቶ ኪሮስ ደስታ (ኢንጂነር)፣ የአገዳ ተክል ልማትና ፋብሪካ ፕሮጀክቶች ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ደረጀ ጉተማ (በሌሉበት)፣ ዋና ሥራ አስኪያጅ የነበሩት አቶ ዮሴፍ በጋሻው፣ ጊዜያዊ ዋና ሥራ አስኪያጅ የነበሩት አቶ አታክልቲ ተስፋዬ፣ የተንዳሆ ስኳር ፋብሪካ ዋና ሥራ አስኪያጅ የነበሩት ኮሎኔል መላኩ ድጋፌና ባለሀብቱ የማነ ግርማይ ጠቅላላ ተቋራጭ ሥራ ዋና አስኪያጅና ባለቤት አቶ ግርማይ የማነ በክሱ ተካተዋል፡፡

ተከሳሾቹ የተሰጣቸውን ኃላፊነት ወደ ጎን በመተውና በጥቅም በመተሳሰር የፋብሪካውን ንብረት ለሦስተኛ ወገን በትውስት ለመስጠት የሚፈቀድ አሠራር ሳይኖር፣ ለየማነ ግርማይ ጠቅላላ ተቋራጭ 40,000 ሜትር ኪዩብ ጠጠር እንዲሰጣቸው ማድረጋቸውን ዓቃቤ ሕግ በክሱ ገልጿል፡፡ ኃላፊዎቹ በቃልና በጽሑፍ በሰጡት ትዕዛዝ 24,179.66 ሜትር ኪዩብ የሚሆን የአርማታ ጠጠርም እንዲሰጥ ማድረጋቸውንም አክሏል፡፡

ኃላፊዎቹ ሲምፕሌክስ ኢንፍራስትራክቸርስ ሊሚትድ ለሚባል ድርጅትም፣ 8,955 ሜትር ኪዩብ የአርማታ ጠጠር እንዲሰጠው ማድረጋቸውንም ዓቃቤ ሕግ በክሱ ጠቁሟል፡፡ 184,654.12 ኪሎ ግራም ጠጠር በተጨማሪ ለየማነ ግርማይ ጠቅላላ ተቋራጭ በብድር በመስጠት በድምሩ በሁለቱ ድርጅቶች 25,167,676 ብር ጉዳት እንዲደረስ ማድረጋቸውን ዓቃቤ ሕግ በክሱ ገልጿል፡፡

ኃላፊዎቹ በተለያዩ ጊዜያት ኦአይኤና ሲሚፕሌክስ ኢንፍራንስትራክቸርስ ሊሚትድን ጨምሮ የአርማታ ጠጠርና ብረት ያላግባብ ለሦስቱ ድርጅቶች በመስጠት ሳያስመልሱ በመቅረታቸው፣ በፋብሪካው ላይ ከ200 ሚሊዮን ብር በላይ የሚደርስ ከፍተኛ ጉዳት ማድረሳቸውን ዓቃቤ ሕግ ክሱን በዝርዝር አቅርቧል፡፡

በተከሳሾች ላይ የተጠቀሰባቸው የሕግ አንቀጽ ዋስትና የሚከለክል መሆኑን በመግለጽ በማረሚያ ቤት ሆነው እንዲከራከሩ ፍርድ ቤቱ ትዕዛዝ ሰጥቶ፣ በክሱ ላይ መቃወሚያ ካላቸው ለመጠባበቅ ለጥቅምት 8 ቀን 2010 ዓ.ም. ቀጥሮአቸዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ከምክክርና ከድርድር ውጪ ምን ዓይነት አማራጭ ይኑረን?

በዘውዳለም መንገሻ የዘመናዊት ኢትዮጵያ ፖለቲካ ውዝግብ በትንሹ የአንድ ምዕተ ዓመት...

ነፃነትና ሰንሰለት

(ክፍል አንድ) በታደሰ ሻንቆ 1) ‹‹ውስጣዊ ሰንሰለቶች እንዳሉ ሁሉ ውጫዊ ሰንሰለቶችም...

ገበያውን ሊያረጋጉ የሚችሉ አዳዲስ መፍትሔዎችን ማምጣት ያስፈልጋል!

የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ሚኒስትር ካሳሁን ጎንፌ (ዶ/ር) በሕዝብ...

አዲሱ የሕንፃ አዋጅ ‹ድርጅት ተኮር› ሳይሆን ‹ባለሙያ ተኮር› ተደርጎ መዘጋጀት አለበት የኢትዮጵያ አርክቴክቶች ማኅበር

የኢትዮጵያ አርክቴክቶች ማኅበር በቀድሞ የሕንፃ አዋጅ የነበረውን ‹‹ባለሙያ ተኮር››...