Wednesday, February 28, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊለአዳዲስ መኖሪያ ቤቶች ግንባታ 20 ቢሊዮን ብር በጀት ተያዘ

ለአዳዲስ መኖሪያ ቤቶች ግንባታ 20 ቢሊዮን ብር በጀት ተያዘ

ቀን:

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በ2010 በጀት ዓመት 25 ሺሕ አዳዲስ ቤቶችን ለመጀመር ቢያቅድም፣ ይህ ዕቅድ አሁንም ውይይት እየተደረገበት በመሆኑ የሚገነቡት ቤቶች ቁጥር ሊጨምርም፣ ሊቀንስም እንደሚችል ተገልጿል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቤቶች ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ይድነቃቸው ዋለልኝ ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ የቤቶቹ ቁጥር ላይ ውይይት እየተካሄደ ነው፡፡ ‹‹በዚህ ዓመት የሚጀመሩት ቤቶች ቁጥር ሊጨምር ወይም ሊቀንስ ይችላል፡፡ ከተመደበው በጀት ጋር በተጣጣመ መንገድ የመኖርያ ቤቶችን ግንባታ ለማካሄድ ዝግጅት እየተካሄደ ነው፤›› ሲሉ አስረድተዋል፡፡

ለአዳዲሶቹ የጋራ መኖሪያ ቤቶች ግንባታ የሚውለውን 20 ቢሊዮን ብር የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እንደሚያቀርብ ተገልጿል፡፡

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ለ20/80 እና ለ40/60 ፕሮግራሞች 31.03 ቢሊዮን ብር ያስፈልግ ነበር፡፡ ነገር ግን ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሊገኝ የቻለው 15 ቢሊዮን ብር ብቻ ነው፡፡

ከዚህ ገንዘብ ውስጥ 8.5 ቢሊዮን ብር የ20/80 ቤቶችን ለሚገነባው የአዲስ አበባ ቤቶች ግንባት ፕሮጀክት ጽሕፈት ቤት፣ እንዲሁም 6.5 ቢሊዮን ብር የ40/60 ቤቶችን ለሚገነባው የአዲስ አበባ ቁጠባ ቤቶች ልማት ኢንተርፕራይዝ ተመድቧል፡፡

በዚህ በጀት ቀደም ባሉት ዓመታት የተጀመሩ 132 ሺሕ ነባር ፕሮጀክቶች ግንባታቸው ቀጥሏል፡፡ ነገር ግን እነዚህ ቤቶችም ቢሆኑ በታሰበላቸው ዕቅድ አልሄዱም፡፡ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ድሪባ ኩማ የ2009 ዓ.ም. ዕቅድ አፈጻጸምና የ2010 በጀት ዓመት ዕቅድ በቅርቡ ለከተማው ምክር ቤት ሲያቀርቡ፣ በ2009 ዓ.ም. የመጀመርያው ግማሽ ዓመት ባጋጠመ የገንዘብ እጥረትና የአንዳንድ የሥራ ተቋራጮች ደካማ መሆን ለሥራ አፈጻጸሙ ዝቅተኛነት አስተዋጽኦ አበርክቷል ብለዋል፡፡

በ2010 በጀት ዓመት የተያዘው 20 ቢሊዮን ብር በጀት ካለፉት ዓመታት ጋር ሲነፃፀር ትልቁ መሆኑን አቶ ይድነቃቸው ገልጸዋል፡፡ ነገር ግን አሁንም ቢሆን ተመዝግበው ቤታቸውን የሚጠባበቁ ነዋሪዎች በሚፈልጉትና የሁለተኛው የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ባስቀመጠው መሠረት፣ የመኖርያ ቤቶች ግንባታ እየተፋጠነ አይደለም፡፡ የፋይናንስ አቅርቦቱም በታቀደው መሠረትም አይደለም፡፡

የ10/90 ጨምሮ በሦስቱ ፕሮግራሞች ከተመዘገቡ 900 ሺሕ ያህል ነዋሪዎች መካከል የቤት ባለቤት መሆን የቻሉት 175 ሺሕ ያህል ናቸው፡፡ በግንባታ ላይ ያሉት 132 ሺሕ ቤቶች ሲሆኑ፣ በዕቅድ ደረጃ በ2010 ዓ.ም. ይገነባሉ የተባለው 25 ሺሕ ቤቶች ናቸው፡፡

ከዚህ አንፃር ተመዝግበው በመጠባበቅ ላይ የሚገኙ ነዋሪዎች ዘወትር ቤታቸውን መቼ እንደሚያገኙ በመጠየቅ ላይ ይገኛሉ፡፡ ከዚህ በተጨማሪም በሁለተኛው የአምስት ዓመት የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ጊዜ ውስጥ 750 ሺሕ ቤቶች እንደሚገነቡ ዕቅድ አለ፡፡ ይህም ማለት በየዓመቱ 150 ሺሕ ቤቶች መገንባት ይኖርቦቸዋል፡፡

ነገር ግን የመኖርያ ቤቶች ግንባታ ዕቅድም ሆነ የገንዘብ አቅርቦቱ ተመጣጣኝ ባለመሆኑ፣ በዕቅድ ዘመኑ ውስጥ ይህንን ግዙፍ ግንባታ ማካሄድ ይቻላል ወይ? የሚለው አጠያያቂ ሆኗል፡፡ 

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

[ክቡር ሚኒስትሩ ወደ መኖሪያ ቤታቸው ሲገቡ ባለቤታቸው በቴሌቪዥን የሚተላለፈውን ዜና በመደነቅ እየተመለከቱ አገኟቸው]

እንዲያው የሚደንቅ ነው እኮ። ምኑ? ዜና ተብሎ በቴሌቪዥን የሚተላለፈው ነገር ነዋ፡፡ ምኑ...

በኦሮሚያ የሚፈጸሙ ግድያዎችና የተጠያቂነት መጥፋት

የካቲት 11 ቀን 2016 ዓ.ም. ቢሾፍቱ አቅራቢያ በሚገኘው የዝቋላ...

የኢትዮጵያ መዋዕለ ንዋይ ገበያ ከሚያስፈልገው ካፒታል ውስጥ 90 በመቶውን ሰበሰበ

እስካሁን 15 ባንኮች የመዋዕለ ንዋይ ገበያው ባለድርሻ ሆነዋል የኢትዮጵያ መዋዕለ...

አዲሱ የንብ ባንክ ቦርድ የባንኩን ካፒታል በአሥር ቢሊዮን ብር ለማሳደግ ማቀዱ ተሰማ

አዲሱ የንብ ኢንተርናሽናል ባንክ የዳይሬክተሮች ቦርድ የባንኩን ካፒታል በአሥር...