Tuesday, April 23, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -

ዜናከሶማሌላንድ ሦስት ሺሕ የኦሮሞ ተወላጆች ተፈናቀሉ

ከሶማሌላንድ ሦስት ሺሕ የኦሮሞ ተወላጆች ተፈናቀሉ

ቀን:

ከጎረቤት ሶማሌላንድ ሦስት ሺሕ የኦሮሞ ብሔር ተወላጆች መፈናቀላቸው ተሰማ፡፡

በኦሮሚያና በሶማሌ ክልላዊ መንግሥታት የጋራ ድንበር አካባቢ በሚኖሩ የኦሮሞና የሶማሌ ተወላጆች መካከል በተፈጠረው ግጭት ሳቢያ፣ በበርካታ ሺዎች የሚቆጠሩ ኦሮሞዎች ከሶማሌ ክልል ሲፈናቀሉ በተመሳሳይ በኦሮሚያ ክልል ይኖሩ የነበሩ ሶማሌዎችም ተፈናቅለዋል፡፡

የሁለቱ ብሔሮች ተወላጆች ግጭት ድንበር ዘሎ ኢትዮጵያ ከሕግ በመለስ እንደ አገር ዕውቅና በሰጠቻት ሶማሌላንድ ውስጥ የሚኖሩ ከሦስት ሺሕ በላይ ኦሮሞዎችም መባረራቸውን፣ የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ሚኒስትሩ ነገሪ ሌንጮ (ዶ/ር) ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

ሚኒስትሩ እንደገለጹት፣ የተፈናቀሉት የኦሮሞ ተወላጆች በአሁኑ ወቅት ቶጎ ውጫሌ በሚባለው የኢትዮጵያ ድንበር እንደሚገኙና ወደ ኦሮሚያ ክልል በመግባት ላይ ናቸው፡፡

የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥትና የክልሉ ገዢ ፓርቲ የኦሮሞ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ ድርጅት (ኦሕዴድ) ከፍተኛ አመራሮች በዚህ ግጭትና ተፈናቃዮችን በመቀበል ላይ ከሕዝብ ጋር በተለያዩ አካባቢዎች ተሰማርተው እየመከሩ መሆኑ ታውቋል፡፡

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ወርቅነህ ገበየሁ (ዶ/ር) በጉዳዩ ላይ ከሶማሌላንድ መንግሥት ኃላፊዎች ጋር እየተነጋገሩ መሆኑንም ለማወቅ ተችሏል፡፡ ሚኒስትሩ ግጭቱ በተከሰተባቸው አካባቢዎች በመዘዋወርም የተፈናቀሉ ወገኖችንና የአገር ሽማግሌዎችን እንዳነጋገሩ የሪፖርተር መረጃዎች አመልክተዋል፡፡

ዜጎች ከቦታ ወደ ቦታ በመዘዋወር የመሥራት መብታቸውን መንግሥት እንደሚያረጋግጥላቸው ለተፈናቃዮቹ የተናገሩት ሚኒስትሩ፣ የፌዴራል መንግሥት ከሁለቱ ክልሎች አመራሮች ጋር ሆኖ ዜጎችን ወደ ቀዬአቸው ለመመለስ ጥረት በማድረግ ላይ መሆኑን ማስታወቃቸው ተሰምቷል፡፡

ከኦሮሚያ ክልል በተጨማሪ በሶማሌ ክልል ርዕሰ ከተማ ጅግጅጋ ከአገር ሽማግሌዎች ጋር ውይይት ያደረጉ ሲሆን፣ መንግሥት ካሁን በኋላ ግጭቶች እንዳይቀሰቀሱ የበኩሉን ኃላፊነት እንደሚወጣ መናገራቸው ታውቋል፡፡

 

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ሰው መሆን ምንድን ነው? ቅርስና ማኅበራዊ ፍትሕ

በሱራፌል ወንድሙ (ዶ/ር) ዳራ ከጎራዎች፣ ከመፈራረጅ፣ ነገሮችን ከማቅለልና ከጊዜያዊ ማለባበስ ወጥተን...

ኢኮኖሚው ኢትዮጵያን እንዳያፈርሳት ያሠጋል

በጌታቸው አስፋው ኢትዮጵያን እንዳያፈርሱ የሚያሠጉኝ አንድ ሁለት ብዬ ልቆጥራቸው የምችላቸው...

የኢትዮጵያ የፖለቲካ ትግል በሕግ አምላክ ይላል

በገነት ዓለሙ የአገራችንን ሰላም፣ የመላውን ዓለም ሰላም ጭምር የሚፈታተነውና አደጋ...

በሽግግር ፍትሕ እንዲታዩ የታሰቡ የወንጀል ጉዳዮች በልዩ ፍርድ ቤት ሳይሆን በልዩ ችሎት እንዲታዩ ተወሰነ

የኤርትራ ወታደሮች በሌሉበትም ቢሆን ይዳኛሉ ተብሏል በፅዮን ታደሰ የሽግግር ፍትሕ የባለሙያዎች...