Friday, June 2, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
- Advertisement -

ፌርማታ ፅሁፎች

ፌርማታ

ትኩስ ፅሁፎች

በመቐለ ከተማ የመስቀል በዓል በሚከበርበት ጮምአ ላይ የተተከለው 52 ሜትር መስቀል መስከረም 14 ቀን 2010 ዓ.ም. በብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ አቡነ ማትያስ ተመርቋል፡፡ ቅዱስ ፓትርያርኩ በምረቃው ላይ ባደረጉት ንግግር መስቀል የሰላም ምልክት በመሆኑ ሁሉም ለሰላም ትኩረት እንዲሰጥ አሳስበዋል፡፡ በዊነር ኢንዱስትሪያል ኢንጂነሪንግ የተሠራው ይህ መስቀል ከመንፈሳዊነቱ ባሻገር ለኢኮ ቱሪዝም ጠቀሜታ እንደሚኖረው የከተማዋ ባህልና ቱሪዝም ጽሕፈት ቤት አስታውቋል፡፡ ለመስቀሉ የወጣው ገንዘብ መጠን ግን አልተገለጸም።

የክፍላችን ገጽታ

ስንቶቻችን ይሆን ዕውቀት የቀሰምነው

መምህር ጓዛቸውን ጠቅልለው ሲገቡ

እንኳን ደኅና መጡ ኧረ ቶሎ ይግቡ

እኛን በሹፈት የለም የሚያህለን

መምህር ሲያስተምር አጉሊ መነጽር የለም የሚያህለው

ሁላችንም ተዋደን ወሬ ስናወራ

ጊዜያችን አለፈ ፍሬ ሳናፈራ

በርግጥ አሉ የተባሉ

ጊዜያቸውን ተጠቅመው ቁም ነገር ላይ ያዋሉ

እኛ ግን ሳይገባን የህይወት ቁምነገሩ

እንደው ስናሽሟጥጥ ተዘጋብን በሩ

ንብረት ተካ፣ የእኔ ባለውለታ፣ (2006)

********

በስፔን የባህር ዳርቻ የተገኘ ግዙፍ የባህር ኤሊ

የባህር ኤሊዎች በመጠናቸው ተቀራራቢ ቢሆኑም ሰሞኑን ከስፔን የባህር ዳርቻ የተገኘው ግዙፍ የባህር ኤሊ ሁለት ሜትር ርዝመትና 700 ኪሎ ግራም ክብደት በማስመዝገብ ትልቁ ተብሏል፡፡

የባህር ኤሊው ከባህር ዳርቻ ወጥቶ የተገኘው ሞቶ ሲሆን፣ የጀርባ ክፍሉም እንደተለመደው ሸካራና ጠንካራ ሳይሆን የቆዳ እንደነበር ኤም ኤስ ኤን አስፍሯል፡፡ ከዚህ ቀደም የጀርባ ክፍሉ ቆዳ የሆነ የባህር ኤሊ ተገኝቶ የነበረ ቢሆንም፣ ክብደቱ ግን 300 ኪሎ ግራም ነበር፡፡

በሜዴትራኒያን ግዙፍ የባህር ኤሊ ማየት የተለመደ አይደለም፡፡ ባለፉት 200 ዓመታት ውስጥም የታዩት ግዙፍ ኤሊዎች 10 ብቻ እንደሆኑ የሥነ ሕይወት ተመራማሪዎች ተናግረዋል፡፡ በስፔን የባህር ዳርቻ የተገኘው የባህር ኤሊ ለምርመራ ባርሴሎና ዩኒቨርሲቲ መወሰዱን ዘገባው ያሳያል፡፡ፌርማታ

*******

የሙሽራዋን የሙሽራ ልብስ ተጐታች በ250 ተማሪዎች ያስጐተቱ ሙሽሮች

ሴሪላንካውያኑ ጥንዶች ለሙሽሪት ያዘጋጁት የሙሽራ ልብስ ተጐታች 3.2 ኪሎ ሜትር ርዝመት ነበረው፡፡ ይህንን ለመጐተት በሙሽሪት ብቻ ሊቃና ስለማይችል 250 ተማሪዎችን ማሳተፍ ግድ ነበር፡፡

አጃንስ ፍራንስ ፕሬስ እንደዘገበው፣ ጥንዶቹም ልዩ እንግዳ አድርገው በጠሯቸው የሴሪላንካ ማዕከላዊ ከተማ ዋና ሚኒስትር ሥር ከሚተዳደር ትምህርት ቤት፣ 250 ተማሪዎች የሙሽራ ልብስ ተጐታች እንዲይዙ ፣100 ተማሪዎች ደግሞ አበባ እንዲበትኑ አድርገዋል፡፡

በሴሪላንካ ከዚህ ቀደም እንዲህ ርዝመት ያለው የሙሽራ ልብስ ተጐታች ታይቶ የማይታወቅና፣ ተማሪዎችም ለእንዲህ ያለ ተግባር እንደማይሳትፉ ዘገባው አስፍሮ፣ ጉዳዩም ምርመራ እየተደረበት መሆኑን ገልጿል፡፡

የአገሪቱ ብሔራዊ የሕፃናት ጥበቃ ባለሥልጣንም ጉዳዩን እየመረመረ መሆኑን አስታውቋል፡፡ፌርማታ

*******

በዓለም የመጀመሪያ የተባለው ከአሸዋ የተሠራ ማረፊያ ቤት

በቤቶች ግንባታ የተለያዩ የግንባታ ግብዓቶች የሚውሉ ቢሆንም በአውስትራሊያ የተሠራው ሆቴል በአሸዋ ክምር ብቻ በመሰራቱ በዓለም የመጀመሪያው ተብሏል፡፡

ዩፒአይ እንደሚለው፣ የእንግዳ ማረፊያ ቤቱን ለመሥራት 24 ቶን አሸዋ የፈጀ ሲሆን፣ የተመረጡ 10 ሰዎች ብቻም ለሁለት ቀን እንዲቆዩበት ተደርጓል፡፡ ፌርማታ

- Advertisement -
- Advertisement -

ተጨማሪ ለማንበብ

በብዛት የተነበቡ ፅሁፎች