Monday, November 28, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - Advertisement -
  - Advertisement -
  ኪንና ባህል‹‹የሁለት አገር ጀግና››

  ‹‹የሁለት አገር ጀግና››

  ቀን:

  ‹‹የሁለት አገር ጀግና-ኮሎኔል ጆን ቻርለስ ሮቢንሰን››  በሳምንቱ አጋማሽ ብርሃን ያገኘ መጽሐፍ ሲሆን፣ አዘጋጁ በዙ ተሰማ ናቸው፡፡ መጽሐፉ ስለ ጥቁር አሜሪካዊው ተዋጊ አውሮፕላን አብራሪ ኮሎኔል ጆን ቻርለስ ሮቢንሰን የሕይወት ታሪክ የሚያወሳ ነው፡፡ ሮቢንሰን  ለኢትዮጵያ ካበረከተው አስተዋጽኦ አንጻር ታሪኩ የሚገባውን ቦታ ሳያገኝ ዓመታት ተቆጥረዋል፡፡ ሆኖም በቂ ባይሆንም አንዳንድ ጅማሬዎች እየተስተዋሉ ነው፡፡ በአሜሪካ ኤምባሲና በኢትዮጵያ አየር መንገድ ቅጥር ግቢ ለመታሰቢያው የተሠሩ ሐውልቶች ተጠቃሽ ናቸው፡፡

  አዘጋጁ በመጽሐፉ መግቢያ ያተቱትም ይህንኑ እውነታ ሲሆን፣ መጽሐፉ ከባለ ታሪኩ በተጨማሪ ጣልያንን በአርበኝነት ሲፋለሙ በቦንብ፣ በመትረየስና በመርዝ ጭስ ሕይወታቸው ላለፈ ወገኖች መታሰቢያ ተሰጥቷል፡፡ አዘጋጁ በመቅድሙ እንዳሰፈሩት፣ መጽሐፉ የሚያጠነጥንበትን የሮቢንሰን ታሪክ የጻፉት በእንግሊዝኛ፣ ጣሊያንኛ፣ ፈረንሳይኛና ጀርመንኛ ከተጻፉ መጻሕፍትና መጽሔቶች መረጃ በማሰባሰብ ነው፡፡

  በተጨማሪም ስለ አምስት ዓመቱ የጣሊያን ወረራ ታሪክ የተጻፉ መዛግብትና ኮሎኔሉን በአካል ከሚያውቁ ሰዎች ጋር የተደረገ ቃለ ምልልስ ተጣቅሰዋል፡፡ መጽሐፉ በ16 ምዕራፎች ከሮቢንስና የልጅነት ታሪክ አንስቶ፣ አውሮፕላን አብራሪ ስለሆነበት ወቅት፣ ወደ ኢትዮጵያ ስለመጣበት አጋጣሚና ስለጦርነቱ ይዳስሳል፡፡ በተጨማሪም ስለ ኢትዮጵያ አየር መንገድና አየር ኃይል ታሪክና በሮቢንሰን የሰለጠኑ ኢትዮጵያውያን የአቪዬሽን ምልምሎች ዝርዝርም ይገኝበታል፡፡

  62 ታሪካዊ ፎቶዎችንም አካቷል፡፡ በሚሊንየም ፕሪንት ለሕትመት የበቃው መጽሐፉ በ99 ብር እየተሸጠ ነው፡፡

                          *****************

  ‹‹የመጽሐፍ በዓል››

  ዝግጅት፡- ‹‹ዘ ቱክል ኦፍ ዘ ቡክ›› በሚል ለሁለት ቀናት የመጻሕፍት ፌስቲቫል  የሚካሄድ ሲሆን፣ ደራስያን፣ አሳታሚዎችና አንባቢያን ይታደማሉ፡፡ በመክፈቻው ዶ/ር አሉላ ፓንክረስትና ሌሎችም ምሁራን ወይይት ያካሂዳሉ

  ቀን፡- ሚያዝያ 13 እና 14 ቀን 2009 ዓ.ም.

  ቦታ፡- አሊያንስ ኢትዮ ፍራንሴዝ

  አዘጋጅ፡- አሊያንስ ኢትዮ ፍራንሴዝ

  spot_img
  - Advertisement -

  ይመዝገቡ

  spot_img
  spot_img

  ተዛማጅ ጽሑፎች
  ተዛማጅ

  በችግር የተተበተበው የሲሚንቶ አቅርቦት

  ሲሚንቶን እንደ ግብዓት ተጠቅሞ ቤት ማደስ፣ መገንባት፣ የመቃብር ሐውልት...

  ‹‹የናይል ዓባይ መንፈስ›› በሜልቦርን

  አውስትራሊያ ስሟ ሲነሳ ቀድሞ የሚመጣው በተለይ በቀደመው ዘመን የባህር...

  ‹‹ልብሴን ለእህቴ››

  ለሰው ልጅ መኖር መሠረታዊ ፍላጎት ተብለው ከተዘረዘሩት ውስጥ ልብስ...

  የአዲስ አበባ ትምህርት ቤቶች የምርመራ ውጤት እስከምን?

  በፍቅር አበበ የትምህርት ጥራትን፣ ውጤታማነትንና ሥነ ምግባርን ማረጋገጥ ዓላማ አድርጎ...